ዘፀአት 25 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 25:1-40

ለመገናኛው ድንኳን የሚቀርቡ ስጦታዎች

25፥1-7 ተጓ ምብ – ዘፀ 35፥4-9

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ 2“ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ።

3“ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤

“ወርቅ፣ ብርና፣ ነሐስ፤

4ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፤

5ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤

6የመብራት ወይራ ዘይት፤

ለቅብዐ ዘይቱና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤

7በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች።

8“ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው ዐድራለሁ። 9ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።

የቃል ኪዳኑ ታቦት

25፥10-20 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥1-9

10“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት25፥10 ርዝመቱ 1.1 ሜትር፣ ጐኑና ርዝመቱ 0.7 ሜትር ያህል ነው። እንዲሠሩ አድርግ። 11ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አብጅለት። 12አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ ሁለቱን በአንድ በኩል ሁለቱን በሌላ በኩል ከአራቱ እግሮች ጋር አያይዝ። 13ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው። 14መሎጊያዎችንም መሸከሚያ እንዲሆኑ በታቦቱ ማእዘኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። 15መሎጊያዎቹ ከታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ምንጊዜም መውጣት የለባቸውም። 16የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር።

17“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል25፥17 ርዝመቱ 1.1 ሜትር፣ ጐኑና ርዝመቱ 0.7 ሜትር ያህል ነው። የሆነ የስርየት መክደኛ25፥17 በትውፊት፣ የጸጋው ዙፋን በመባል ይታወቃል። ከንጹሕ ወርቅ ሥራለት። 18በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ። 19አንዱን ኪሩብ በአንደኛው፣ ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላኛው ዳር አድርግ በሁለቱም ጫፎች ሁለቱን ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር አንድ ወጥ አድርገህ ሥራቸው። 20ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍኑ፤ እርስ በርሳቸው ትይዩ በመሆንም ፊታቸውን ወደ ስርየት መክደኛው ያድርጉ። 21የስርየት መክደኛውን በታቦቱ ዐናት ላይ አስቀምጠው፤ እኔ የምሰጥህን ምስክሩንም በታቦቱ ውስጥ አስቀምጥ። 22በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል፣ በስርየት መክደኛው ላይ በዚያ እኔ ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ ለእስራኤላውያን የሚሆኑትን ትእዛዞቼንም እሰጥሃለሁ።

የኅብስቱ ማስቀመጫ ጠረጴዛ

25፥23-29 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥10-16

23“ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ።25፥23 ርዝመቱ 0.9 ሜትር፣ ጐኑና 0.5 ርዝመቱ 0.7 ሜትር ያህል ነው 24በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት። 25ዙሪያውንም አንድ ስንዝር25፥25 ወደ 8 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ስፋት ያለው ጠርዝ አብጅለት፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አድርግለት። 26ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ፣ አራቱ እግሮች ባሉበት በአራቱ ማእዘኖች ላይ አያይዘው። 27ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ይይዙ ዘንድ፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ አጠገብ ይሁኑ። 28መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሥራቸው፤ በወርቅ ለብጣቸው፤ ጠረጴዛውንም ተሸከምባቸው። 29ለመጠጥ ቍርባን መፍሰሻ ይሆኑም ዘንድ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፣ እንዲሁም ማንቈርቈሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖቹን ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው። 30በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ።

የመብራቱ መቅረዝ

25፥31-39 ተጓ ምብ – ዘፀ 37፥17-24

31“ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቆሚያና ዘንግ አብጅለት፤ ጽዋ መሰል አበባዎች፣ እንቡጦችና የፈነዱ አበባዎች ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ይሠሩ። 32ከመቅረዙ ግራና ቀኝ ጐን ጋር የተያያዙ፣ በአንዱ በኩል ሦስት በሌላው በኩል ሦስት በድምሩ ስድስት ቅርንጫፎች ይኑሩት። 33ከመቅረዙ ጋር የተያያዙት ስድስቱ ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ሦስት ጽዋ መሰል አበባዎች ጋር ያኑሯቸው። 34በመቅረዙም ላይ አበባዎች እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው አራት የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ጽዋዎች ይኑሩ። 35በመቅረዙ ላይ ላሉት ለስድስቱ ቅርንጫፎች እንቡጥ በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እንቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር፣ ሦስተኛውም እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ይሁን። 36እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከንጹሕ ወርቅ ተቀርጸው ይሠሩ።

