ዘዳግም 7 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 7:1-26

አሕዛብን ማስወጣት

1አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህና ብዙዎችን ከአንተ የሚበልጡ ታላላቆችና ብርቱዎች የሆኑትን ሰባቱን አሕዛብ፦ ኬጢያውያንን፤ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ በሚያስወጣቸው ጊዜ፣ 2አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጅህ አሳልፎ በሰጠህና አንተም ድል ባደረግሃቸው ጊዜ፣ ሁሉንም ፈጽመህ ደምስሳቸው7፥2 በዚህና በቍጥር 26 ላይ የዕብራይስጡ ቃል አንድን ነገር ወይም አንድን ሰው ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን የሚያሳይ ነው።፤ ከእነርሱ ጋር አትዋዋል፤ አትራራላቸውም። 3ከእነርሱ ጋር ጋብቻ አታድርግ፤ ሴት ልጆችህን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጥ፤ ወይም ለወንድ ልጆችህ ሴት ልጆቻቸውን አታምጣ፤ 4ምክንያቱም እኔን ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ ስለሚያደርጉና ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ በላይህ ነዶ፣ ፈጥኖ ስለሚያጠፋህ ነው። 5እንግዲህ በእነርሱ ላይ የምታደርጉት ይህ ነው፤ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን7፥5 እዚህ ላይና በዚሁ መጽሐፍ በሌላ ስፍራ አሼራ የምትባለውን ጣዖት ምስል የሚያመለክት ነው። ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን ቍረጡ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ። 6አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቅዱስ ሕዝብ ስለ ሆንህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የራሱ ሕዝብ፣ ርስትም እንድትሆንለት በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ መረጠህ።

7እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከሌሎች ሕዝቦች በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም፤ ቍጥራችሁማ ከሕዝቦች ሁሉ እጅግ አነስተኛ ነበር። 8ነገር ግን እናንተን በብርቱ እጅ ያወጣችሁ፣ ከባርነት ምድርና ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን መዳፍ የተቤዣችሁ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን ስለ ወደዳችሁና ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ ነው። 9ስለዚህም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አምላክ (ኤሎሂም) መሆኑን ዕወቅ፤ እርሱ ለሚወድዱትና ትእዛዞቹን ለሚጠብቁት የፍቅሩን ኪዳን እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ ታማኝ አምላክ (ኤሎሂም) ነው። 10ነገር ግን፣ የሚጠሉትን ዐይናቸው እያየ ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ዐይናቸው እያየ ለመበቀል አይዘገይም። 11ስለዚህ በዛሬው ቀን የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ለመከተል ጥንቃቄ አድርግ።

12እነዚህን ሕግጋት ብታዳምጥና በጥንቃቄ ብትጠብቃቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ከአንተ ጋር የገባውን የፍቅር ኪዳኑን ይጠብቃል። 13ይወድሃል፤ ይባርክሃል፤ ያበዛሃልም። ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የማሕፀንህን ፍሬ፣ የምድርህን ሰብል፣ እህልህን፣ አዲሱን ወይንና ዘይት፤ የከብት መንጋህን ጥጆች፣ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገሎች ይባርካል። 14ከሕዝቦች ሁሉ የበለጠ አንተ ትባረካለህ፤ ከአንተ ወይም ከከብቶችህ መካከል የማይወልድ ወንድ ወይም ሴት አይኖርም። 15እግዚአብሔር (ያህዌ) ከማናቸውም በሽታ ነጻ ያደርግሃል፤ በግብፅ የምታውቃቸውን እነዚያን አሠቃቂ በሽታዎች በሚጠሉህ ሁሉ ላይ እንጂ በአንተ ላይ አያመጣብህም። 16አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ማጥፋት አለብህ፤ አትዘንላቸው፤ ወጥመድ ስለሚሆኑብህም አማልክታቸውን አታምልክ።

17“እነዚህ አሕዛብ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ስለ ሆኑ፣ እንዴት አድርገን እናስወጣቸዋለን?” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።

