ዘዳግም 17 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 17:1-20

1እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በእርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አትሠዋ።

2እግዚአብሔር (ያህዌ) በሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ አብሮህ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፣ 3ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፣ ለእርሱም ማለትም ለፀሓይ ወይም ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፣ 4አንተም ይህ መደረጉን ብትሰማ፣ ነገሩን በጥንቃቄ መርምር፤ የተባለውም እውነት ከሆነና እንዲህ ያለው አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣ 5ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፣ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። 6ሞት የሚገባው ሰው፣ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። 7ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፣ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ ክፉን ከመካከልህ አስወግድ።

የፍርድ አደባባይ

8በአንድ የነፍስ ግድያ ዐይነትና በሌላ፣ በአንድ ዐይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፣ ወይም በአንድ የክስ ዐይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጕዳይ ቢነሣ፣ ከዐቅምህ በላይ የሆነ ጕዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፣ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ፤ 9ካህናት ወደ ሆኑት ሌዋውያንና በዚያን ጊዜ ዳኛ ወደ ሆነው ሰው ሄደህ ስለ ጕዳዩ ጠይቃቸው፤ እነርሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል። 10አንተም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሚመርጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡህ ውሳኔ መሠረት ፈጽም። እንድትፈጽም የሚሰጡህን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርግ። 11በሚያስተምሩህ ሕግና በሚሰጡህ መመሪያዎች መሠረት ፈጽም። እነርሱ ከሚነግሩህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። 12አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህን ወይም ዳኛ የሚንቅ ይገደል፤ ከእስራኤልም መካከል ክፉውን አስወግድ። 13ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከዚያ ወዲያም እንዲህ ያለውን የንቀት ድርጊት አይደግመውም።

ንጉሥን ስለ ማንገሥ

14አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፣ “በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፣ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ” ብትል፣ 15አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፤ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ፣ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ። 16ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና። 17ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ።

18በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ፣ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅልል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ። 19አምላኩን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ማክበር ይማር ዘንድ፣ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዐት በጥንቃቄ ይከተል ዘንድ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው። 20እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ፣ ከሕጉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይቍጠር።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 17:1-20

1“不可把有缺陷或残疾的牛羊献给你们的上帝耶和华,因为这是祂所憎恶的。

2“如果有人在你们的上帝耶和华将要赐给你们的各城镇做祂视为恶的事,违背祂的约, 3不遵守祂的禁令,去供奉和祭拜其他神明,祭拜日、月或星辰, 4你们得知后,必须彻底调查。如果属实,在以色列确实有人做这种可憎之事, 5就要把那人带到城门口,用石头打死他。 6但你们不可单凭一个证人便处死那人,要有两三个证人方可处死他。 7证人要先扔石头,众人随后,这样就除掉了你们中间的罪恶。

复杂案件的处理

8“如果案件复杂,难以决断,如谋杀、诉讼、人身伤害等,就要把案件带到你们的上帝耶和华选定的地方, 9交给当值的利未祭司和审判官去审理。 10你们必须执行他们在耶和华所选择的地方宣告的判决,你们要谨慎遵行他们的一切指示。 11他们教导你们律法,宣布判决后,你们必须完全执行,丝毫不可偏离。 12如果有人不肯接受事奉你们上帝耶和华的祭司和审判官的判决,就必须处死他。如此,你们便从以色列除掉了罪恶, 13使众人得知后心中害怕,不敢再任意妄为。

立王的条例

14“你们进入并占领你们的上帝耶和华将要赐给你们的土地,安顿下来后,就会想立自己的王,像周围的国家一样。 15那么,你们一定要立你们的上帝耶和华拣选的人;必须立你们的以色列同胞为王,不可立外族人。 16王不可拥有大量马匹,也不可派人到埃及去购买马匹,因为耶和华已经告诉你们不可回埃及17他不可拥有许多妃嫔,恐怕他的心会偏离耶和华,也不可为自己积蓄大量金银。 18他登基后,要在利未祭司面前为自己抄录一份律法书, 19把它放在身边,一生诵读,以便学习敬畏他的上帝耶和华,遵守律法书上的一切诫命和律例。 20这样,他就不会妄自尊大,违背诫命,他和他的子孙就可以长久统治以色列