ዘሌዋውያን 10 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 10:1-20

የናዳብና የአብዩድ መሞት

1የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው ፍም አደረጉባቸው፤ ዕጣንም ጨመሩባቸው፤ እርሱ ያላዘዛቸውን፣ ያልተፈቀደውን እሳት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አቀረቡ። 2ከዚህም የተነሣ እሳት ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ወጥቶ በላቸው፤ በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ሞቱ። 3ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ)

“ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡት መካከል፣

ቅድስናዬን እገልጣለሁ፤

በሕዝቡም ሁሉ ፊት፣

እከበራለሁ’

ብሎ የተናገረው ይህን ነው።” አሮንም ዝም አለ።

4ሙሴ የአሮንን አጎት የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ፣ “ወደዚህ ኑና ወንድሞቻችሁን አንሡ፤ ከመቅደሱም ደጃፍ አርቃችሁ፣ ከሰፈር ወደ ውጭ ውሰዷቸው” አላቸው። 5እነርሱም መጥተው ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት፣ ሟቾቹ የክህነት ቀሚሳቸውን እንደ ለበሱ ተሸክመው ከሰፈር ወደ ውጭ አወጧቸው።

6ሙሴም አሮንንና የአሮንን ልጆች፣ አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “እንዳትሞቱ፣ በሕዝቡም ላይ ቍጣ እንዳይመጣ ጠጕራችሁን አትንጩ፤10፥6 ወይም አትላጩ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ስላጠፋቸው ሰዎች ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ሊያለቅሱላቸው ይችላሉ። 7የእግዚአብሔር (ያህዌ) የመቅቢያ ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን አትውጡ።” እነርሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ።

8እግዚአብሔርም (ያህዌ) አሮንን እንዲህ አለው፤ 9“እንዳትሞቱ አንተና ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን በምትገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም በልጅ ልጃችሁ ዘንድ የሚጠበቅ ዘላለማዊ ሥርዐት ነው። 10የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን፣ ርኩሱንና ንጹሑን ለዩ፤ 11እግዚአብሔርም (ያህዌ) በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውን ሥርዐት ሁሉ ለእስራኤላውያን አስተምሩ።”

12ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ያለ እርሾ ጋግሩት፤ እጅግ ቅዱስ ስለሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት። 13ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት ያንተና የልጆችህ ድርሻ ይህ ስለሆነ፣ በተቀደሰ ስፍራ ብሉት፤ እንዲህ ታዝዣለሁና። 14ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት10፥14 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል ላይ የእናንተ ድርሻ ሆኖ ስለ ተሰጠ፣ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ብሉት። 15የቀረበውን ወርችና የተወዘወዘውን ፍርምባ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት ሆኖ በእሳት ከቀረበው ሥብ ጋር ይምጣ። ይህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።”

16ሙሴ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበውን ፍየል አጥብቆ ፈለገ፤ መቃጠሉንም በተረዳ ጊዜ የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ 17“የኀጢአት መሥዋዕቱን ለምን በተቀደሰው ስፍራ አልበላችሁትም? እጅግ የተቀደሰ ነው፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ስርየት በማስገኘት የሕዝቡን ኀጢአት እንድታስወግዱበት የተሰጣችሁ ነበር፤ 18ደሙ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ስላልገባ፣ በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት ፍየሉን በተቀደሰው ስፍራ መብላት ይገባችሁ ነበር።”

19አሮንም ሙሴን፣ “እነሆ፤ በዛሬው ቀን የኀጢአት መሥዋዕታቸውንና የሚቃጠል መሥዋዕታቸውን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አቀረቡ፤ እኔም እንዲህ ያለ ነገር የደረሰብኝ ሰው ነኝ፤ ታዲያ፣ ዛሬ የኀጢአት መሥዋዕቱን ብበላ ኖሮ እግዚአብሔርስ (ያህዌ) ደስ ይለው ኖሯልን?” አለው። 20ሙሴም ይህን በሰማ ጊዜ መልሱ አረካው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

利未記 10:1-20

拿答和亞比戶之死

1亞倫的兒子拿答亞比戶各拿自己的香爐,點火加香,在耶和華面前獻上凡火。他們這樣做不合耶和華的吩咐。 2於是,有火從耶和華面前出來吞噬了他們,他們就死在耶和華面前。 3摩西告訴亞倫:「耶和華曾說過,『我要在事奉我的人10·3 事奉我的人」希伯來文是「靠近我的人」。中顯明我的聖潔,在所有子民面前彰顯我的榮耀。』」亞倫默默無言。 4摩西叫來亞倫的叔父烏薛的兒子米沙利以利撒反,對他們說:「過來,把你們弟兄的屍體從聖所前抬到營外去。」 5他們就遵照摩西的吩咐,把仍穿著內袍的屍體抬到營外。 6摩西亞倫和他剩下的兩個兒子以利亞撒以他瑪說:「你們不要蓬頭散髮,也不要撕裂衣服,免得你們死亡,也免得耶和華向全體會眾發怒。不過,你們的所有以色列同胞都可以為耶和華用火燒死的人哀傷。 7你們不可走出會幕門口,否則你們都會死,因為耶和華的膏油在你們身上。」他們就遵照摩西的話去做。

有關祭司的條例

8耶和華對亞倫說: 9「你和你兒子們進會幕前,淡酒烈酒都不可喝,否則你們都會死。你們世世代代都要遵守這永遠的條例。 10你們必須明辨什麼是聖潔的、什麼是世俗的,什麼是潔淨的、什麼是不潔淨的。 11你們必須將我藉摩西賜給以色列人的一切律例教導他們。」

12摩西亞倫及其兩個兒子以利亞撒以他瑪說:「你們要把獻給耶和華的火祭中剩下的素祭做成無酵餅,在壇邊吃,因為這是至聖之物。 13你們要在聖潔之處吃,因為在獻給耶和華的火祭中,這是你們和你們的子孫應得之份。這是耶和華對我的吩咐。 14至於作搖祭的胸肉和作舉祭的腿肉,你們和你們的子孫可以在潔淨的地方吃。因為在以色列人所獻的平安祭中,這是你們應得之份。 15在獻火祭的脂肪時,要把作舉祭的腿肉和作搖祭的胸肉一起帶到耶和華面前,這些永遠是你們和你們的子孫應得之份,正如耶和華的吩咐。」

16摩西到處尋找那隻作贖罪祭的公山羊,卻發現那隻羊已經被焚燒了。他憤怒地對亞倫剩下的兩個兒子以利亞撒以他瑪說: 17「你們為什麼不在聖潔之處吃這贖罪祭?這是至聖之物,耶和華賜給你們是要叫你們為會眾擔罪,在耶和華面前為他們贖罪。 18既然這祭牲的血沒有被帶進聖所,你們本應按照我的吩咐在聖潔之處吃這祭肉。」 19亞倫摩西說:「看啊,他們今天向耶和華獻贖罪祭和燔祭,卻有這樣的災禍發生在我身上。今天我如果吃了這贖罪祭的祭肉,耶和華會悅納嗎?」 20摩西亞倫的回答感到滿意。