ዘሌዋውያን 7 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 7:1-38

የበደል መሥዋዕት

1“ ‘እጅግ ቅዱስ የሆነው የበደል መሥዋዕት የአቀራረብ ሥርዐት ይህ ነው፦ 2የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የበደሉም መሥዋዕት እዚያው ይታረድ፤ ደሙም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይረጭ። 3ሥቡን በሙሉ ያቅርብ፤ ይኸውም፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ 4ሁለቱ ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም ከኵላሊቶቹ ጋር የሚወጣውን የጕበቱን ሽፋን አብሮ ያቅርብ። 5ካህኑም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ይህም የበደል መሥዋዕት ነው። 6ከካህን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከዚህ መብላት ይችላል፤ ነገር ግን በተቀደሰ ስፍራ ይበላ፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው።

7“ ‘የኀጢአት መሥዋዕትና የበደል መሥዋዕት አቀራረብ ሥርዐት አንድ ነው፤ መሥዋዕቶቹ የስርየቱን ሥርዐት ለሚያስፈጽመው ካህን ይሰጣሉ። 8ስለ ማንኛውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበው ካህን ቈዳውን ለራሱ ይውሰድ። 9በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቍርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ። 10ማናቸውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቍርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ።

የኅብረት መሥዋዕት

11“ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት7፥11 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል፤ እንዲሁም 13-37 ይመ በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፦

12“ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋር ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥቡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት አብሮ ያቅርብ። 13ለምስጋና ከሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ጋር፣ በእርሾ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ። 14ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ። 15ለምስጋና የሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ እንጂ አንዳች አይደር።

16“ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱም ይበላ። 17እስከ ሦስት ቀን የቈየ ማንኛውም የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቃጠል። 18ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።

19“ ‘ርኩስ ከሆነ ነገር ጋር የተነካካ ሥጋ ይቃጠል እንጂ አይበላ። ሌላውን ሥጋ ግን በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይብላ፤ 20ነገር ግን ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የቀረበውን የትኛውንም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ከሕዝቡ ፈጽሞ ይወገድ። 21ማንኛውም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም ርኩስ እንስሳን ወይም ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ያ ሰው ፈጽሞ ከሕዝቡ ይወገድ።’ ”

ሥብና ደም መብላት መከልከሉ

22እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 23“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የበሬ ወይም የላም፣ የበግ ወይም የፍየል ሥብ አትብሉ። 24ሞቶ የተገኘ ወይም አውሬ የገደለው ከብት ሥብ ለሌላ ተግባር ይዋል እንጂ አይበላ። 25ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ከሚቀርብ7፥25 ወይም በእሳት ከቀረበው እንስሳ ሥብ የሚበላ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ ይወገድ። 26በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ። 27ማንኛውም ሰው ደም ቢበላ፣ ያ ሰው ከሕዝቡ ይወገድ።’ ”

የካህኑ ድርሻ

28እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 29“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ስለ ራሱ መሥዋዕት አድርጎ ከዚሁ ላይ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቅርብ። 30በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው፤ ሥቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርብ፤ ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ይወዝውዘው። 31ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ። 32የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት። 33የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ሥብ የሚያቀርበው የአሮን ልጅ ቀኝ ወርቹን የራሱ ድርሻ አድርጎ ይውሰድ። 34ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ”

35ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲያገለግሉ በቀረቡ ቀን፣ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከቀረበው መሥዋዕት ላይ ለአሮንና ለልጆቹ የተመደበላቸው ድርሻ ይህ ነው። 36ካህናቱ በተቀቡበት ቀን፣ እስራኤላውያን መደበኛ ድርሻ አድርገው ከትውልድ እስከ ትውልድ ይህን እንዲሰጧቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) አዘዘ።

37እንግዲህ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የኀጢአት መሥዋዕት፣ የበደል መሥዋዕት፣ የክህነት ሹመት መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው፤ 38ይህም፣ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠው ሥርዐት ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

