ፋሲካ
16፥1-8 ተጓ ምብ – ዘፀ 12፥14-20፤ ዘሌ 23፥4-8፤ ዘኍ 28፥16-25
1አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣህ፣ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፋሲካ አክብርበት። 2እግዚአብሔር (ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፋሲካ አድርገህ ሠዋው። 3ከቦካ ቂጣ ጋር አትብላው፤ ከግብፅ የወጣኸው በችኰላ ነውና ከግብፅ የወጣህበትን ጊዜ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ታስብ ዘንድ የመከራ ቂጣ ሰባት ቀን ብላ። 4በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ። 5አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ በማናቸውም ከተማ ፋሲካን መሠዋት አይገባህም፤ 6ነገር ግን ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚመርጠው ስፍራ፣ ፀሓይ ስትጠልቅ ምሽቱ16፥6 ወይም፣ ፀሓይ ስትወጣ ንጋቱ ላይ። ላይ ከግብፅ በወጣህበት ሰዓት16፥6 ወይም ዓመታዊ መታሰቢያ እንዲሆን፣ በዚያ ፋሲካን ሠዋ። 7ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ።
8ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የተቀደሰ ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት።
የመከር በዓል
16፥9-12 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥15-22፤ ዘኍ 28፥26-31
9እህልህን ማጨድ ከምትጀምርበት ዕለት አንሥቶ ሰባት ሳምንት ቍጠር። 10ከዚያም በኋላ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን፣ በፈቃድህ የምታመጣውን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አክብር። 11አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፣ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ደስ ይበላችሁ። 12አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ይህንም በጥንቃቄ ጠብቅ።
የዳስ በዓል
16፥13-17 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥33-43፤ ዘኍ 29፥12-39
13የእህልህን ምርት ከዐውድማህ፣ ወይንህንም ከመጭመቂያህ ከሰበሰብህ በኋላ፣ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብር። 14በበዓልህ አንተ፣ ወንድና ሴት ልጅህ፣ ወንድና ሴት አገልጋይህ፣ በከተማው ያለ ሌዋዊ፣ መጻተኛ፣ አባት አልባውና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15እግዚአብሔር (ያህዌ) በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል።
16ወንዶችህ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ፣ በቂጣ በዓል፣ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ይቅረቡ፤ ማንም ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ። 17አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።
ስለ ፍርድ አሰጣጥ
18አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ። 19ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጕቦም አትቀበል፤ ጕቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። 20በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።
ሌሎችን አማልክት ስለ ማምለክ
21ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም16፥21 ወይም፣ ለአሼራ ብለህ ምንም ዐይነት ዛፍ አትትከል።። 22አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለአንተ አታቁም።
เทศกาลปัสกา
(อพย.12:14-20; ลนต.23:4-8; กดว.28:16-25)
1จงฉลองเทศกาลปัสกาของพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านในเดือนอาบีบ เพราะในเดือนนั้นพระองค์ทรงนำท่านออกจากอียิปต์ในยามค่ำคืน 2จงเลือกเครื่องบูชาปัสกาจากฝูงแพะแกะและฝูงวัวของท่าน ถวายแด่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านในที่ซึ่งองค์พระผู้เป็นเจ้าจะทรงเลือกเป็นที่สถาปนาพระนามของพระองค์ 3จงรับประทานเครื่องบูชานี้พร้อมกับขนมปังไม่ใส่เชื้อ จงรับประทานขนมปังไม่ใส่เชื้อตลอดเจ็ดวันนี้ ซึ่งเป็นขนมปังแห่งความทุกข์ เพราะท่านออกมาจากอียิปต์อย่างเร่งรีบ เพื่อท่านจะได้ระลึกถึงตอนที่ท่านออกมาจากอียิปต์ตลอดชีวิตของท่าน 4ตลอดเจ็ดวันอย่าให้มีเชื้อยีสต์ในอาณาเขตของท่านเลย และอย่าให้เนื้อที่ท่านถวายในเย็นวันแรกเหลือค้างถึงรุ่งเช้า
