ዘሌዋውያን 3 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 3:1-17

የኅብረት መሥዋዕት

1“ ‘ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ቍርባን ከላሞች መንጋ የሚቀርብ የኅብረት መሥዋዕት3፥1 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል፤ እንዲሁም 3፡6፡9 ይመ። ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ። 2በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት። 3ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣ 4ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ፣ ከኵላሊቶቹ ጋር አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ። 5የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።

6“ ‘ከበግ ወይም ከፍየሉ መንጋ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት ያቅርብ። 7መሥዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነም፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያምጣው፤ 8በጠቦቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት። 9ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ ሥቡን፣ እስከ ጀርባ ዐጥንቱ ድረስ የተቈረጠ ላቱን በሙሉ፣ የሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣ 10ሁለቱን ኵላሊቶች፣ ኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋር አብሮ አውጥቶ ያቅርብ። 11ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።

12“ ‘መሥዋዕቱ ፍየል ከሆነ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ፤ 13በራሱም ላይ እጁን ይጫንበት፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት። 14ከሚያቀርበውም መሥዋዕት ላይ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያቅርብ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣ 15ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ፣ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋር አብሮ አውጥቶ ያቅርብ። 16ካህኑም ይህን ሁሉ በእሳት የሚቀርብና ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ሥብ ሁሉ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።

17“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”

New International Version

Leviticus 3:1-17

The Fellowship Offering

1“ ‘If your offering is a fellowship offering, and you offer an animal from the herd, whether male or female, you are to present before the Lord an animal without defect. 2You are to lay your hand on the head of your offering and slaughter it at the entrance to the tent of meeting. Then Aaron’s sons the priests shall splash the blood against the sides of the altar. 3From the fellowship offering you are to bring a food offering to the Lord: the internal organs and all the fat that is connected to them, 4both kidneys with the fat on them near the loins, and the long lobe of the liver, which you will remove with the kidneys. 5Then Aaron’s sons are to burn it on the altar on top of the burnt offering that is lying on the burning wood; it is a food offering, an aroma pleasing to the Lord.

6“ ‘If you offer an animal from the flock as a fellowship offering to the Lord, you are to offer a male or female without defect. 7If you offer a lamb, you are to present it before the Lord, 8lay your hand on its head and slaughter it in front of the tent of meeting. Then Aaron’s sons shall splash its blood against the sides of the altar. 9From the fellowship offering you are to bring a food offering to the Lord: its fat, the entire fat tail cut off close to the backbone, the internal organs and all the fat that is connected to them, 10both kidneys with the fat on them near the loins, and the long lobe of the liver, which you will remove with the kidneys. 11The priest shall burn them on the altar as a food offering presented to the Lord.

12“ ‘If your offering is a goat, you are to present it before the Lord, 13lay your hand on its head and slaughter it in front of the tent of meeting. Then Aaron’s sons shall splash its blood against the sides of the altar. 14From what you offer you are to present this food offering to the Lord: the internal organs and all the fat that is connected to them, 15both kidneys with the fat on them near the loins, and the long lobe of the liver, which you will remove with the kidneys. 16The priest shall burn them on the altar as a food offering, a pleasing aroma. All the fat is the Lord’s.

17“ ‘This is a lasting ordinance for the generations to come, wherever you live: You must not eat any fat or any blood.’ ”