ዘካርያስ 8 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 8:1-23

እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለመባረክ ቃል ገባ

1እንደ ገናም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ስለ ጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ፤ ስለ እርሷም በቅናት ነድጃለሁ።”

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የእግዚአብሔር ጸባኦት ተራራም ቅዱስ ተራራ ይባላል።”

4እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ሽማግሌዎችና አሮጊቶች እንደ ገና በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ብዛት የተነሣ ምርኵዝ ይይዛሉ። 5የከተማዪቱም አደባባዮች እዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።” 6እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በዚያን ጊዜ ይህ ለቀረው የእስራኤል ሕዝብ አስደናቂ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ለእኔ ግን አስደናቂ ሊሆን ይችላልን?” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋለሁ። 8በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በጽድቅና በታማኝነት አምላካቸው እሆናለሁ።”

9እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት መሠረት ሲጣል፣ በዚያ የነበሩ ነቢያት የተናገሩትን ቃል አሁን የምትሰሙ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመሥራት እጃችሁን አበርቱ። 10ከዚያ በፊት ለሰው ደመወዝ፣ ለእንስሳም ኪራይ አይከፈልም ነበር፤ ጠላት በመኖሩም ማንም ሥራውን በሰላም ማከናወን አልቻለም፤ እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው ላይ እንዲነሣ አድርጌ ነበርና። 11አሁን ግን ቀድሞ እንዳደረግሁት በዚህ በቀረው ሕዝብ ላይ አላደርግም” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

12“ዘሩ ጥሩ ሆኖ ይበቅላል፤ ወይኑ ፍሬውን ያፈራል፤ ምድሪቱ አዝመራዋን ታበረክታለች፤ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለቀሪው ሕዝብ ርስት አድርጌ እሰጣለሁ። 13የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል የርግማን ምሳሌ ነበራችሁ፤ አሁን ግን አድናችኋለሁ፤ እናንተም በረከት ትሆናላችሁ። አትፍሩ፤ ነገር ግን እጃችሁን አበርቱ።”

14እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ያለ አንዳች ሐዘኔታ ጥፋት ላመጣባችሁ እንደ ወሰንሁ፣” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤ 15“አሁን ደግሞ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ መልካም ነገርን ላደርግ ወስኛለሁ፤ አትፍሩ። 16ልታደርጓቸው የሚገባችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም እውነትንና ትክክለኛ ፍርድን አስፍኑ፤ 17በባልንጀራችሁ ላይ ክፋትን በልባችሁ አታውጠንጥኑ፤ በሐሰት መማልን አትውደዱ፤ እነዚህን ሁሉ እጸየፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር18እንደ ገናም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 19እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”

20እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ሕዝቦችና የብዙ ከተሞች ነዋሪዎች ገና ይመጣሉ፤ 21የአንዲቱ ከተማ ነዋሪዎችም፣ ‘እግዚአብሔርን ለመለመን እግዚአብሔር ጸባኦትን ለመፈለግ፣ ኑ፤ በፍጥነት እንሂድ፤ እኔም ራሴ እሄዳለሁ’ እያሉ ወደ ሌላዪቱ ከተማ ይሄዳሉ። 22ብዙ ሕዝብና ኀያላን መንግሥታትም እግዚአብሔር ጸባኦትን ለመፈለግና ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።” 23እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በእነዚያም ቀናት ከየወገኑና ከየቋንቋው ዐሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና አብረን እንሂድ’ ” ይሉታል።

Thai New Contemporary Bible

เศคาริยาห์ 8:1-23

องค์พระผู้เป็นเจ้า

1อีกครั้งหนึ่งมีพระดำรัสของพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์มาถึงข้าพเจ้าว่า 2พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “เราหวงแหนศิโยนยิ่งนัก เราหวงแหนด้วยใจที่รุ่มร้อน”

3องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสดังนี้ว่า “เราจะกลับมาหาศิโยน มาอยู่ในเยรูซาเล็ม แล้วเยรูซาเล็มจะได้ชื่อว่า ‘นครแห่งความจริง’ และภูเขาของพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์จะได้ชื่อว่า ‘ภูเขาศักดิ์สิทธิ์’ ”

4พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “ตามถนนหนทางในเยรูซาเล็มจะกลับมีชายหญิงที่แก่หง่อม ถือไม้เท้านั่งอยู่เหมือนแต่ก่อน 5ตามท้องถนนก็มีเด็กชายหญิงวิ่งเล่นอยู่”

6พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “มันอาจดูเป็นไปไม่ได้สำหรับชนหยิบมือที่เหลืออยู่นี้ แต่สำหรับเราแล้วมันจะเป็นไปไม่ได้เชียวหรือ?” พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ประกาศดังนั้น

7พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “เราจะช่วยประชากรของเราจากประเทศต่างๆ ทางตะวันออกและตะวันตก 8เราจะพาพวกเขากลับมาอยู่ที่เยรูซาเล็ม เขาจะเป็นประชากรของเรา และเราจะเป็นพระเจ้าผู้ซื่อสัตย์และชอบธรรมของเขา”

9พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “พวกเจ้าซึ่งบัดนี้ฟังถ้อยคำของบรรดาผู้เผยพระวจนะซึ่งอยู่ด้วยเมื่อครั้งวางฐานรากพระนิเวศของพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ จงให้มือของเจ้าเข้มแข็งเพื่อสร้างพระวิหารให้สำเร็จ 10ก่อนหน้านั้นไม่มีค่าจ้างให้คนหรือสัตว์ ผู้คนที่สัญจรไปมาเพื่อค้าขายก็ไม่ปลอดภัยจากศัตรู เพราะเราทำให้เพื่อนบ้านทุกคนเป็นศัตรูกัน 11แต่เดี๋ยวนี้เราจะไม่ทำกับชนหยิบมือที่เหลืออยู่เหมือนในอดีต” พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ประกาศดังนั้น

12“เมล็ดจะงอกงาม เถาองุ่นจะออกผล ผืนแผ่นดินจะให้พืชผล และฟ้าจะหยาดน้ำค้างลงมา เราจะมอบสิ่งทั้งปวงนี้ให้เป็นกรรมสิทธิ์ของชนหยิบมือที่เหลืออยู่ 13ยูดาห์และอิสราเอลเอ๋ย เจ้าเคยเป็นที่สาปแช่งในหมู่ชนชาติทั้งหลายนั้นอย่างไร เราจะช่วยเจ้าและเจ้าจะเป็นพระพรอย่างนั้น อย่ากลัวเลย แต่จงให้มือของเจ้าเข้มแข็ง”

14พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “ตามที่เราเคยตัดสินใจนำภัยพิบัติมายังเจ้าและไม่ปรานีเจ้า ตอนที่บรรพบุรุษของเจ้าทำให้เราโกรธ” พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสดังนั้น 15“แต่บัดนี้เราตัดสินใจจะทำดีต่อเยรูซาเล็มและยูดาห์อีก ฉะนั้นอย่ากลัวเลย 16เจ้าจงทำอย่างนี้คือ จงพูดความจริงต่อกัน จงตัดสินความในศาลอย่างถูกต้องและเที่ยงธรรม 17อย่าคิดร้ายต่อเพื่อนบ้าน และอย่าชอบสาบานเท็จ เพราะเราเกลียดชังสิ่งทั้งปวงนี้” องค์พระผู้เป็นเจ้าประกาศดังนั้น

18อีกครั้งหนึ่งมีพระดำรัสของพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์มาถึงข้าพเจ้า 19พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “การถืออดอาหารในเดือนที่สี่ เดือนที่ห้า เดือนที่เจ็ด และเดือนที่สิบ จะเป็นเวลาแห่งความชื่นชมยินดีและเปรมปรีดิ์ และเป็นเทศกาลแห่งความสุขสำหรับยูดาห์ ฉะนั้นจงรักความจริงและสันติภาพ”

20พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “ชนชาติต่างๆ และคนที่อาศัยอยู่ในนครต่างๆ หลายแห่งยังจะมา 21ชาวเมืองหนึ่งจะไปชวนอีกเมืองหนึ่งว่า ‘ให้เราไปทูลอ้อนวอนองค์พระผู้เป็นเจ้าเดี๋ยวนี้ ไปแสวงหาพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์กันเถิด เราเองก็จะไปด้วย’ 22ชนชาติทั้งหลายและชาติมหาอำนาจต่างๆ จะมายังเยรูซาเล็มเพื่อแสวงหาพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์และอ้อนวอนพระองค์”

23พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า “เมื่อถึงเวลานั้นชายสิบคนจากทุกชาติทุกภาษาจะยึดชายเสื้อคลุมของชาวยิวคนหนึ่งไว้และกล่าวว่า ‘ขอเราไปกับท่านเถิด เพราะเราได้ยินมาว่าพระเจ้าสถิตกับท่าน’ ”