5อย่าถวายเครื่องบูชาปัสกาในเมืองใดๆ ที่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านประทาน 6ท่านจะต้องถวายในสถานที่ซึ่งพระเจ้าทรงเลือกเป็นที่สถาปนาพระนามของพระองค์เท่านั้น จงถวายปัสกาในเวลาเย็นเมื่อดวงอาทิตย์ลับไป ในวันครบรอบปี16:6 หรือเมื่อตะวันตกดินในช่วงเวลานั้นของวันแห่งการเดินทางออกจากอียิปต์ 7จงย่างและรับประทานเครื่องบูชาในสถานที่ซึ่งพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านจะทรงเลือก แล้วกลับไปยังเต็นท์ในเช้าวันรุ่งขึ้น 8และจงรับประทานขนมปังไม่ใส่เชื้อตลอดหกวันหลังจากนั้น ในวันที่เจ็ดให้ประชากรมาชุมนุมกันต่อหน้าพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่าน และอย่าทำงาน
เทศกาลแห่งสัปดาห์
(ลนต.23:15-22; กดว.28:26-31)
9เจ็ดสัปดาห์หลังจากที่ท่านเริ่มลงมือเกี่ยวข้าว 10จงฉลองเทศกาลแห่งสัปดาห์ถวายแด่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านโดยถวายเครื่องบูชาตามความสมัครใจ ตามสัดส่วนของพระพรที่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านได้ประทานแก่ท่าน 11และท่าน บุตรชายบุตรสาว ทาสชายหญิง คนเลวีในเมืองของท่าน คนต่างด้าว ลูกกำพร้าพ่อ และหญิงม่ายซึ่งอาศัยอยู่ในหมู่พวกท่าน จงชื่นชมยินดีต่อหน้าพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านในสถานที่ซึ่งพระองค์จะทรงเลือกเป็นที่สถาปนาพระนามของพระองค์ 12อย่าลืมว่าท่านเคยเป็นทาสในอียิปต์ ฉะนั้นจงใส่ใจปฏิบัติตามกฎเกณฑ์เหล่านี้
เทศกาลอยู่เพิง
(ลนต.23:33-43; กดว.29:12-39)
13หลังจากเก็บรวบรวมผลิตผลจากลานนวดข้าวและบ่อย่ำองุ่นแล้ว จงฉลองเทศกาลอยู่เพิงตลอดเจ็ดวัน 14ท่าน บุตรชายบุตรสาว ทาสชายหญิง คนเลวี คนต่างด้าว ลูกกำพร้าพ่อ และหญิงม่ายในเมืองของท่านจงฉลองวาระชื่นชมยินดีด้วยกัน 15ตลอดเจ็ดวันจงฉลองเทศกาลนี้ถวายแด่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านในสถานที่ซึ่งองค์พระผู้เป็นเจ้าจะทรงเลือก เพราะพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านจะทรงอวยพรท่านในการเก็บเกี่ยวและในการงานทุกอย่างที่ท่านทำ และท่านจะชื่นชมยินดีเต็มที่
16ชายทุกคนในอิสราเอลต้องเข้าเฝ้าพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านปีละสามครั้งในสถานที่ซึ่งพระองค์ทรงเลือกในเทศกาลขนมปังไม่ใส่เชื้อ เทศกาลแห่งสัปดาห์ และเทศกาลอยู่เพิง อย่าให้ผู้ใดเข้าเฝ้าองค์พระผู้เป็นเจ้ามือเปล่า 17แต่ละคนจงนำของถวายมาตามสัดส่วนที่พระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านทรงอวยพร
ตุลาการ
18จงแต่งตั้งตุลาการและเจ้าหน้าที่ปกครองสำหรับแต่ละเผ่าในทุกเมืองซึ่งพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านจะประทานแก่ท่าน คนเหล่านี้จะตัดสินความอย่างยุติธรรม 19อย่าบิดเบือนความยุติธรรมหรือมีอคติลำเอียง อย่ารับสินบนเพราะสินบนบังตาคนที่มีสติปัญญาและบิดเบือนถ้อยคำของผู้ชอบธรรม 20จงปฏิบัติตามความยุติธรรมเท่านั้น เพื่อท่านจะมีชีวิตอยู่และครอบครองดินแดนซึ่งพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านจะประทานแก่ท่าน
การนมัสการพระอื่น
21อย่าตั้งเสาไม้ของเจ้าแม่อาเชราห์ขึ้นข้างๆ แท่นบูชาที่ท่านสร้างถวายพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่าน 22และอย่าตั้งหินศักดิ์สิทธิ์ขึ้น เพราะพระยาห์เวห์พระเจ้าของท่านทรงเกลียดชังสิ่งเหล่านี้