ኤፌሶን 4 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤፌሶን 4:1-32

በክርስቶስ አካል ያለ አንድነት

1እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣ ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ። 2ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ። 3በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። 4በተጠራችሁ ጊዜ ወደ አንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ 5አንድ ጌታ፣ አንድ እምነትና አንድ ጥምቀት አለ፤ 6ከሁሉም በላይ የሆነ፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።

7ነገር ግን ክርስቶስ በወሰነው መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል። 8ስለዚህም እንዲህ ይላል፤

“ወደ ላይ በወጣ ጊዜ፣

ምርኮ ማረከ፤

ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ።”

9ታዲያ፣ “ወደ ላይ ወጣ” ማለት ደግሞ ወደ ምድር ታችኛው ክፍል4፥9 ወይም ወደ ምድር ጥልቀት እንደ ብርሃን ልጆች መኖር ወረደ ማለት ካልሆነ በቀር ምን ማለት ነው? 10ወደ ታች የወረደውም፣ መላውን ፍጥረተ ዓለም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው እርሱ ራሱ ነው። 11አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤ 12ይኸውም የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ሲሆን፣ 13ይህም የሚሆነው፣ ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኘው አንድነት በመምጣትና ሙሉ ሰው በመሆን፣ በክርስቶስ ወዳለው ፍጹምነት ደረጃ እስከምንደርስ ነው።

14ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም። 15ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፤ 16ከእርሱም የተነሣ፣ አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፣ እያንዳንዱ ክፍል የራሱን ሥራ እያከናወነ በፍቅር ያድጋል፤ ራሱንም ያንጻል።

እንደ ብርሃን ልጆች መኖር

17ስለዚህ ይህን እነግራችኋለሁ፤ በጌታም ዐደራ እላለሁ፤ በአስተሳሰባቸው ከንቱነት እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ልትመላለሱ አይገባም። 18እነርሱ ከልባቸው መደንደን የተነሣ ስለማያስተውሉ ልቦናቸው ጨልሟል፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ተለይተዋል። 19ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።

20እናንተ ግን ክርስቶስን ያወቃችሁት እንደዚህ ባለ መንገድ አይደለም፤ 21በርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስም እንዳለው እውነት በእርሱ ተምራችኋል። 22ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጐደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ 23ደግሞም በአእምሯችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ 24እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።

25ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና። 26ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤ በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤ 27ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት። 28ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።

29እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ። 30ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ። 31መራርነትን ሁሉ፣ ቍጣና ንዴትን፣ ጭቅጭቅና ስድብን ከማንኛውም ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ። 32እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以弗所书 4:1-32

信徒同属一体

1所以,我这为主被囚禁的劝你们,既然蒙了上帝的呼召,就要过与所蒙的呼召相称的生活。 2凡事要谦虚、温柔、忍耐,用爱心互相宽容, 3以和平彼此联结,竭力持守圣灵所赐的合一。 4正如你们蒙召后有同一个盼望,你们同属一个身体,有同一位圣灵、 5同一位主、同一个信仰、同一种洗礼、 6同一位上帝,就是万物之父。祂超越万物,贯穿万物,且在万物之中。

7然而,我们各人都是按照基督所赐的分量领受恩典。 8因此圣经上说:

“祂升上高天时,

带着许多俘虏,

将恩赐赏给众人。”

9既然说“升上”,岂不表示祂曾经降到地上吗? 10降下的是祂,升到诸天之上的也是祂,祂充满万物。 11祂赐恩让一些人做使徒,一些人做先知,一些人做传福音的,一些人做牧师和教师, 12为要装备信徒,使他们各尽其职,建立基督的身体, 13直到我们对上帝的儿子有一致的信仰和认识,逐渐成熟,达到基督那样完美的生命。 14这样,我们就不再像小孩子,被各种异端邪说之风吹得飘来飘去,被人的阴谋诡计欺骗,随波逐流。 15相反,我们说话要凭爱心坚持真理,在各方面都要追求长进,更像元首基督。 16整个身体靠祂巧妙地结合在一起,筋骨相连,彼此供应,使各部位各尽其职,身体便渐渐长大,在爱中建立起来。

新人新生命

17因此,我奉主的名郑重地劝告各位,不要再像不信的外族人一样过着心灵空虚的日子。 18他们因为愚昧无知,顽固不化,理智受到蒙蔽,与上帝所赐的生命隔绝了。 19他们丧尽天良,放纵情欲,沉溺于各种污秽的事。 20但基督绝不是这样教导你们的。

21如果你们听过祂的事,领受了祂的教诲,就是在祂里面的真理, 22就应该与从前的生活方式一刀两断,脱去因私欲的迷惑而渐渐败坏的旧人, 23洗心革面, 24穿上照着上帝形象所造的新人。这新人有从真理而来的公义和圣洁。

25所以不要再说谎,大家都要彼此说真话,因为我们都是一个身体的肢体。 26不要因生气而犯罪,不要到日落时还怒气未消, 27不要让魔鬼有机可乘。 28从前偷窃的要改过自新,自食其力,做正当事,以便能够分给有需要的人。 29污言秽语一句都不可出口,要随时随地说造就人的好话,使听的人得益处。 30不要让上帝的圣灵担忧,你们已经盖上了圣灵的印记,将来必蒙救赎。 31要从你们当中除掉一切的苦毒、恼恨、怒气、争吵、毁谤和邪恶。 32总要以恩慈、怜悯的心彼此相待,要互相饶恕,正如上帝在基督里饶恕了你们一样。