ዕብራውያን 13 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 13:1-25

የመጨረሻ ምክር

1እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች ተዋደዱ። 2እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ፣ ሳያውቁ መላእክትን አስተናግደዋልና። 3በእስር ላይ ያሉትን ከእነርሱ ጋር እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ አስቧቸው፤ እንዲሁም በሰው እጅ የሚንገላቱትን ራሳችሁ መከራ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ አስቧቸው።

4ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአመንዝሮችና በሴሰኞች ሁሉ ላይ ይፈርዳል። 5ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣

“ከቶ አልተውህም፤

በፍጹም አልጥልህም” ብሏል።

6ስለዚህ በሙሉ ልብ፣

“ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤

ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።

7የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፤ የኑሯቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው። 8ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።

9በልዩ ልዩ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን የሚጸናው በጸጋ እንጂ የምግብ ሥርዐት በመጠበቅ አይደለም፤ ይህን ሥርዐት የሚጠብቁት እንኳ በዚህ አልተጠቀሙም። 10በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን።

11ሊቀ ካህናቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚሆነውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል። 12እንዲሁም ኢየሱስ በራሱ ደም አማካይነት ሕዝቡን ሊቀድስ ከከተማው በር ውጭ መከራን ተቀበለ። 13ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ። 14ምክንያቱም በዚህ ቋሚ ከተማ የለንም፤ ነገር ግን ወደ ፊት የምትመጣዋን ከተማ እንጠብቃለን።

15ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት ይኸውም ለስሙ የሚመስክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ። 16ደግሞም መልካም ማድረግንና ያላችሁንም ከሌሎች ጋር መካፈልን አትርሱ፤ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኘው እንደዚህ ባለው መሥዋዕት ነውና።

17ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።

18ለእኛ ደግሞ ጸልዩልን። በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን ርግጠኞች ነን። 19በተለይም ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ ዐደራ እላችኋለሁ።

20በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ፣ 21ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

22ወንድሞች ሆይ፤ የጻፍሁላችሁ መልእክት ዐጭር እንደ መሆኑ፣ የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ ዐደራ እላችኋለሁ።

23ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ፤ ቶሎ ከመጣ፣ ከእርሱ ጋር ላያችሁ እመጣለሁ።

24ለመሪዎቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

ከኢጣሊያ የሆኑትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

25ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

希伯來書 13:1-25

做上帝喜悅的事

1你們要繼續彼此相愛,情同手足。 2不要忘記款待客旅,因為曾經有人接待客旅時不知不覺接待了天使。 3要設身處地地顧念那些被囚禁的人,要感同身受地顧念那些遭遇苦難的人。

4人人都要尊重婚姻,不可玷污夫妻關係13·4 夫妻關係」希臘文是「婚姻的床」。,因為上帝必審判淫亂和通姦的人。

5不要貪愛錢財,要對自己擁有的知足,因為上帝說過:

「我永不撇下你,也不離棄你。」

6這樣,我們可以放膽地說:

「主是我的幫助,

我必不懼怕,

人能把我怎麼樣?」

7你們要記住從前帶領你們、把上帝的道傳給你們的人,留心觀察他們一生如何行事為人,效法他們的信心。 8耶穌基督昨日、今日、直到永遠都不改變。 9你們不要被五花八門的異端邪說勾引了去,因為心中得到力量是靠上帝的恩典,而不是靠飲食上的禮儀,這些禮儀從未使遵守的人受益。

10我們有一座祭壇,壇上的祭物是那些在聖幕裡工作的人沒有權利吃的。 11大祭司把祭牲的血帶進聖所作為贖罪祭獻上,而祭牲的身體則在營外燒掉。 12同樣,耶穌也在城門外受難,為要用自己的血使祂的子民聖潔。 13因此,讓我們也走出營外到祂那裡,忍受祂所忍受的凌辱吧! 14我們在地上沒有永遠的城,我們尋求的是那將來的城。

15讓我們靠著基督,常常開口以頌讚為祭獻給上帝,這是承認主名的人13·15 承認主名的人」希臘文是「承認主名的嘴唇」。所結的果子。 16不可忘記行善和幫補別人,因為這樣的祭是上帝所喜悅的。

17要順服引導你們的人,因為他們為你們的靈魂時刻警醒,將來要向上帝交帳。你們要聽從他們,使他們滿心喜樂地盡此職責,不致憂愁,否則對你們毫無益處。

18請為我們禱告,因為我們自信良心無愧,凡事都願意遵行正道。 19也請你們特別為我禱告,使我能夠早日回到你們那裡。

祝福與問安

20願賜平安的上帝,就是那位憑著立永恆之約的血使群羊的大牧人——我主耶穌從死裡復活的上帝, 21在各樣善事上成全你們,好使你們遵行祂的旨意,並藉著主耶穌在你們心中動工,使你們做祂喜悅的事!願榮耀歸給上帝,直到永永遠遠。阿們!

22弟兄姊妹,我簡短地寫信給你們,希望你們聽我勸勉的話。 23你們知道,我們的弟兄提摩太已經被釋放了。如果他及時來到,我會與他一起去看你們。

24請代我問候所有帶領你們的人以及眾聖徒。從義大利來的人也問候你們。

25願恩典與你們眾人同在!