37“ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው። 38መኰስተሪያና የኵስታሪ ማስቀመጫ ሳሕኖቹም ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። 39ለመቅረዙና ለዕቃዎቹ ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ነው። 40በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።

Thai New Contemporary Bible

อพยพ 25:1-40

เครื่องถวายสำหรับพลับพลา

(อพย.35:4-9)

1องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 2“จงสั่งชนอิสราเอลให้นำสิ่งของมาถวายเรา เจ้าจงรับของที่ทุกคนนำมาถวายเราด้วยความสมัครใจ 3เจ้าจงรับของถวายที่เขานำมามอบให้ได้แก่ ทองคำ เงิน และทองสัมฤทธิ์ 4ด้ายสีน้ำเงิน สีม่วง และสีแดง ผ้าลินินเนื้อดี ขนแพะ 5หนังแกะตัวผู้ย้อมสีแดง หนังพะยูน ไม้กระถินเทศ 6น้ำมันมะกอกสำหรับจุดประทีป เครื่องเทศสำหรับปรุงน้ำมันเพื่อใช้เจิมและสำหรับเครื่องหอม 7โกเมนและอัญมณีอื่นๆ สำหรับฝังในเอโฟดและทับทรวง

8“แล้วให้ประชากรอิสราเอลสร้างสถานนมัสการให้เรา และเราจะอยู่ท่ามกลางพวกเขา 9จงสร้างพลับพลาและทำอุปกรณ์ตกแต่งทุกอย่างตามรูปแบบที่เราจะสำแดงแก่เจ้า”

หีบพันธสัญญา

(อพย.37:1-9)

10“จงให้พวกเขาทำหีบด้วยไม้กระถินเทศขนาดยาว 2.5 ศอก25:10 คือ ยาวประมาณ 1.1 เมตร กว้างและสูงเท่ากัน 1.5 ศอก25:10 คือ กว้างและสูงประมาณ 0.7 เมตร 11หุ้มด้วยทองคำบริสุทธิ์ทั้งด้านในและด้านนอก และใช้ทองคำทำเป็นคิ้วทับโดยรอบ 12จงหล่อห่วงทองคำสี่ห่วงติดไว้ที่มุมทั้งสี่ของขอบหีบ โดยมีสองห่วงอยู่ทางด้านหนึ่งและอีกสองห่วงอยู่อีกด้านหนึ่ง 13จากนั้นจงทำคานหามสองอันจากไม้กระถินเทศหุ้มด้วยทองคำ 14สอดคานลอดห่วงทั้งสองด้านของหีบไว้สำหรับหาม 15อย่าชักคานนี้ออกจากห่วงเลย ให้คงไว้เช่นนั้นตลอดไป 16แล้วนำแผ่นศิลาจารึกพันธสัญญาซึ่งเราจะให้แก่เจ้าใส่ไว้ในหีบนั้น

17“และจงทำฝาหีบพันธสัญญา (คือพระที่นั่งกรุณา)25:17 คือ สถานลบบาป จากทองคำบริสุทธิ์ขนาดยาว 2.5 ศอก กว้าง 1.5 ศอก25:17 คือ ยาวประมาณ 1.1 เมตร กว้างประมาณ 0.7 เมตร 18แล้วเคาะทองคำบริสุทธิ์เป็นเครูบสองตนที่ปลายทั้งสองด้านของพระที่นั่งกรุณา 19เครูบทั้งสองนี้ติดเข้าเป็นเนื้อเดียวกับพระที่นั่งกรุณา 20หันหน้าเข้าหากัน มองมายังพระที่นั่งกรุณา และคลี่ปีกจดกันเหนือพระที่นั่งกรุณา 21จงตั้งพระที่นั่งกรุณานี้ไว้บนหีบ และจงบรรจุแผ่นศิลาซึ่งเราจะให้เจ้าไว้ในหีบ 22เราจะมาพบเจ้าเหนือพระที่นั่งกรุณาระหว่างเครูบทั้งสองที่อยู่เหนือหีบพันธสัญญา และแจ้งคำบัญชาทั้งหมดของเราสำหรับประชากรอิสราเอลแก่เจ้า

