ዘካርያስ 6 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 6:1-15

አራቱ ሠረገሎች

1እንደ ገናም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። 2የመጀመሪያው ሠረገላ መጋላ፣ ሁለተኛው ዱሪ፤ 3ሦስተኛው ዐምባላይ፤ አራተኛውም ዝጕርጕር ፈረሶች ነበሯቸው፤ ሁሉም ጠንካሮች ነበሩ። 4እኔም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት።

5መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ አራቱ ቆመው ከነበሩበት ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት የወጡ የሰማይ መናፍስት6፥5 ወይም ነፋሳት ሊሆን ይችላል። ናቸው። 6የባለ ዱሪ ፈረሶች ወደ ሰሜን፤ የባለ አምባላይ ፈረሶች ወደ ምዕራብ6፥6 ወይም ከኋላቸው ፈረሶች እንደ ማለት ነው። አገር፣ የባለ ዝጕርጕር ፈረሶች ወደ ደቡብ አገር ይወጣል።” 7ጠንካሮቹ ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ለመመላለስ አቈብቍበው ነበር። እርሱም፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። 8ከዚያም ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ወደ ሰሜን አገር የሚወጡት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።”

ለኢያሱ የተደረገለት አክሊል

9የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 10“ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ከሔልዳይና ከጦብያ፣ ከዮዳኤም ወርቅና ብር ውሰድ፤ በዚያው ቀን ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ። 11ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ፤ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ በኢያሱ ራስ ላይም አድርገው፤ 12ለእርሱም እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እነሆ፤ ስሙ ቅርንጫፍ የተባለው ሰው ይህ ነው፤ እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ይሠራል። 13የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብርን ይጐናጸፋል፤ በዙፋኑ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል።’ 14አክሊሉም ለሔሌምና6፥14 ሲርያክ፤ ዕብራይስጡ ሔሌም ይላል። ለጦብያ፣ ለዮዳኤና ለሶፎንያስ ልጅ ለሔን6፥14 ወይም ርኅሩኁ እንደ ማለት ነው። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መታሰቢያ ይሆናል። 15እነዚያ በሩቅ ያሉት መጥተው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሠራ ያግዛሉ፤ እናንተም እግዚአብሔር ጸባኦት እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በጥንቃቄ ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

撒迦利亚书 6:1-15

四辆马车

1我又举目观看,见有四辆马车从两座铜山之间出来。 2第一辆车套着红马,第二辆车套着黑马, 3第三辆车套着白马,第四辆车套着斑点马,马都很雄壮。 4我问与我说话的天使:“主啊,这些马车是什么意思?” 5天使说:“他们是侍立在天下之主面前的四灵6:5 ”或译“风”。,正在出发。” 6套着黑马的车前往北方,套着白马的车前往西方6:6 前往西方”或译“跟在后面”。,套着斑点马的车前往南方。 7这些雄壮的马出来,迫不及待地要巡察大地。天使说:“你们去巡察大地吧!”它们便遵命而行。 8他又高声对我说:“看啊,那些到北方去的已在那里使我的心得到安慰。”

为约书亚加冕

9耶和华的话传给了我,说: 10“被掳到巴比伦黑玳多比雅耶大雅已经回来了,你要收集他们奉献的金银,并在当天去西番雅的儿子约西亚家。 11要用这些金银制作冠冕,戴在约撒答的儿子约书亚大祭司头上, 12告诉他,万军之耶和华说,‘看啊,那被称为大卫苗裔的要从自己的地方兴起,建造耶和华的殿。 13祂必建造耶和华的殿,带着王者的尊荣坐在宝座上掌权,宝座上也必坐着祭司6:13 宝座上也必坐着祭司”或译“并在宝座上做祭司”。,两者和谐共存。’ 14这冠冕要留在耶和华的殿中,作为对黑玳6:14 黑玳”希伯来文作“希连”。多比雅耶大雅西番雅的儿子约西亚6:14 约西亚”希伯来文作“贤”,意思是“恩慈者”。的纪念。”

15远方的人也要来建造耶和华的殿。那时你们便知道是万军之耶和华差遣我到你们这里来的。你们若全心遵从你们上帝耶和华的话,这事就必成就。