ዘፀአት 23 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 23:1-33

የፍትሕና የምሕረት ሕጎች

1“የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።

2“ክፉ በማድረግ ብዙዎችን አትከተል፤ በሕግ ፊት ምስክርነት ስትሰጥ፣ ከብዙዎቹ ጋር ተባብረህ ፍትሕ አታጣምም። 3በዳኝነት ጊዜ ለድኻው አታድላ።

4“የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እርሱ መልሰው። 5የሚጠላህ ሰው አህያ፣ ጭነት ከብዶት ወድቆ ብታየው ርዳው እንጂ ትተኸው አትሂድ።

6“በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት። 7ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ትክክለኛውን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።

8“ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ አጥርተው የሚያዩትን ሰዎች ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

9“መጻተኛውን አትጨቍን፤ በግብፅ መጻተኛ ስለ ነበራችሁ፣ መጻተኛ ምን እንደሚሰማው እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።

የሰንበት ሕጎች

10“ስድስት ዓመት በዕርሻህ ላይ ዝራ፤ አዝመራንም ሰብስብ፤ 11ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱን ሳትጠቀምባትና ሳታርሳት እንዲሁ ተዋት፤ ከዚያም በወገንህ መካከል ያሉት ድኾች ከእርሷ ምግብ ያገኛሉ፤ የዱር አራዊትም ከእነርሱ የተረፈውን ይበላሉ። በወይን ቦታህና በወይራ ዛፎችህም ላይ እንዲሁ አድርግ።

12“ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ያርፉ ዘንድ በሰባተኛው ቀን ምንም አትሥራ።

13“ያልኋችሁን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ተጠንቀቁ፤ የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፤ ከአፋችሁም አይስሙ።

ሦስቱ ዐውደ ዓመታዊ በዓላት

14“በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታከብራላችሁ።

15“ያልቦካ የቂጣ በዓልን አክብር፤ እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን እርሾ የሌለውን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በአቢብ ወር በተወሰነ ቀን አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና።

“ማንም በፊቴ ባዶ እጁን አይቅረብ።

16“በማሳህ ላይ በዘራኸው እህል በኵራት የመከርን በዓል አክብር።

“በዓመቱ መጨረሻ በማሳህ ላይ ያለውን እህልህን ስትሰበስብ የመክተቻውን በዓል አክብር።

17“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር (አዶናይ ያህዌ) ፊት ይቅረብ።

18“የመሥዋዕትን ደም እርሾ ካለበት ነገር ጋር አድርገህ ለእኔ አታቅርብ።

“የበዓል መሥዋዕቴ ስብ እስከ ንጋት ድረስ አይቈይ።

19“የምድርን ምርጥ ፍሬ በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አምጣ።

“ጠቦት ፍየልን በእናቱ ወተት አትቀቅል።

የእግዚአብሔር መልአክ መንገድ ስለ መምራቱ

20“እነሆ፤ በጕዞ ላይ ሳለህ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ ልኬልሃለሁ። 21በጥንቃቄ ተከተለው፤ የሚናገረውንም ልብ ብለህ አድምጠው፤ አታምፅበት። ስሜ በእርሱ ላይ ነውና ዐመፅህን ይቅር አይልም። 22የሚናገረውን በጥንቃቄ ብታደምጥና ያልኩህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህን እቃወማለሁ። 23መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል፤ እኔም እነርሱን አጠፋቸዋለሁ። 24ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፤ ወይም አታምልካቸው፤ ወይም ልምዳቸውን አትከተል፤ እነርሱን ማፈራረስ አለብህ፤ የአምልኮ ድንጋዮቻቸውንም ሰባብር። 25አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) አምልክ፤ በረከቱም በምትበላውና በምትጠጣው ላይ ይሆናል፤ በሽታንም ከአንተ ዘንድ አርቃለሁ። 26በምድርህም የሚያስወርዳት ወይም መካን ሴት አትኖርም፤ ረዥም ዕድሜም እሰጥሃለሁ።

27“በሚያጋጥሙህ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስፈራቴን በፊትህ እልካለሁ፤ ግራም አጋባቸዋለሁ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲሸሹ አደርጋለሁ። 28ኤዊያውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን ከመንገድህ ለማስወጣት ተርብን በፊትህ እሰድዳለሁ። 29ነገር ግን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አላወጣቸውም፤ ምክንያቱም ምድሪቱ ባድማ ሆና የዱር አራዊት ይበዙባችኋል። 30ቍጥርህ ጨምሮ ምድሪቱን ለመውረስ እስክትበቃ ድረስ ጥቂት በጥቂት ከፊታችሁ አባርራቸዋለሁ።