18ነገር ግን አትፍራቸው፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ላይ ያደረገውን በሚገባ አስታውስ። 19ታላላቅ ፈተናዎችን፣ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አንተን ያወጣበትን ብርቱ እጅና የተዘረጋች ክንድ በገዛ ዐይንህ አይተሃል። አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አሁን በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያንኑ ያደርጋል። 20ይልቁንም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሕይወት ተርፈው፣ ከአንተ የተደበቁት እንኳ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ተርብ ይሰድድባቸዋል። 21በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ (ኤሎሂም) ስለሆነ አያስደንግጡህ። 22አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊቱ ቍጥር በአካባቢህ እንዳይበራከት ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይፈቀድልህም፤ 23አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ግን እስኪጠፉ ድረስ ከባድ ትርምስ ፈጥሮባቸው በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል። 24ነገሥታታቸውን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ። እስክትደመስሳቸው ድረስ አንተን መቋቋም የሚችል አንድም ሰው የለም። 25የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ዘንድ አስጸያፊ ስለሆነ ያሰናክልሃል። 26አስጸያፊ ነገርን ወደ ቤትህ ወይም ወደ ራስህ አታምጣ፤ አለዚያ አንተም እንደ እርሱ ለጥፋት ትዳረጋለህ፤ ፈጽመህ ጥላው፤ ተጸየፈውም፤ ለጥፋት የተለየ ነውና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 7:1-26

做上帝的子民

1“你们的上帝耶和华带领你们进入将要占领的土地时,会为你们赶走人、革迦撒人、亚摩利人、迦南人、比利洗人、希未人和耶布斯人这七个比你们强大的民族。 2当你们的上帝耶和华把他们交在你们手里、使你们打败他们后,你们必须彻底毁灭他们。不可与他们立约,不可怜悯他们。 3不可与他们通婚,不可让你们的儿女与他们的儿女通婚, 4因为他们会让你们的儿女离弃耶和华去拜其他神明,以致耶和华向你们发怒,迅速毁灭你们。 5你们要拆毁他们的祭坛,打碎他们的神柱,砍下他们的亚舍拉神像,焚烧他们的偶像。 6因为你们属于你们的上帝耶和华,是圣洁的民族,祂从天下万族中拣选了你们做祂的子民——祂宝贵的产业。

7“耶和华喜爱你们、拣选你们,不是因为你们的人口比别的民族多——其实你们在万族中是最小的—— 8而是因为祂爱你们,遵守祂向你们祖先所起的誓。因此,祂用大能的手把你们从受奴役的地方领出来,从埃及王法老手中救赎了你们。 9所以你们要知道,你们的上帝耶和华是真神,是信实的真神,祂向爱祂、遵守祂诫命的人守约、施慈爱直到千代。 10但祂必毫不迟延地报应、毁灭那些恨祂的人。 11所以,你们要遵行我今天吩咐你们的诫命、律例和典章。

遵守诫命必蒙福

12“如果你们听从并谨遵这一切,你们的上帝耶和华就会信守祂给你们祖先的誓约,以慈爱待你们。 13祂会爱你们,赐福给你们,使你们在祂向你们祖先起誓要赐给你们的土地上子孙昌盛,牛羊成群,收获丰富的谷物、新酒和油。 14天下万族之中,你们是最蒙福的,你们的男人、女人和牲畜没有不能生育的。 15耶和华要使你们免患疾病,免遭你们在埃及所见的恶疾,祂要把那些恶疾降在一切憎恶你们的人身上。 16你们必须灭绝你们的上帝耶和华交在你们手里的各族,不可怜悯他们,不可拜他们的神明,因为那样会使你们陷入网罗。

17“也许你们心里会说,‘这些民族都比我们强大,我们怎能赶走他们呢?’ 18不要怕他们,要牢记你们的上帝耶和华曾如何对付埃及和法老, 19你们亲眼目睹祂如何降下大灾难、行神迹奇事、伸出臂膀和大能的手领你们离开埃及,祂也要这样对付你们所惧怕的各族。 20你们的上帝耶和华还要派黄蜂去攻击他们,直到躲藏起来的残存者也全部灭亡。 21不要惧怕他们,因为你们的上帝耶和华住在你们当中,祂是伟大而可畏的上帝。 22你们的上帝耶和华将在你们前面渐渐地赶走那些民族,你们不可急速地灭尽他们,否则你们周围的野兽会大增,危害你们。 23你们的上帝耶和华要将他们交给你们,使他们惊恐万状,直到被灭绝。 24祂要将他们的王交在你们手中,无人能抵挡你们,你们要毁灭他们,使他们的名字从世上绝迹。 25你们要烧毁他们的神像,不可贪图神像上的金银,不可将那些金银据为己有,免得你们因此陷入网罗;因为那是你们的上帝耶和华所憎恶的。 26不可把可憎之物带到家里,否则你们会像它们一样被毁灭。你们要极其憎恶、厌弃它们,因为它们是当毁灭之物。