ዘሌዋውያን 6 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 6:1-30

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ማንኛውም ሰው በዐደራ የተሰጠውን ወይም በመያዣነት የተቀበለውን በመካድና ባልንጀራውን በማጭበርበር ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔርንም (ያህዌ) ቢበድል ወይም ባልንጀራውን ቢቀማው ወይም ቢያታልለው፣ 3ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን እንዲህ ያለውን ማናቸውንም ኀጢአት ቢሠራ፣ 4በዚህ ሁኔታ ኀጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ የሰረቀውን ወይም የቀማውን ወይም በዐደራ የተሰጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን ይመልሳል፤ 5በሐሰት የማለበትንም ሁሉ ይመልስ፤ የበደል መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ጊዜ የወሰደውን በሙሉ የዋናውን አንድ አምስተኛ በመጨመር ለባለንብረቱ ንብረቱ ይመልስ። 6ከመንጋውም እንከን የሌለበትን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አውራ በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ 7በዚህም ሁኔታ ካህኑ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ስለ ፈጸመው ስለ ማንኛውም በደል ይቅር ይባላል።”

የሚቃጠል መሥዋዕት

8እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 9“አሮንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ስለሚቃጠለው መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጥ፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ሲነድድ ይደር። 10ካህኑም ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ሱሪውን ካጠለቀ በኋላ፣ የበፍታ ቀሚሱን ይልበስ፤ እሳቱ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕቱን ከበላው በኋላ የሚቀረውን ዐመድ አንሥቶ፣ በመሠዊያው አጠገብ ያፍስስ። 11ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይቀይር፤ ዐመዱንም ተሸክሞ ከሰፈር ውጭ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ይውሰድ። 12በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምንጊዜም አይጥፋ። ካህኑ ጧት ጧት እሳቱ ላይ ማገዶ ይጨምር፤ በእሳቱ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያዘጋጅ፤ በዚህም ላይ የኅብረት መሥዋዕቱን6፥12 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። ሥብ ያቃጥል። 13በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምንጊዜም አይጥፋ።

የእህል ቍርባን

14“ ‘የእህል ቍርባን ሥርዐት ይህ ነው፦ የአሮን ልጆች ቍርባኑን በመሠዊያው ትይዩ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርቡት። 15ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ ዕፍኝ ያንሣለት፤ በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውንም ዕጣን በሙሉ ይውሰድ፤ ይህንም፣ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ፣ ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው። 16የተረፈውንም አሮንና ልጆቹ ይብሉት፤ እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ፣ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ አደባባዩ ላይ ይብሉት። 17ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቍርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው። 18ማንኛውም ከአሮን ዘር የተወለደ ወንድ ሊበላው ይችላል፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከሚቀርበው የእሳት ቍርባን ለእርሱ የተመደበ የዘላለም ድርሻው ነው፤ የሚነካውም ሁሉ6፥18 ወይም የሚነካው ሰው ሁሉ፤ እንዲሁም 27 ይመ ቅዱስ ይሆናል።’ ”

19እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 20“አሮን ወይም ልጆቹ በተቀቡበት ዕለት6፥20 ወይም በተቀባበት ዕለት አሮን እና ልጆቹ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፦ የኢፍ6፥20 ሁለት ሊትር ገደማ ይሆናል አንድ ዐሥረኛው የላመ ዱቄት ግማሹን ለጧት፣ ግማሹን ለማታ የዘወትር የእህል ቍርባን አድርገው ያቅርቡት። 21በሚገባ በዘይት ተለውሶ በምጣድ ላይ ይጋገር፤ ከዚያም የእህሉን ቍርባን ቈራርሰህ6፥21 የዚህ ቃል የዕብራይስጡ ትርጓሜ በርግጠኝነት አይታወቅም ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ አቅርብ። 22በእርሱ ቦታ ተቀብቶ ካህን የሚሆነው ልጁ ይህን ያዘጋጅ፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተመደበ ድርሻ ነውና ፈጽሞ ይቃጠል። 23ካህኑ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃጠል እንጂ አይበላ።”

