ዘዳግም 33 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 33:1-29

ሙሴ የእስራኤልን ነገዶች ባረከ

33፥1-29 ተጓ ምብ – ዘፍ 49፥1-28

1የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰጠው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው፤ 2እንዲህም አለ፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሲና መጣ፤

በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤

ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤

ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር33፥2 ወይም በአእላፋት ቅዱሳኑ። መጣ፤

በስተ ቀኙ የሚነድድ እሳት ነበር።

3በርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤

ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው።

ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤

ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤

4ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፣

የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።

5የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፣

በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣

እርሱ በይሹሩን33፥5 በዚህ ስፍራና በቍጥር 26 ላይ ይሽሩን ማለት፣ ቅን ወይም ትክክለኛ ማለት ሲሆን ይኸውም እስራኤልን የሚያሳይ ነው። ላይ ንጉሥ ነበር።

6“ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤

የወገኖቹ ቍጥርም አይጕደልበት።”

7ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤

ወደ ወገኖቹም አምጣው።

በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤

አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!”

8ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦

“ቱሚምህና ኡሪምህ፣

ለምትወድደው ሰው ይሁን፤

ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤

በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።

9ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣

‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ።

ወንድሞቹን አልለያቸውም፤

ልጆቹንም አላወቃቸውም።

ለቃልህ ግን ጥንቃቄ አደረገ፤

ኪዳንህንም ጠበቀ።

10ሥርዐትህን ለያዕቆብ፣

ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል።

ዕጣን በፊትህ፣

የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በመሠዊያህ ላይ ያቀርባል።

11እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ኀይሉን ሁሉ ባርክለት፤

በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤

በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቍረጠው፤

ጠላቶቹንም እንዳያንሠራሩ አድርገህ ምታቸው።”

12ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦

የእግዚአብሔር (ያህዌ) ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤

ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤

እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚወድደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”

13ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦

እግዚአብሔር (ያህዌ) ምድሩን ይባርክ፤

ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣

ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ

14ፀሓይ በምታስገኘው ምርጥ ፍሬ፣

ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም

15ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፣

በዘላለማዊ ኰረብቶች ፍሬያማነት፤

16ምድር በምታስገኘው ምርጥ ስጦታና በሙላቷ፣

በሚቃጠለው ቍጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ ሞገስ።

እነዚህ ሁሉ በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፣

በዮሴፍ ዐናት ላይ ይውረዱ።

17በግርማው እንደ በኵር ኰርማ ነው፤

ቀንዶቹም የጐሽ ቀንዶች ናቸው።

በእነርሱም ሕዝቦችን፣

በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤

እነርሱም የኤፍሬም ዐሥር ሺዎቹ ናቸው፤

የምናሴም ሺዎቹ እንደዚሁ ናቸው።”

18ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ፦

“ዛብሎን ሆይ፤ ወደ ውጭ በመውጣትህ፣

አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ፤

19አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤

በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ።

በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣

በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።”

20ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦

“የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተመሰገነ ነው!

ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፣

ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።

21ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤

የአለቃም ድርሻ ለእርሱ ተጠብቆለታል።

የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣

የእግዚአብሔርን (ያህዌ) የቅን ፈቃድና፣

በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።”

22ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦

“ዳን ከባሳን ዘልሎ የሚወጣ፣

የአንበሳ ደቦል ነው።”

23ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦

“ንፍታሌም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ሞገስ ረክቷል፤

በበረከቱም ተሞልቷል፤

ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።”

24ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦

“አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤

በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤

እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።

25የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሆናል፤

ኀይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።

26“አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣

በደመናትም ላይ በግርማው እንደሚገሠግሥ፣

እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።

27ዘላለማዊ አምላክ (ኤሎሂም) መኖርያህ ነው፤

የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤

‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣

ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።

28ስለዚህ እስራኤል ብቻውን በሰላም ይኖራል፤

የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣

እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣

የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።

29እስራኤል ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤

እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዳነው ሕዝብ፣

እንደ አንተ ያለ ማን አለ?

እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው።

ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤

አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን

መረማመጃ ታደርጋለህ።”

Thai New Contemporary Bible

เฉลยธรรมบัญญัติ 33:1-29

โมเสสอวยพรเผ่าต่างๆ

(ปฐก.49:1-28)

1ก่อนสิ้นชีวิต โมเสสคนของพระเจ้าได้อวยพรประชากรอิสราเอล 2เขากล่าวว่า

องค์พระผู้เป็นเจ้าเสด็จจากซีนาย

ทรงฉายแสงอรุณเหนือพวกเขาจากเสอีร์

ทรงเปล่งรังสีจากภูเขาปาราน

พระองค์เสด็จมากับ33:2 หรือจากผู้บริสุทธิ์นับหมื่นแสน

จากทิศใต้ จากลาดเขา33:2 ในภาษาฮีบรูวลีนี้มีความหมายไม่ชัดเจนของพระองค์

3แน่นอน พระองค์ทรงรักเหล่าประชากร

วิสุทธิชนทั้งปวงอยู่ในพระหัตถ์

พวกเขากราบลงแทบพระบาท

และรับการสั่งสอนจากพระองค์

4คือบทบัญญัติที่โมเสสให้แก่เราไว้

เป็นกรรมสิทธิ์ของชุมชนยาโคบ

5พระองค์ทรงเป็นกษัตริย์เหนือเยชูรุน33:5 แปลว่า ผู้เที่ยงธรรม คือ อิสราเอล เช่นเดียวกับข้อ 26

เมื่อบรรดาผู้นำมาชุมนุมกัน

ร่วมกับเผ่าต่างๆ ของอิสราเอล

6“ขอให้รูเบนดำรงอยู่เป็นอมตะ

อย่าให้33:6 หรือแต่ให้ คนของเขามีน้อย”

7และเขากล่าวถึงยูดาห์ว่า

“ข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้าขอทรงฟังเสียงร่ำร้องของยูดาห์

ประสานเขาเข้ากับชนชาติของเขา

เขาต่อสู้ฟันฝ่าด้วยมือของเขาเอง

ขอทรงช่วยยูดาห์ต่อกรกับศัตรู!”

8เขากล่าวถึงเผ่าเลวีว่า

“อูริมและทูมมิมของพระองค์

อยู่กับผู้ที่พระองค์ทรงโปรดปราน

พระองค์ทรงทดสอบเขาที่มัสสาห์

พระองค์ทรงต่อสู้กับเขาที่ห้วงน้ำเมรีบาห์

9เขากล่าวถึงบิดามารดาของตนว่า

‘ข้าพเจ้าไม่เห็นแก่หน้าพวกเขา’

เขาไม่เห็นแก่พี่น้องของเขา

ไม่เห็นแก่บุตรของเขา

แต่เขาพิทักษ์รักษาพระดำรัสของพระองค์

และปกป้องพันธสัญญาของพระองค์

10เขาจะสอนพระโอวาทของพระองค์แก่ยาโคบ

และสอนบทบัญญัติของพระองค์แก่อิสราเอล

เขาถวายเครื่องหอมต่อหน้าพระองค์

และถวายเครื่องเผาบูชาทั้งสิ้นบนแท่นของพระองค์

11ข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้าขอทรงอวยพรความชำนาญทั้งสิ้นของเขา

และพอพระทัยผลงานที่เขาทำ

ขอทรงบดขยี้ผู้ที่ต่อสู้เขา

ขอทรงฟาดฟันศัตรูของเขาจนลุกขึ้นไม่ได้อีกต่อไป”

12เขากล่าวถึงเผ่าเบนยามินว่า

“ขอให้ผู้ที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงรักพักพิงในพระองค์อย่างมั่นคงปลอดภัย

เพราะพระองค์ทรงปกป้องเขาวันยังค่ำ

และให้ผู้ที่พระองค์ทรงรักพักอยู่แนบพระทรวงของพระองค์”

13เขากล่าวถึงเผ่าโยเซฟว่า

“ขอองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงอวยพรดินแดนของเขา

ด้วยน้ำค้างล้ำเลิศจากฟ้าสวรรค์เบื้องบน

และด้วยห้วงน้ำลึกเบื้องล่าง

14ด้วยผลผลิตยอดเยี่ยมจากดวงตะวัน

และด้วยผลผลิตที่ดีที่สุดตามฤดูกาล33:14 หรือและด้วยผลผลิตที่ดีที่สุดตามแต่ละเดือน

15ด้วยของขวัญเลอเลิศจากภูเขาดึกดำบรรพ์

ด้วยความสมบูรณ์พูนผลจากภูเขาอันถาวรนิรันดร์

16ด้วยของขวัญล้ำค่าจากผืนแผ่นดิน และความอุดมสมบูรณ์จากพื้นพสุธา

และด้วยความโปรดปรานจากพระองค์ผู้ประทับในพุ่มไม้ที่ลุกเป็นไฟ

ขอให้พรทั้งปวงนี้มาเหนือโยเซฟ

เหนือเจ้านายในหมู่พี่น้อง33:16 หรือเหนือผู้พลัดพรากจากพี่น้อง

17ผู้ทรงไว้ซึ่งศักดาดุจลูกวัวหนุ่มหัวปี

เขาสัตว์ของเขาคือเขาของวัวป่า

เขาจะขวิดประชาชาติทั้งหลายด้วยเขาสัตว์เหล่านั้น

แม้ประชาชาติที่อยู่สุดปลายแผ่นดินโลก

นี่แหละคือชนเอฟราอิมนับหมื่น

และชนมนัสเสห์นับพัน”