31“ድንበርህን ከቀይ ባሕር23፥31 በዕብራይስጥ፣ ያም ሱፍ ይባላል፤ ይኸውም፣ የደንገል ባሕር ማለት ነው። እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣23፥31 የሜዲትራንያን ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ23፥31 የኤፍራጥስ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ። 32ከእነርሱም ሆነ ከአማልክቶቻቸው ጋር ኪዳን አታድርግ። 33በምድርህ ላይ እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ እኔን እንድትበድል ያደርጉሃል፤ አማልክታቸውን ማምለክ በርግጥ ወጥመድ ይሆንብሃልና።”

New International Version

Exodus 23:1-33

Laws of Justice and Mercy

1“Do not spread false reports. Do not help a guilty person by being a malicious witness.

2“Do not follow the crowd in doing wrong. When you give testimony in a lawsuit, do not pervert justice by siding with the crowd, 3and do not show favoritism to a poor person in a lawsuit.

4“If you come across your enemy’s ox or donkey wandering off, be sure to return it. 5If you see the donkey of someone who hates you fallen down under its load, do not leave it there; be sure you help them with it.

6“Do not deny justice to your poor people in their lawsuits. 7Have nothing to do with a false charge and do not put an innocent or honest person to death, for I will not acquit the guilty.

8“Do not accept a bribe, for a bribe blinds those who see and twists the words of the innocent.

9“Do not oppress a foreigner; you yourselves know how it feels to be foreigners, because you were foreigners in Egypt.

Sabbath Laws

10“For six years you are to sow your fields and harvest the crops, 11but during the seventh year let the land lie unplowed and unused. Then the poor among your people may get food from it, and the wild animals may eat what is left. Do the same with your vineyard and your olive grove.

12“Six days do your work, but on the seventh day do not work, so that your ox and your donkey may rest, and so that the slave born in your household and the foreigner living among you may be refreshed.

13“Be careful to do everything I have said to you. Do not invoke the names of other gods; do not let them be heard on your lips.

The Three Annual Festivals

14“Three times a year you are to celebrate a festival to me.

15“Celebrate the Festival of Unleavened Bread; for seven days eat bread made without yeast, as I commanded you. Do this at the appointed time in the month of Aviv, for in that month you came out of Egypt.

“No one is to appear before me empty-handed.

16“Celebrate the Festival of Harvest with the firstfruits of the crops you sow in your field.

“Celebrate the Festival of Ingathering at the end of the year, when you gather in your crops from the field.

17“Three times a year all the men are to appear before the Sovereign Lord.

18“Do not offer the blood of a sacrifice to me along with anything containing yeast.

“The fat of my festival offerings must not be kept until morning.

19“Bring the best of the firstfruits of your soil to the house of the Lord your God.

“Do not cook a young goat in its mother’s milk.

God’s Angel to Prepare the Way

20“See, I am sending an angel ahead of you to guard you along the way and to bring you to the place I have prepared. 21Pay attention to him and listen to what he says. Do not rebel against him; he will not forgive your rebellion, since my Name is in him. 22If you listen carefully to what he says and do all that I say, I will be an enemy to your enemies and will oppose those who oppose you. 23My angel will go ahead of you and bring you into the land of the Amorites, Hittites, Perizzites, Canaanites, Hivites and Jebusites, and I will wipe them out. 24Do not bow down before their gods or worship them or follow their practices. You must demolish them and break their sacred stones to pieces. 25Worship the Lord your God, and his blessing will be on your food and water. I will take away sickness from among you, 26and none will miscarry or be barren in your land. I will give you a full life span.

27“I will send my terror ahead of you and throw into confusion every nation you encounter. I will make all your enemies turn their backs and run. 28I will send the hornet ahead of you to drive the Hivites, Canaanites and Hittites out of your way. 29But I will not drive them out in a single year, because the land would become desolate and the wild animals too numerous for you. 30Little by little I will drive them out before you, until you have increased enough to take possession of the land.

31“I will establish your borders from the Red Sea23:31 Or the Sea of Reeds to the Mediterranean Sea,23:31 Hebrew to the Sea of the Philistines and from the desert to the Euphrates River. I will give into your hands the people who live in the land, and you will drive them out before you. 32Do not make a covenant with them or with their gods. 33Do not let them live in your land or they will cause you to sin against me, because the worship of their gods will certainly be a snare to you.”