โต๊ะเครื่องถวายเบื้องพระพักตร์

(อพย.37:10-16)

23“แล้วจงใช้ไม้กระถินเทศทำโต๊ะตัวหนึ่งขนาดยาว 2 ศอก กว้าง 1 ศอก และสูง 1.5 ศอก25:23 คือ ยาวประมาณ 0.9 เมตร กว้างประมาณ 0.5 เมตร และสูงประมาณ 0.7 เมตร 24หุ้มด้วยทองคำบริสุทธิ์และใช้ทองคำทำเป็นคิ้วโดยรอบ 25คิ้วรอบขอบโต๊ะนี้กว้างหนึ่งฝ่ามือ25:25 คือ กว้างประมาณ 8 เซนติเมตร และมีลวดลายเป็นทองคำทาบลงไปโดยรอบอีกครั้ง 26จงทำห่วงทองคำสี่ห่วงติดไว้ที่มุมด้านนอกของขาโต๊ะทั้งสี่ขา 27ห่วงเหล่านั้นจะอยู่ใกล้กับขอบบนสำหรับสอดคานเพื่อหามโต๊ะ 28จงทำคานจากไม้กระถินเทศหุ้มด้วยทองคำเพื่อใช้หามโต๊ะ 29แล้วจงทำภาชนะด้วยทองคำบริสุทธิ์ได้แก่ จานและชาม คนโทและอ่างสำหรับใช้เทเครื่องดื่มบูชา 30และจงวางขนมปังเบื้องพระพักตร์บนโต๊ะนี้ต่อหน้าเราตลอดเวลา

คันประทีป

(อพย.37:17-24)

31“จงทำคันประทีปอันหนึ่งจากทองคำบริสุทธิ์เคาะให้เป็นตัวคันประทีปและลวดลายทั้งหมดให้เป็นเนื้อเดียวกัน คือทั้งฐาน ลำคันประทีป ถ้วยรองตะเกียงลักษณะคล้ายดอกไม้ และดอกไม้ทั้งตูมและบาน 32มีหกกิ่งแยกจากลำคันประทีป ข้างละสามกิ่งขนานกัน 33ทำกิ่งแต่ละกิ่งคล้ายดอกอัลมอนด์ทั้งตูมและบานอย่างละสามดอก บนยอดของแต่ละกิ่งนั้นทำเป็นถ้วยรองตะเกียงมีลักษณะคล้ายดอกอัลมอนด์เช่นกัน 34ลำคันประทีปทำเป็นดอกอัลมอนด์ทั้งตูมและบานอย่างละสี่ดอก บนยอดของลำคันประทีปทำเป็นถ้วยรองตะเกียงลักษณะคล้ายดอกอัลมอนด์เช่นกัน 35ให้ทำดอกตูมดอกหนึ่งรองรับกิ่งขนานคู่แรก อีกดอกหนึ่งรองรับกิ่งขนานคู่ที่สอง และอีกดอกหนึ่งรองรับกิ่งขนานคู่ที่สาม 36ลวดลายที่ตกแต่งทั้งหมดรวมทั้งกิ่งและตัวคันประทีปล้วนเป็นเนื้อเดียวกัน เคาะจากทองคำบริสุทธิ์

37“แล้วจงทำตะเกียงเจ็ดดวงวางไว้บนถ้วยรองเหล่านั้นเพื่อให้ความสว่างหน้าคันประทีป 38กรรไกรตัดไส้ตะเกียงและถาดรองทำด้วยทองคำบริสุทธิ์ 39จะต้องใช้ทองทั้งหมดหนักประมาณ 34 กิโลกรัม25:39 ภาษาฮีบรูว่า 1 ตะลันต์ สำหรับคันประทีปและเครื่องประกอบทั้งหมด 40จงทำสิ่งเหล่านี้ตามแบบที่เราได้สำแดงแก่เจ้าบนภูเขานั้น