ዘዳግም 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 9:1-29

የሕዝቡ አለመታዘዝ

1እስራኤል ሆይ፤ ስማ፤ ሰማይ ጠቀስ ቅጥር ያላቸው ታላላቅ ከተሞች ያሏቸውን፣ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ አስለቅቀህ ለመግባት ዮርዳኖስን አሁን ትሻገራለህ። 2ዔናቃውያን ብርቱና ቁመተ ረጃጅም ሕዝቦች ናቸው፤ ስለ እነርሱ ታውቃለህ፤ “ዔናቃውያንን ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?” ሲባልም ሰምተሃል። 3ይሁን እንጂ እንደሚባላ እሳት ከፊትህ ቀድሞ የሚሻገረው አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሆኑን ዛሬ ርግጠኛ ሁን፤ እነርሱን ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ድል ያደርጋቸዋል፤ አንተም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት ታስወጣቸዋለህ፤ በፍጥነትም ትደመስሳቸዋለህ። 4አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እነርሱን ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፣ “ይህችን ምድር እንድወርስ እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደዚህ ያመጣኝ፣ ከጽድቄ የተነሣ ነው” ብለህ በልብህ አታስብ። በዚህ አይደለም፤ እነዚህን አሕዛብ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከፊትህ የሚያሳድዳቸው በክፋታቸው ምክንያት ነው። 5ምድራቸውን ገብተህ የምትወርሳት ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሣ ሳይሆን፣ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እነዚህን አሕዛብ ከክፋታቸው የተነሣ ከፊትህ ስለሚያባርራቸው ነው። 6ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሣ አለመሆኑን አስተውል፤ አንተ ዐንገተ ደንዳና ነህና።

የወርቁ ጥጃ

7አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በምድረ በዳ እንዴት እንዳስቈጣኸው አስታውስ፤ ከቶም አትርሳ። ከግብፅ ከወጣህበት ዕለት አንሥቶ እዚህ ቦታ እስከ ደረስህበት ጊዜ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ እንዳመፅህ ነህ። 8በኮሬብ እግዚአብሔርን (ያህዌ) ለቍጣ አነሣሣችሁት፤ እርሱም እናንተን ሊያጠፋችሁ እጅግ ተቈጣ። 9እኔም የድንጋይ ጽላቶቹን፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእናንተ ጋር የገባውን የኪዳን ጽላቶች ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ፣ እህል ሳልበላ፣ ውሃም ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ፤ 10በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁበት ዕለት እግዚአብሔር (ያህዌ) ከተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ትእዛዞች ሁሉ በእነርሱ ላይ ነበሩባቸው።

11አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከተፈጸመ በኋላ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ማለትም የኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ። 12ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ “ተነሣ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋልና ፈጥነህ ከዚህ ውረድ፤ እኔ ካዘዝኋቸው ፈጥነው ፈቀቅ ብለዋል፤ ቀልጦ የተሠራ ጣዖትም ለራሳቸው አበጅተዋል” ብሎ ነገረኝ።

13ደግሞም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በርግጥ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው፣ 14አጠፋቸውና ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ይልቅ ብርቱና ብዙ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

15ስለዚህ ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ ሳለ፣ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች በሁለቱም እጆቼ እንደ ያዝሁ9፥15 ወይም፣ ሁለቱም የቃል ኪዳን ጽላቶች ከእኔ ጋር ነበሩ፤ አንዱም በአንዱ፣ ሌላውም በሌላው እጄ ነበር ተብሎ መተርጐም ይችላል። ከተራራው ተመልሼ ወረድሁ። 16በርግጥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ላይ ኀጢአት ሠርታችሁ እንደ ነበር ተመለከትሁ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስልም ለራሳችሁ አበጃችሁ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን ካዘዛችሁ መንገድ በፍጥነት ወጥታችሁ ነበር። 17ስለዚህ ሁለቱን ጽላቶች ወስጄ ከእጆቼ አሽቀንጥሬ በፊታችሁ ሰባበርኋቸው።

18ከዚያም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ክፉ ነገርን በመፈጸም ለቍጣ እንዲነሣሣ የሚያደርገውን ኀጢአት ሁሉ ስለ ሠራችሁ፣ እህል ውሃ ሳልቀምስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደ ገና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በግምባሬ ተደፋሁ። 19እናንተን ሊያጠፋችሁ ክፉኛ ተቈጥቶ ነበርና፣ እኔም የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቍጣና መዓት ፈራሁ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን እንደ ገና ሰማኝ። 20እግዚአብሔር (ያህዌ) አሮንን ሊያጠፋው ክፉኛ ተቈጥቶ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ለአሮንም ጸለይሁ። 21ደግሞም ያን የኀጢአት ሥራችሁን፣ አበጅታችሁት የነበረውን ጥጃ ወስጄ በእሳት አቃጠልሁት፤ ከዚያም ሰባብሬ እንደ ትቢያ ዱቄት እስኪሆን ድረስ ፈጭቼ ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንሁት።