利未記 7:1-38

祭司獻贖過祭的條例

1「以下是獻贖過祭的條例。

「贖過祭是至聖的。 2要在殺燔祭牲的地方宰贖過祭祭牲,祭牲的血要灑在祭壇周圍。 3要獻上祭牲的所有脂肪,包括肥尾巴、遮蓋內臟的脂肪、 4兩個腎臟和腎臟上靠近腰部的脂肪以及肝葉。 5祭司要在壇上焚燒這一切,作為獻給耶和華的火祭。這是贖過祭。 6祭司家的任何男子都可以吃剩下的祭肉,但要在聖潔之處吃,因為這是至聖之物。 7祭物要歸主持祭禮的祭司,這一條例也適用於贖罪祭。 8燔祭牲的皮要歸主持祭禮的祭司。 9至於素祭,不論是用爐烤的,還是用平底鍋或煎鍋做的,都要歸主持祭禮的祭司。 10但調油的或乾的素祭要歸亞倫的子孫,由他們均分。

獻平安祭的條例

11「以下是向耶和華獻平安祭的條例。

12「如果有人為感謝耶和華而獻平安祭,除了獻祭牲以外,要一同獻上調油的無酵餅、塗油的無酵薄餅及調油的細麵餅, 13也要一同獻上有酵餅。 14他要從每種餅中各取一個,作為舉祭獻給耶和華。舉祭歸灑平安祭祭牲血的祭司。 15至於祭牲的肉,要在獻祭的當天吃完,不可留到次日早晨。 16如果是自願獻的或為了還願而獻的祭物,要在當天吃祭肉,剩下的可以留到第二天吃。 17但到第三天,必須燒掉剩下的祭肉。 18如果第三天仍然吃,所獻的祭便不蒙悅納,毫無價值,是不潔淨的。吃的人要自擔罪責。

19「祭肉如果接觸到任何不潔之物,就不可以吃,要燒掉。潔淨的人都可以吃平安祭的祭肉。 20如果有人不潔淨,卻吃獻給耶和華的平安祭祭肉,要將他從民中剷除。 21如果有人接觸到人或獸的不潔之物,或任何不潔的可憎之物,又吃獻給耶和華的平安祭祭肉,要將他從民中剷除。」

22耶和華對摩西說: 23「你把以下條例告訴以色列人。

「你們不可吃牛、綿羊或山羊的脂肪。 24自然死亡或被野獸咬死的動物的脂肪也不可吃,但可以作其他用途。 25無論誰吃了獻給耶和華的火祭祭牲的脂肪,都要將他從民中剷除。 26你們無論住在哪裡,都不可吃鳥和獸的血。 27凡吃血的,要將他從民中剷除。」

28耶和華對摩西說: 29「你把以下條例告訴以色列人。

「凡向耶和華獻平安祭的,都要從平安祭中取出一份獻給耶和華作禮物。 30他要親手將這獻給耶和華的火祭帶來,將祭牲的脂肪和胸肉帶來,在耶和華面前將胸肉搖一搖,當作搖祭獻上。 31祭司要把脂肪放在壇上焚燒,胸肉歸亞倫及其子孫。 32你們要把祭牲的右腿獻為舉祭,歸給祭司。 33要把右腿歸給亞倫子孫中獻平安祭的血和脂肪的那位祭司。 34因為耶和華已經從以色列人獻的平安祭中,把作搖祭的胸肉和作舉祭的腿肉賜給祭司亞倫及其子孫。他們在以色列人中要永遠享有這一份。 35亞倫及其子孫受膏為祭司事奉耶和華開始,在獻給耶和華的火祭中,這是他們應得之份。 36祭司受膏之日,耶和華就命令以色列人把這部分祭肉分給他們,這是他們世世代代應得之份。」

37以上是獻燔祭、素祭、贖罪祭、贖過祭、平安祭和授聖職時所獻之祭的條例。 38這些條例是耶和華在西奈山上吩咐摩西的。同一天,摩西命令以色列人在西奈曠野向耶和華獻祭。