የኀጢአት መሥዋዕት

24እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 25“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱም መሥዋዕት እዚያው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ይታረድ፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው። 26መሥዋዕቱንም የሚያቀርበው ካህን ይብላው፤ ይህም በተቀደሰው ስፍራ በመገናኛው ድንኳን ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ በአደባባዩ ላይ ይበላ። 27ሥጋውን የሚነካ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ ደሙ በልብስ ላይ ቢረጭ፣ ያን ልብስ በተቀደሰ ስፍራ ዕጠብ። 28ሥጋው የተቀቀለበት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ የናስ ዕቃ ከሆነ ግን ተፈግፍጎ በውሃ ይታጠብ። 29ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከዚህ መብላት ይችላል፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው። 30ነገር ግን ደሙ ማስተስረያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደ ቅድስት የቀረበው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ በእሳት ይቃጠል እንጂ አይበላ።

Thai New Contemporary Bible

เลวีนิติ 6:1-30

1องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 2“ผู้ใดทำบาปและไม่ซื่อตรงต่อองค์พระผู้เป็นเจ้า โดยหลอกเพื่อนบ้านเกี่ยวกับสิ่งของที่รับฝาก หรืออยู่ในการดูแล หรือถูกขโมย หรือคดโกงเพื่อนบ้าน 3หรือเก็บของได้และโกหกว่าไม่ได้เอาไป หรือสาบานเท็จ หรือทำบาปใดๆ 4เมื่อเขาทำบาปและมีความผิด เขาต้องคืนสิ่งที่ขโมย หรือที่ขู่กรรโชกมา หรือของที่เขารับฝากไว้ หรือของที่เขาเก็บได้ 5หรืออะไรก็ตามที่เขาสาบานเท็จเกี่ยวกับสิ่งนั้น เขาต้องชดใช้ให้เต็มราคา และเพิ่มอีกหนึ่งในห้าของราคานั้นให้กับเจ้าของในวันที่เขาถวายเครื่องบูชาลบความผิด 6และเพื่อเป็นการลงโทษ เขาต้องนำเครื่องบูชาลบความผิดมาให้ปุโรหิต นั่นคือเขาต้องถวายแกะผู้ที่ไม่มีตำหนิและมีค่าเหมาะสมจากฝูงแด่องค์พระผู้เป็นเจ้า 7ปุโรหิตจะทำการลบบาปให้เขาต่อหน้า องค์พระผู้เป็นเจ้าด้วยวิธีนี้ แล้วเขาจะได้รับการอภัยสำหรับความผิดเหล่านี้ที่ได้ทำไป”

เครื่องเผาบูชา

8องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 9“จงแจ้งคำสั่งนี้แก่อาโรนและบรรดาบุตรชายของเขาว่า ‘นี่เป็นกฎระเบียบเกี่ยวกับเครื่องเผาบูชา ให้ทิ้งเครื่องเผาบูชาไว้ตรงที่เผาตลอดคืนจนรุ่งเช้า และปล่อยให้ไฟบนแท่นบูชาลุกอยู่เช่นนั้น 10แล้วปุโรหิตจะสวมเครื่องแต่งกายที่ทำจากผ้าลินินพร้อมกับเครื่องแต่งกายชั้นในที่ติดกับตัว และเขาจะกวาดเถ้าของเครื่องเผาบูชากองไว้ข้างแท่น 11จากนั้นเขาต้องเปลี่ยนเสื้อผ้า แล้วนำเถ้าออกนอกค่ายพักแรมไปยังที่ที่ไม่เป็นมลทินตามระเบียบพิธี 12ให้ไฟบนแท่นบูชาลุกอยู่ตลอดเวลา อย่าให้ดับ ปุโรหิตจะเติมฟืนทุกเช้า วางเครื่องเผาบูชาประจำวันบนฟืน แล้วเผาไขมันของเครื่องสันติบูชาบนแท่น 13จงให้ไฟลุกโชนอยู่ที่แท่นตลอดเวลา อย่าให้ดับเลย

