ዕብራውያን 8 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 8:1-13

የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት

1እንግዲህ የምንናገረው ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ 2እርሱም በሰው ሳይሆን በጌታ በተተከለችው፣ እውነተኛ ድንኳን በሆነችው ቤተ መቅደስ አገልጋይ ነው።

3እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት የሚሾመው መባንና መሥዋዕትን ለማቅረብ ነው፤ ስለዚህ ይህኛውም ሊቀ ካህን የሚያቀርበው ነገር ያስፈልገዋል። 4እርሱ በምድር ቢኖር ኖሮ ካህን ባልሆነም ነበር፤ ምክንያቱም በሕግ በታዘዘው መሠረት መባን የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ። 5እነርሱ ያገለገሉት በሰማይ ላለችው መቅደስ ምሳሌና ጥላ በሆነችው ውስጥ ነው፤ ሙሴ ድንኳኒቱን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ፣ “በተራራው ላይ በተገለጠልህ ምሳሌ መሠረት ሁሉን ነገር እንድታደርግ ተጠንቀቅ” የሚል ትእዛዝ የተሰጠው በዚህ ምክንያት ነበር። 6ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው።

7የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጕድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። 8ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጕድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል8፥8 አንዳንድ የጥንት ቅጆች ጕድለት በማግኘቱ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸዋል

“ከእስራኤል ቤት ጋር፣

ከይሁዳም ቤት ጋር፣

አዲስ ኪዳን የምገባበት፣

ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ።

9ይህም እነርሱን ከግብፅ ምድር

ለማውጣት እጃቸውን በያዝሁ ጊዜ፣

ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ኪዳን አይደለም፤

ምክንያቱም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑም፤

እኔም ከእነርሱ ዘወር አልሁ፤

ይላል ጌታ።

10ከዚያን ጊዜ በኋላ፣

ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤

ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤

በልባቸውም እጽፈዋለሁ።

እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤

እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

11ከእንግዲህ ማንም ሰው ጎረቤቱን

ወይም ወንድሙን፣ ‘ጌታን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤

ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ፣

ሁሉም ያውቁኛል።

12በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውን

ከእንግዲህ አላስብም።”

13ይህን ኪዳን፣ “አዲስ” በማለቱ የፊተኛውን ኪዳን አሮጌ አድርጎታል፤ ስለዚህ ያረጀ ያፈጀው የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።

King James Version

Hebrews 8:1-13

1Now of the things which we have spoken this is the sum: We have such an high priest, who is set on the right hand of the throne of the Majesty in the heavens; 2A minister of the sanctuary, and of the true tabernacle, which the Lord pitched, and not man. 3For every high priest is ordained to offer gifts and sacrifices: wherefore it is of necessity that this man have somewhat also to offer. 4For if he were on earth, he should not be a priest, seeing that there are priests that offer gifts according to the law: 5Who serve unto the example and shadow of heavenly things, as Moses was admonished of God when he was about to make the tabernacle: for, See, saith he, that thou make all things according to the pattern shewed to thee in the mount. 6But now hath he obtained a more excellent ministry, by how much also he is the mediator of a better covenant, which was established upon better promises. 7For if that first covenant had been faultless, then should no place have been sought for the second. 8For finding fault with them, he saith, Behold, the days come, saith the Lord, when I will make a new covenant with the house of Israel and with the house of Judah: 9Not according to the covenant that I made with their fathers in the day when I took them by the hand to lead them out of the land of Egypt; because they continued not in my covenant, and I regarded them not, saith the Lord. 10For this is the covenant that I will make with the house of Israel after those days, saith the Lord; I will put my laws into their mind, and write them in their hearts: and I will be to them a God, and they shall be to me a people: 11And they shall not teach every man his neighbour, and every man his brother, saying, Know the Lord: for all shall know me, from the least to the greatest. 12For I will be merciful to their unrighteousness, and their sins and their iniquities will I remember no more. 13In that he saith, A new covenant, he hath made the first old. Now that which decayeth and waxeth old is ready to vanish away.