ዘሌዋውያን 22 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 22:1-33

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“እስራኤላውያን ቀድሰው ለእኔ የለዩትን ቅዱስ መሥዋዕት በአክብሮት ባለመያዝ፣ ቅዱስ ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

3“እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው፣ እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለይተው ወዳቀረቡት ቅዱስ መሥዋዕት ቢቀርብ ያ ሰው ከፊቴ ይወገድ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

4“ ‘ከአሮን ዘር ተላላፊ የቈዳ በሽታ22፥4 በትውፊት ለምጽ ይባላል፤ የዕብራይስጡ ቃል ለምጽ ብቻ ሳይሆን ከቈዳ ጋር የተያያዘ በሽታን ያመለክታል ያለበት ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ማንኛውም ሰው እስኪነጻ ድረስ ቅዱሱን መሥዋዕት አይብላ፤ እንዲሁም በአስከሬን የረከሰውን ነገር ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበትን ሰው ቢነካ፣ 5ወይም በደረቱ የሚሳብ የሚያረክስ ነገርን ወይም የሚያረክስ ማንኛውንም ሰው ቢነካ፣ የቱንም ዐይነት ርኩሰት ቢሆን፣ 6እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ነገር የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ሰውነቱንም በውሃ ካልታጠበ፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ። 7ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ የተቀደሰውን መሥዋዕት መብላት ይችላል፤ ምግቡ ነውና። 8እንዳይረክስ ማንኛውንም ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

9“ ‘ካህናት ትእዛዞቼን በመናቅ በደለኛ እንዳይሆኑና እንዳይሞቱ ይጠብቋቸው፤ የምቀድሳቸው22፥9 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያቸው፤ እንዲሁም 16 ይመ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

10“ ‘ከካህን ቤተ ሰብ በቀር የካህኑ እንግዳም ሆነ ቅጥር ሠራተኛ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ። 11ነገር ግን ካህኑ በገንዘብ የገዛው ወይም በቤቱ የተወለደ ባሪያ ቢኖረው፣ ያ ባሪያ ከካህኑ ድርሻ መብላት ይችላል። 12የካህን ልጅ፣ ካህን ያልሆነ ሌላ ሰው ካገባች፣ ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አትችልም። 13ይሁን እንጂ የካህኑ ልጅ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታ፣ ልጆችም ባይኖሯትና እንደ ልጅነት ጊዜዋ በአባቷ ቤት ለመኖር ብትመለስ፣ ከአባቷ ድርሻ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ሰው ግን ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አይችልም።

14“ ‘ማንኛውም ሰው ባለማወቅ የተቀደሰውን መሥዋዕት ቢበላ፣ የመሥዋዕቱን አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይተካ። 15እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያቀርቡትን የተቀደሰ መሥዋዕት ካህናቱ አያርክሱት፤ 16ይህንኑ የተቀደሰ መሥዋዕት እንዲበሉና ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽሙ አያድርጉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

ለእግዚአብሔር መቅረብ የማይገባው መሥዋዕት

17እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18“ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ከእናንተ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ቢሆን፣ 19መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲኖረው ከላም ወገን ወይም ከበጎች ወይም ከፍየሎች እንከን የሌለበትን ተባዕት ያቅርብ። 20እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ፤ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት አይኖረውምና። 21ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት22፥21 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል። ሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና ነውር የሌለበትን ያቅርብ። 22ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም ማንኛውንም ዐይነት እከክ ወይም ቋቍቻ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አታቅርቡ፤ ከእነዚህ መካከል የትኛውንም በመሠዊያው ላይ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አታቅርቡ። 23አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ22፥23 የዕብራይስጡ ቃል ተባዕትና እንስትን ሊያጠቃልል ይችላል። ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም። 24አባለዘሩ የተቀጠቀጠ ወይም የተኰላሸ፣ የተሰነጠቀ ወይም የተቈረጠ ማንኛውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አታቅርቡ፤ እነዚህንም በምድራችሁ አትሠዉ። 25እንደነዚህ ያሉትን እንስሳት ከባዕዳን በመቀበል ለአምላካችሁ (ኤሎሂም) ምግብ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ ነውር ስላለባቸው ፍጹም አይደሉምና ተቀባይነት አይኖራቸውም።’ ”

26እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 27“ጥጃ ወይም የበግ ግልገል ወይም የፍየል ግልገል በሚወለድበት ጊዜ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቈይ፤ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ግን ተቀባይነት ያለው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል። 28ላምን ከጥጃዋ፣ በግንም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ።

29ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምስጋና መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጋችሁ አቅርቡት። 30መሥዋዕቱ በዚያኑ ዕለት ይበላ፤ ለሚቀጥለውም ቀን አታሳድሩ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

31“ትእዛዞቼን ጠብቁ፤ አድርጓቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ። 32ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ቅዱስ መሆኔ በእስራኤላውያን ዘንድ ይታወቅ፤ የምቀድሳችሁ22፥32 ወይም የቀደስኋችሁ22፥32 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ። 33አምላካችሁ (ኤሎሂም) እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።”

New International Version – UK

Leviticus 22:1-33

1The Lord said to Moses, 2‘Tell Aaron and his sons to treat with respect the sacred offerings the Israelites consecrate to me, so that they will not profane my holy name. I am the Lord.

3‘Say to them: “For the generations to come, if any of your descendants is ceremonially unclean and yet comes near the sacred offerings that the Israelites consecrate to the Lord, that person must be cut off from my presence. I am the Lord.

4‘ “If a descendant of Aaron has a defiling skin disease22:4 The Hebrew word for defiling skin disease, traditionally translated ‘leprosy’, was used for various diseases affecting the skin. or a bodily discharge, he may not eat the sacred offerings until he is cleansed. He will also be unclean if he touches something defiled by a corpse or by anyone who has an emission of semen, 5or if he touches any crawling thing that makes him unclean, or any person who makes him unclean, whatever the uncleanness may be. 6The one who touches any such thing will be unclean till evening. He must not eat any of the sacred offerings unless he has bathed himself with water. 7When the sun goes down, he will be clean, and after that he may eat the sacred offerings, for they are his food. 8He must not eat anything found dead or torn by wild animals, and so become unclean through it. I am the Lord.

9‘ “The priests are to perform my service in such a way that they do not become guilty and die for treating it with contempt. I am the Lord, who makes them holy.

10‘ “No-one outside a priest’s family may eat the sacred offering, nor may the guest of a priest or his hired worker eat it. 11But if a priest buys a slave with money, or if slaves are born in his household, they may eat his food. 12If a priest’s daughter marries anyone other than a priest, she may not eat any of the sacred contributions. 13But if a priest’s daughter becomes a widow or is divorced, yet has no children, and she returns to live in her father’s household as in her youth, she may eat her father’s food. No unauthorised person, however, may eat it.

14‘ “Anyone who eats a sacred offering by mistake must make restitution to the priest for the offering and add a fifth of the value to it. 15The priests must not desecrate the sacred offerings the Israelites present to the Lord 16by allowing them to eat the sacred offerings and so bring upon them guilt requiring payment. I am the Lord, who makes them holy.” ’

Unacceptable sacrifices

17The Lord said to Moses, 18‘Speak to Aaron and his sons and to all the Israelites and say to them: “If any of you – whether an Israelite or a foreigner residing in Israel – presents a gift for a burnt offering to the Lord, either to fulfil a vow or as a freewill offering, 19you must present a male without defect from the cattle, sheep or goats in order that it may be accepted on your behalf. 20Do not bring anything with a defect, because it will not be accepted on your behalf. 21When anyone brings from the herd or flock a fellowship offering to the Lord to fulfil a special vow or as a freewill offering, it must be without defect or blemish to be acceptable. 22Do not offer to the Lord the blind, the injured or the maimed, or anything with warts or festering or running sores. Do not place any of these on the altar as a food offering presented to the Lord. 23You may, however, present as a freewill offering an ox22:23 The Hebrew word can include both male and female. or a sheep that is deformed or stunted, but it will not be accepted in fulfilment of a vow. 24You must not offer to the Lord an animal whose testicles are bruised, crushed, torn or cut. You must not do this in your own land, 25and you must not accept such animals from the hand of a foreigner and offer them as the food of your God. They will not be accepted on your behalf, because they are deformed and have defects.” ’

26The Lord said to Moses, 27‘When a calf, a lamb or a goat is born, it is to remain with its mother for seven days. From the eighth day on, it will be acceptable as a food offering presented to the Lord. 28Do not slaughter a cow or a sheep and its young on the same day.

29‘When you sacrifice a thank-offering to the Lord, sacrifice it in such a way that it will be accepted on your behalf. 30It must be eaten that same day; leave none of it till morning. I am the Lord.

31‘Keep my commands and follow them. I am the Lord. 32Do not profane my holy name, for I must be acknowledged as holy by the Israelites. I am the Lord, who made you holy 33and who brought you out of Egypt to be your God. I am the Lord.’