เครื่องธัญบูชา

14“ ‘ต่อไปนี้เป็นกฎระเบียบเกี่ยวกับเครื่องธัญบูชา บรรดาบุตรชายของอาโรนจะนำเครื่องธัญบูชามาต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าหน้าแท่นบูชา 15ปุโรหิตจะเอาแป้งบดละเอียดหนึ่งกำมือ เคล้าน้ำมันและเครื่องหอมจากเครื่องธัญบูชา แล้วเผาส่วนอนุสรณ์นั้นบนแท่นบูชา เป็นกลิ่นหอมที่องค์พระผู้เป็นเจ้าพอพระทัย 16อาโรนและบรรดาบุตรชายจะกินส่วนที่เหลือ แต่ต้องกินโดยไม่ใส่เชื้อในที่บริสุทธิ์ นั่นคือที่ลานเต็นท์นัดพบ 17จะต้องอบแป้งนั้นโดยไม่ใส่เชื้อ เรายกเครื่องบูชาส่วนนี้ซึ่งถวายแก่เราด้วยไฟให้เป็นส่วนของปุโรหิต เป็นของบริสุทธิ์ที่สุดเช่นเดียวกับเครื่องบูชาไถ่บาปและเครื่องบูชาลบความผิด 18ลูกหลานของอาโรนที่เป็นผู้ชายจะกินของนี้ได้ เป็นส่วนประจำของเขาจากเครื่องบูชาด้วยไฟถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าสืบไปทุกชั่วอายุ สิ่งใดก็ตามที่แตะต้องสิ่งเหล่านี้จะบริสุทธิ์6:18 หรือผู้ใดก็ตามที่แตะต้องสิ่งเหล่านี้จะต้องบริสุทธิ์เหมือนกับข้อ 27’ ”

19แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสอีกว่า 20“นี่คือเครื่องบูชาที่อาโรนและบรรดาบุตรชายของเขาจะต้องนำมาถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าในวันที่เขา6:20 หรือแต่ละคนได้รับการเจิมตั้ง คือแป้งละเอียดประมาณ 2 ลิตร6:20 ภาษาฮีบรูว่า หนึ่งในสิบเอฟาห์ เป็นเครื่องธัญบูชาที่ถวายเป็นประจำ ครึ่งหนึ่งถวายตอนเช้า อีกครึ่งหนึ่งถวายตอนเย็น 21จงทอดแป้งนั้นกับน้ำมันในกระทะ คลุกเคล้าให้เข้ากันอย่างดีและนำเครื่องธัญบูชาที่หัก6:21 ในภาษาฮีบรูคำนี้มีความหมายไม่ชัดเจนเป็นชิ้นๆ นี้มาถวาย เป็นกลิ่นหอมที่องค์พระผู้เป็นเจ้าพอพระทัย 22บุตรชายผู้ที่จะสืบทอดตำแหน่งปุโรหิตที่ได้รับการเจิมตั้งต่อจากอาโรนจะเป็นผู้เตรียมเครื่องถวายนี้ นี่เป็นส่วนที่ถวายแด่องค์พระผู้เป็นเจ้าเป็นประจำและจะต้องเผาให้หมด 23ธัญบูชาของปุโรหิตทุกอย่างจะต้องเผาให้หมด ห้ามกิน”

เครื่องบูชาไถ่บาป

24องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 25“จงบอกอาโรนและบรรดาบุตรชายว่า ‘ต่อไปนี้เป็นกฎระเบียบเกี่ยวกับเครื่องบูชาไถ่บาปคือ จะต้องนำเครื่องบูชาไถ่บาปมาฆ่าต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้าในที่สำหรับฆ่าสัตว์เป็นเครื่องเผาบูชา เครื่องบูชาไถ่บาปนี้คือของบริสุทธิ์ที่สุด 26ปุโรหิตผู้ประกอบพิธีจะกินเครื่องบูชานี้ในที่บริสุทธิ์ คือในลานเต็นท์นัดพบ 27สิ่งใดก็ตามที่แตะต้องเนื้อนั้นจะบริสุทธิ์ และหากเลือดกระเซ็นไปเปื้อนเสื้อผ้า จะต้องซักในที่บริสุทธิ์ 28จะต้องทุบหม้อดินเผาซึ่งใช้ต้มเนื้อนั้นทิ้ง หรือหากใช้ภาชนะทองสัมฤทธิ์ต้ม ก็ต้องขัดและล้างน้ำ 29ผู้ชายทุกคนในครอบครัวปุโรหิตเท่านั้นที่กินเครื่องบูชานี้ได้ เพราะเป็นของบริสุทธิ์ที่สุด 30อย่ากินเครื่องบูชาไถ่บาปซึ่งเลือดของมันถูกนำเข้าไปในเต็นท์นัดพบเพื่อทำการลบบาปในวิสุทธิสถาน แต่จะต้องเผาทิ้ง