ዘዳግም 29 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 29:1-29

የቃል ኪዳኑ መታደስ

1እግዚአብሔር (ያህዌ) በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።

2ሙሴ እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) በግብፅ፣ በፈርዖን፣ በሹማምቱ ሁሉና በመላ አገሩ ላይ ያደረገውን ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋል። 3እነዚያን ከባድ ፈተናዎች፣ ታምራዊ ምልክቶችና ታላላቅ ድንቆች በገዛ ዐይኖቻችሁ አይታችኋል። 4ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያስተውል አእምሮ ወይም የሚያይ ዐይን ወይም የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም። 5በምድረ በዳ በመራኋችሁ በእነዚያ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብሳችሁ አላረጀም፤ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም። 6ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ ነው።

7ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፣ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። 8ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን።

9እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ፣ የዚህን ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ። 10እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፣ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ቆማችኋል፤ 11ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ዕንጨትህን እየፈለጡ፣ ውሃህንም እየቀዱ በሰፈርህ የሚኖሩ መጻተኞችም አብረውህ ቆመዋል። 12እዚህ የቆምኸው እግዚአብሔር (ያህዌ) ዛሬ ከአንተ ጋር ወደሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ጋር ትገባ ዘንድ፣ 13ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ (ኤሎሂም) ይሆን ዘንድ፣ አንተም ሕዝቡ መሆንህን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው። 14እኔም ይህን የመሐላ ኪዳን የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም፤ 15አብራችሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋር ነው።

16በግብፅ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 17በመካከላቸውም አስጸያፊ ምስሎቻቸውንና የዕንጨትና የድንጋይ፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል። 18የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ጐሣም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አለመገኘቱን አረጋግጡ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ።

19እንዲህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፣ በልቡ ራሱን በመባረክ፣ “እንደ ልቤ ሐሳብ ብኖርም እንኳ ሰላም አለኝ” ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል29፥19 ወይም፣ ለመርካት ስካርን ይጨምራል20እግዚአብሔር (ያህዌ) ለዚያ ሰው ፈጽሞ ይቅርታ አያደርግለትም፤ ቍጣውና ቅናቱ በእርሱ ላይ ይነድድበታል። በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። 21በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።

22የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር (ያህዌ) ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ። 23ምድሪቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች። አንዳች ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አያቈጠቍጥባትም፤ የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የሚደርስባት ውድመት እግዚአብሔር (ያህዌ) በታላቅ ቍጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፣ እንደ አዳማና ሲባዮ ጥፋት ይሆናል። 24አሕዛብም ሁሉ፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚህች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድድ ቍጣስ ለምን መጣባት?” ብለው ይጠይቃሉ።

25መልሱም፣ “የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው። 26ወጥተውም የማያውቋቸውን፣ እርሱም ያላዘዛቸውን ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም። 27ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣባት ድረስ፣ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ በዚህች ምድር ላይ ነደደ። 28በአስፈሪ ቍጣና በታላቅ መዓት እግዚአብሔር (ያህዌ) ከምድራቸው ነቀላቸው፤ አሁን እንደ ሆነውም ወደ ሌላ ምድር ጣላቸው” የሚል ይሆናል።

29ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንከተል ዘንድ ለዘላለም የእኛና የልጆቻችን ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 29:1-29

在摩押立约

1耶和华除了与以色列人在何烈山立约外,还在摩押吩咐摩西以色列人立以下的约。

2摩西召来所有以色列人,对他们说:“你们曾亲眼见过耶和华在埃及怎样对付法老及其臣仆和国民, 3怎样降下巨大的灾难,行伟大的神迹奇事。 4但耶和华至今还没有赐给你们能明白的心、能看见的眼、能听清的耳。 5四十年来,我领你们走过旷野,你们身上的衣服没有穿破,脚上的鞋子没有穿坏; 6你们没有吃饼,也没有喝淡酒和烈酒。这是为了让你们知道耶和华是你们的上帝。 7我们来到这里的时候,希实本西宏巴珊都来攻击我们,我们击败了他们, 8并将占领的土地分给吕便支派、迦得支派和玛拿西半个支派作产业。 9所以,你们要谨遵这约上的话,以便你们可以凡事顺利。

10“今天,你们全都站在你们的上帝耶和华面前,包括你们的族长、长老、官员、所有以色列男子、 11你们的孩子、妻子和寄居在你们中间为你们砍柴挑水的外族人, 12为要接受你们的上帝耶和华与你们立的誓约。 13这样,祂今天将宣告你们是祂的子民、祂是你们的上帝,正如祂对你们的应许和对你们祖先亚伯拉罕以撒雅各的誓言。 14耶和华的这誓约不仅是与你们立的, 15也是与今天一同站在我们的上帝耶和华面前的人,以及今天不在这里的人29:15 今天不在这里的人”或译“我们将来的子孙”。立的。

16“你们知道我们如何在埃及生活,也知道我们如何穿越列国来到这里。 17你们也见过他们用木、石、金、银造的可憎神像。 18你们中间,不论男人或女人,家族或支派,切不可有人背弃我们的上帝耶和华,去祭拜列国的神明,免得你们中间有残根长出苦毒的果实, 19免得有人听了这誓言后,心存侥幸地说,‘即使我一意孤行,连累他人,也必平安无事。’ 20耶和华绝不会赦免这样的人,祂必向这样的人发烈怒,使记在这书上的一切咒诅临到他身上,从世上抹去他的名字。 21耶和华必把他从以色列各支派中隔离出来,使他按律法书上约中的一切咒诅受惩罚。

22“你们的子孙后代和从远方来的外族人,必看见耶和华降在这地方的灾祸和疾病。 23遍地将是硫磺和盐,无法耕种,寸草不生,如同耶和华盛怒之下毁灭的所多玛蛾摩拉押玛洗扁24万国必问,‘耶和华为什么要这样对待这地方?祂为什么大发烈怒?’ 25必有人回答说,‘因为这地方的人背弃了他们祖先的上帝耶和华领他们出埃及时与他们所立的约, 26去供奉、祭拜他们所不认识、并非耶和华所分派的神明。 27因此,耶和华向这片土地发怒,把这书上的一切咒诅都降在这里。 28耶和华盛怒之下把他们从这地方连根拔起,扔到别的地方,正如今日的情形。’

29“奥秘的事属于我们的上帝耶和华,只有显明的事永远属于我们和我们的子孙,以便我们可以遵守这律法上的一切话。”