ዘካርያስ 3 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 3:1-10

ለሊቀ ካህኑ የሚሆን ንጹሕ ልብስ

1እርሱም ሊቀ ካህኑን ኢያሱን3፥1 የየሽዋ ለሚለው ተለዋጭ ስም ነው፤ እዚህ ላይ እንዲሁም በዘካርያስ መጽሐፍ በሌሎች ቦታ። በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ፣ ሰይጣንም3፥1 ሰይጣንም ትርጕሙ “ከሳሽ” ማለት ነው። ሊከስሰው በስተ ቀኙ ቆሞ አሳየኝ። 2እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን፤ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።

3ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። 4መልአኩም ከፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው።

ኢያሱንም፣ “እነሆ፤ ኀጢአትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው።

5እኔም፣ “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት” አልሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ እያለ፣ ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት።

6የእግዚአብሔርም መልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤ 7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።

8“ ‘ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ሆይ፤ ስማ፤ በፊትህ የሚቀመጡትም ረዳቶችህ ገና ወደ ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፤ ባሪያዬን ቍጥቋጡን አመጣለሁ። 9በኢያሱ ፊት ያስቀመጥሁት ድንጋይ እነሆ፤ በዚያ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች3፥9 ወይም ገጾች አሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

10“ ‘በዚያን ቀን እያንዳንዱ በገዛ ወይኑና በለሱ ሥር ሆኖ ባልንጀራውን ይጋብዛል’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።”

Thai New Contemporary Bible

เศคาริยาห์ 3:1-10

เครื่องแต่งกายสะอาดสำหรับมหาปุโรหิต

1แล้วทูตองค์นั้นได้แสดงให้ข้าพเจ้าเห็นมหาปุโรหิตโยชูวา3:1 เป็นอีกรูปหนึ่งของเยชูวาเช่นเดียวกับที่อื่นๆ ในพระธรรมเศคาริยาห์ยืนอยู่ต่อหน้าทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้า และซาตาน3:1 แปลว่า ผู้กล่าวโทษยืนอยู่ขวามือของเขาเพื่อกล่าวหาเขา 2องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับซาตานว่า “ซาตาน! องค์พระผู้เป็นเจ้าตำหนิเจ้า องค์พระผู้เป็นเจ้าผู้เลือกสรรเยรูซาเล็มตำหนิเจ้า! ชายผู้นี้เป็นดุ้นฟืนติดไฟที่ถูกดึงออกจากไฟไม่ใช่หรือ?”

3โยชูวานั้นสวมเสื้อผ้าสกปรกยืนอยู่ต่อหน้าทูตสวรรค์องค์นั้น 4ทูตนั้นกล่าวแก่บรรดาผู้ยืนอยู่เบื้องหน้าเขาว่า “ถอดเสื้อผ้าสกปรกของเขาออกเถิด”

แล้วกล่าวกับโยชูวาว่า “ดูเถิด เราได้ปลดเปลื้องบาปของเจ้าออกไปแล้ว และเราจะให้เจ้าสวมเสื้อผ้างดงาม”

5ข้าพเจ้าจึงกล่าวว่า “ขอให้เอาผ้าโพกศีรษะที่สะอาดมาโพกให้เขา” แล้วพวกเขาก็โพกศีรษะโยชูวาด้วยผ้าสะอาดและแต่งกายให้ขณะที่ทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้ายืนอยู่ใกล้ๆ

6ทูตขององค์พระผู้เป็นเจ้ากล่าวกำชับโยชูวาว่า 7“พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า ‘หากเจ้าดำเนินในวิถีทางของเรา และรักษากฎเกณฑ์ของเรา เจ้าจะได้ปกครองนิเวศของเรา รวมทั้งลานวิหารของเรา เราจะให้เจ้าดำเนินอยู่ต่อหน้าเราร่วมกับคนเหล่านี้ที่ยืนอยู่ที่นี่

8“ ‘ฟังเถิด มหาปุโรหิตโยชูวาและเพื่อนร่วมงานซึ่งนั่งอยู่ตรงหน้าเจ้า พวกเจ้าผู้เป็นคนซึ่งเป็นสัญลักษณ์บ่งถึงสิ่งที่จะเกิดขึ้นในอนาคต เราจะนำผู้รับใช้ของเรามาคือ “กิ่ง” 9จงดูศิลาที่เราตั้งไว้ตรงหน้าโยชูวาเถิด! ศิลาก้อนเดียวมีเจ็ดเหลี่ยม3:9 หรือเจ็ดตา และเราจะสลักคำจารึกบนศิลานั้น’ พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า ‘และเราจะขจัดบาปของดินแดนนี้ภายในวันเดียว

10“ ‘ในวันนั้น พวกเจ้าแต่ละคนจะเชิญเพื่อนบ้านมานั่งใต้เถาองุ่นและต้นมะเดื่อของตน’ พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ประกาศดังนั้น”