18เขากล่าวถึงเผ่าเศบูลุนว่า

“จงร่าเริงยินดีเถิด เศบูลุนเอ๋ย เมื่อท่านออกไป

และท่านอิสสาคาร์เอ๋ย จงร่าเริงยินดีในเต็นท์ของท่าน

19พวกเขาจะเรียกประชากรมาชุมนุมที่ภูเขา

และถวายเครื่องบูชาแห่งความชอบธรรมที่นั่น

เขาจะเฉลิมฉลองความอุดมสมบูรณ์แห่งท้องทะเล

เฉลิมฉลองทรัพย์สมบัติที่ซ่อนไว้ในหาดทราย”

20เขากล่าวถึงเผ่ากาดว่า

“ขอถวายสรรเสริญแด่พระองค์ผู้ทรงขยายอาณาจักรของกาด!

กาดมีชีวิตอยู่เยี่ยงราชสีห์

ซึ่งฉีกทึ้งแขนหรือศีรษะ

21เขาเลือกดินแดนดีเยี่ยมที่สุดไว้เป็นของตนเอง

ส่วนที่เป็นของผู้นำถูกสงวนไว้สำหรับเขา

เมื่อบรรดาหัวหน้าของประชาชนมาชุมนุมกัน

เขาทำให้ลุล่วงตามพระประสงค์อันชอบธรรมขององค์พระผู้เป็นเจ้า

และตามพระวินิจฉัยเกี่ยวกับอิสราเอล”

22เขากล่าวถึงเผ่าดานว่า

“ดานเหมือนลูกสิงห์

โลดแล่นออกมาจากบาชาน”

23เขากล่าวถึงเผ่านัฟทาลีว่า

“นัฟทาลีอิ่มเอิบด้วยความโปรดปรานจากองค์พระผู้เป็นเจ้า

และเต็มเปี่ยมด้วยพระพรของพระองค์

เขาจะครอบครองไปทางใต้ถึงทะเลสาบ”

24เขากล่าวถึงเผ่าอาเชอร์ว่า

“อาเชอร์เป็นลูกที่ได้รับพรมากที่สุด

ขอให้เขาเป็นที่ชื่นชอบของพี่ๆ น้องๆ

และให้เขาล้างเท้าด้วยน้ำมัน

25ดาลประตูของท่านจะเป็นเหล็กและทองสัมฤทธิ์

และพลังวังชาของท่านจะอยู่คู่คืนวันของท่าน

26“ไม่มีผู้ใดเสมอเหมือนพระเจ้าแห่งเยชูรุน

ผู้ประทับอยู่บนฟ้าสวรรค์เพื่อช่วยท่าน

ผู้ประทับเหนือเมฆด้วยพระบารมีของพระองค์

27พระเจ้าองค์นิรันดร์เป็นที่ลี้ภัยของท่าน

และเบื้องล่างคืออ้อมแขนอันนิรันดร์

พระองค์จะทรงขับไล่เหล่าศัตรูออกไปให้พ้นหน้าท่าน

ตรัสว่า ‘จงทำลายพวกเขาเสีย!’

28ฉะนั้นอิสราเอลจะอาศัยอยู่โดยสวัสดิภาพ

ธารน้ำพุของยาโคบมั่นคง

ในดินแดนแห่งข้าวและเหล้าองุ่นใหม่

ที่ซึ่งฟ้าสวรรค์หยาดรินน้ำค้างลงมา

29อิสราเอลเอ๋ย! พระพรนี้มีแก่ท่าน

ใครเล่าเสมอเหมือนท่าน?

ชนชาติซึ่งองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงช่วยให้รอด

พระองค์ทรงเป็นโล่และเป็นผู้ช่วยท่าน

และทรงเป็นดาบอันรุ่งโรจน์ของท่าน

ศัตรูของท่านจะก้มหัวให้ท่าน

และท่านจะย่ำบนที่สูง33:29 หรือจะย่ำบนร่างของเขาของเขา”