22በተቤራም፣ በማሳህና በቂብሮት ሐታአዋ እግዚአብሔርን (ያህዌ) አስቈጣችሁት።

23እግዚአብሔር (ያህዌ) ከቃዴስ በርኔ ባስወጣችሁ ጊዜ፣ “ውጡ፤ የሰጠኋችሁንም ምድር ርስት አድርጋችሁ ውረሷት” አላችሁ። እናንተ ግን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፤ እርሱን አልታመናችሁበትም፤ አልታዘዛችሁትምም። 24እኔ እናንተን ካወቅኋችሁ ጊዜ ጀምሮ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ እንዳመፃችሁ ናችሁ።

25እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን እንደሚያጠፋችሁ ተናግሮ ስለ ነበር፣ በእነዚያ አርባ ቀናትና አርባ ሌሊቶች በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፋሁ፤ 26እንዲህም በማለት ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጸለይሁ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ (አዶናይ ያህዌ) በታላቅ ኀይልህ የተቤዠኸውንና በኀያል ክንድህ ከግብፅ ያወጣኸውን፣ ያንተ ርስት የሆነውን ሕዝብህን አታጥፋ። 27ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ዐስብ፤ የዚህን ሕዝብ ልበ ደንዳናነት፣ ክፋትና ኀጢአት አትመልከት። 28አለዚያ እኛን ካመጣህበት ምድር ያሉ ሰዎች ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያገባቸው ስላልቻለና ስለ ጠላቸው፣ በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው’ ይላሉ። 29ነገር ግን እነርሱ በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

申命記 9:1-29

以色列人的悖逆

1以色列人啊,你們要聽!今天你們要過約旦河,去趕出那些比你們強大的民族。他們住在城牆高聳入雲的大城裡, 2是長得高大威猛的亞衲人。你們瞭解他們,也聽人說過,『誰能抵擋亞衲人呢?』 3但今天你們要知道,你們的上帝耶和華要走在你們前面,像烈火一樣吞噬他們。祂要制伏他們,使你們迅速趕走他們,毀滅他們,正如祂對你們的應許。

4「你們的上帝耶和華趕走他們以後,你們不要以為耶和華帶領你們佔領那片土地是因為你們公義,其實是因為那裡的民族邪惡,耶和華才將他們從你們面前趕走。 5你們能佔領他們的土地並非因為你們公義、行為正直。你們的上帝耶和華從你們面前趕走那些民族,是因為他們邪惡,也是為了實現祂給你們祖先亞伯拉罕以撒雅各的誓言。 6你們要知道,耶和華賜給你們那佳美之地不是因為你們有好品德。其實你們是頑固不化的人。

7「要牢記你們在曠野怎樣觸怒你們的上帝耶和華。從你們離開埃及那天到現在,你們屢屢背叛耶和華。 8何烈山,你們觸怒了耶和華,以致祂要毀滅你們。 9那時,我上山去接受耶和華與你們立約的石版,在山上待了四十晝夜,不吃也不喝。 10耶和華把兩塊立約的石版交給我,上面刻著那天你們聚會時祂在山上的火焰中對你們說的話,是祂用手指刻上去的。 11四十晝夜後,耶和華把那兩塊刻著約的石版交給我, 12對我說,『快下山吧,你從埃及領出來的百姓已經敗壞了。他們這麼快就偏離了我吩咐他們走的道,為自己鑄造了神像。』

13「耶和華又對我說,『我已看出,這是頑固不化的百姓。 14不要攔我,我要毀滅他們,從世上抹去他們的名字。我要使你的子孫成為一個比他們更強大的民族。』 15我雙手拿著那兩塊石版,轉身從烈火熊熊的山上下來, 16看見你們為自己鑄造了牛犢像,得罪了你們的上帝耶和華,這麼快就偏離了耶和華吩咐你們走的道, 17就當著你們的面摔碎了那兩塊石版。

18「我又俯伏在耶和華面前,四十晝夜不吃不喝,因為你們犯了大罪,做耶和華憎惡的事,惹祂發怒。 19耶和華向你們發烈怒,要毀滅你們,我非常懼怕。但耶和華再次垂聽了我的祈求。 20耶和華對亞倫非常憤怒,以致要殺掉他,於是我也為他祈求。 21我焚燒了你們鑄造的罪惡之物——牛犢像,把它磨成細粉,撒在從山上流下來的溪水中。

22「你們在他備拉瑪撒基博羅·哈他瓦三番四次地觸怒耶和華。 23你們的上帝耶和華吩咐你們離開加低斯·巴尼亞,去佔領祂賜給你們的土地,你們卻背叛祂,不信靠祂,也不聽從祂。 24自從我認識你們以來,你們就不斷地背叛耶和華。

25「因為耶和華說要毀滅你們,我就俯伏在耶和華面前四十晝夜, 26向祂祈求說,『主耶和華啊,求你不要毀滅你的子民!他們是你的產業,是你用大能的手從埃及拯救出來的。 27求你看在你僕人亞伯拉罕以撒雅各的份上,不要計較這個民族的頑固和罪惡, 28免得你帶領我們離開之地的人說,你不能把他們領到你應許給他們的地方,你憎惡他們,所以把他們帶到曠野殺了。 29他們畢竟是你的子民,你的產業,是你伸出大能的臂膀從埃及帶出來的。』