ኤርምያስ 49 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 49:1-39

ስለ አሞን የተነገረ መልእክት

1ስለ አሞናውያን፤

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እስራኤል ወንዶች ልጆች አልወለደምን?

ወራሾችስ የሉትምን?

ታዲያ፣ ሚልኮምሸ49፥1 ወይም ንጉሣቸው፤ ዕብራይስጡ መልካም ይላል፤ 3 ይመ። ጋድን ለምን ወረሰ?

የእርሱ ሰዎች ለምን በከተሞቿ ይኖራሉ?

2ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣

የጦርነት ውካታ ድምፅ

የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤”

ይላል እግዚአብሔር

“እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤

በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤

እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣

ከአገሯ ታስወጣለች፤”

ይላል እግዚአብሔር

3“ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤

የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤

ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤

ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣

ተማርኮ ይወሰዳልና፣

በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።

4አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤

በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ?

ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ?

በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣

‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ።

5በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣

ሽብር አመጣብሻለሁ፤”

ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

“እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤

በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም።

6“ከዚያ በኋላ ግን፣ የአሞናውያንን ምርኮ እመልሳለሁ”

ይላል እግዚአብሔር

ስለ ኤዶም የተነገረ መልእክት

49፥9-10 ተጓ ምብ – አብ 5-6

49፥14-16 ተጓ ምብ – አብ 1-4

7ስለ ኤዶም፤

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ጥበብ ከቴማን ጠፍቷልን?

ምክር ከአስተዋዮች ርቋልን?

ጥበባቸውስ ተሟጧልን?

8ዔሳውን በምቀጣ ጊዜ፣

ጥፋት ስለማመጣበት፣

እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፤

ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሽሹ፤ ጥልቅ ጕድጓድ ውስጥ ተደበቁ።

9ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣

ጥቂት ወይን አያስቀሩምን?

ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣

የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ብቻ አይደለምን?

10እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤

መደበቅም እንዳይችል፣

መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤

ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤

እርሱም ራሱ አይኖርም።

11ወላጆች የሌላቸውን ልጆችህን ተዋቸው፤ እኔ ለሕይወታቸው እጠነቀቃለሁ፤ መበለቶቻችሁም በእኔ ይታመኑ።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከጽዋው መጠጣት የማይገባቸው ሊጠጡ ግድ ከሆነ፣ አንተ እንዴት ሳትቀጣ ትቀራለህ? መቀጣትህ አይቀርም፤ መጠጣት ይገባሃል። 13ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”

14ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤

“እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤

ለጦርነትም ውጡ”

የሚል መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኳል።

15“እነሆ፤ በሕዝቦች መካከል ታናሽ፣

በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አደርግሃለሁ።

16አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣

የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤

የምትነዛው ሽብር፣

የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤

መኖሪያህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ብትሠራም፣

ከዚያ ወደ ታች እጥልሃለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

17“ኤዶም የድንጋጤ ምልክት ትሆናለች፤

ከቍስሎቿም ሁሉ የተነሣ፣

በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በመደነቅ ያላግጥባታል።

18በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋር፣

ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣”

ይላል እግዚአብሔር

እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤

አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

19“አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣

ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣

እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ።

የመረጥሁትን በእርሱ ላይ እሾማለሁ፤

እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል?

የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”

20ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ ያለውን ዕቅድ፣

በቴማን በሚኖሩትም ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤

ታናናሹ መንጋ ተጐትቶ ይወሰዳል፤

በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።

21በውድቀታቸው ድምፅ ምድር ትናወጣለች፤

ጩኸታቸውም እስከ ቀይ ባሕር49፥21 ዕብራይስጡ ያም ሱፍ ይላል፤ ትርጕሙ የሸንበቆ ባሕር ማለት ነው። ያስተጋባል።

22እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤

ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤

በዚያን ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣

በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

ስለ ደማስቆ የተነገረ መልእክት

23ስለ ደማስቆ፣

“ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣

ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤

እንደ49፥23 ዕብራይስጡ በተናወጠ ይላል። ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤

ልባቸውም ቀልጧል።

24ደማስቆ ተዳከመች፤

ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤

ብርክ ያዛት፣

ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣

ጭንቅና መከራ ዋጣት።

25ደስ የምሰኝባት፣

የታወቀችው ከተማ እንዴት ተተወች?

26በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤

በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”

ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

27“በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤

የወልደ አዴርንም ዐምባ ይበላል።”

ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር የተነገረ መልእክት

28የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤

የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።

29ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤

መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣

ከነዕቃዎቻቸው ይነጠቃሉ፤

ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’

እያሉ ይጮኹባቸዋል።

30በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣

በጥድፊያ ሽሹ፤ በጥልቅ ጕድጓድ ተሸሸጉ፤”

ይላል እግዚአብሔር

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ ጠንክሯልና፣

ወረራም ዶልቶባችኋል።

31“ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣

በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤”

ይላል እግዚአብሔር

“መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤

ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።

32ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤

ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤

ጠጕሩን የሚቀነብበውን ወገን49፥32 ወይም በሩቅ ስፍራ ያለውን

እበትናለሁ፤ ከየአቅጣጫው መዓት አመጣባችኋለው።”

ይላል እግዚአብሔር

33“ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣

ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤

ማንም በዚያ አይኖርም፤

የሚቀመጥባትም አይገኝም።”

ስለ ኤላም የተነገረ መልእክት

34በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

35የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ የኀያልነቷን መሠረት፣

የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።

36ከአራቱ የሰማይ ማእዘናት፣

በኤላም ላይ አራቱን ነፋሳት አመጣለሁ፤

ወደ አራቱም ነፋሳት እበትናቸዋለሁ፤

ከኤላም የሚማረኩት የማይደርሱበት፣

አገር አይገኝም።

37ነፍሳቸውን በሚሹ ጠላቶቻቸው ፊት፣

ኤላምን አርበደብዳለሁ፤

በላያቸው ላይ መዓትን፣

ይኸውም ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

“ፈጽሜ አስካጠፋቸውም ድረስ፣

በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

38ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤

ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

39“ነገር ግን የኋላ ኋላ፣

የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 49:1-39

审判亚扪的预言

1论到亚扪人,耶和华说:

“难道以色列没有子孙,

没有继承人吗?

为什么祭拜米勒公的人占据了迦得,住在城邑中?”

2耶和华说:

“看啊,时候将到,

我要使亚扪人的拉巴城外响起战争的呐喊。

拉巴必沦为废墟,

它周围的乡村都要被焚烧,

以色列人必收复失地。

这是耶和华说的。

3希实本啊,哀哭吧!

因为城毁灭了。

拉巴的居民啊,痛哭吧!

披上麻衣悲伤地在城墙内跑来跑去吧!

因为米勒公及其祭司和官长都要被掳走。

4背叛的人民啊,

你们为肥沃的山谷而感到自豪吗?

你们依仗财富以为无人敢来侵犯。”

5上帝——万军之耶和华说:

“看啊,我要使你们四面受敌,

惊恐万状,四散奔逃,

溃不成军。

6然而,日后我要使被掳的亚扪人重建家园。

这是耶和华说的。”

审判以东的预言

7论到以东,万军之耶和华说:

提幔再没有智者了吗?

谋士已无计可施了吗?

他们都失去智慧了吗?

8底但的居民啊,

你们要转身逃命,

藏在深洞里,

因为我必降灾祸惩罚以东

9人们来以东摘葡萄,不会摘尽;

盗贼夜间来偷东西,不会偷光。

10但我要夺走以东人所有的一切,

我要使他们无处藏身。

他们及其孩子、弟兄和邻居必一同灭亡。

11撇下你们的孤儿吧!

我必使他们存活;

你们的寡妇也可以倚靠我。”

12耶和华说:“看啊,那些本不该喝这杯愤怒的人尚且要喝,更何况你们呢?你们必难逃惩罚,你们一定要喝这杯愤怒。 13因为我已凭自己起誓,波斯拉必沦为废墟,令人惊惧,被人嘲笑和咒诅。它周围的村镇要永远荒凉。这是耶和华说的。”

14我从耶和华那里听到消息,

有位使者被派去联合列国来攻打以东

15耶和华说:

以东啊,我要使你在列国中成为被藐视的弱国。

16你这栖身在石缝间、盘踞在高山上的民族啊,

你令人惊惧、心高气傲,

其实只是自欺。

尽管你像老鹰在高处搭窝,

我也必把你拉下来。

这是耶和华说的。

17以东的下场将很可怕,它的满目疮痍令路人惊惧、嗤笑。 18那里要像所多玛蛾摩拉及其周围的村镇一样被毁灭,荒无人烟。这是耶和华说的。 19看啊,我必在瞬间把以东人赶离家园,如约旦河边丛林中跳出的狮子赶散草场的羊群。我要派我拣选的人统治这地方。谁能与我相比?谁能与我较量?哪位首领能抵挡我?” 20因此,你们要听听耶和华攻击以东的策略,听听祂攻击提幔居民的计划。他们的孩子要被拖走,他们的家园要被毁灭。 21以东倾覆的声音震动大地,哭喊声直传到海。 22看啊,敌人必像展翅飞来的鹰一样攻击波斯拉。到那日,以东的勇士必像临盆的妇女一样胆战心惊。

审判大马士革的预言

23论到大马士革,耶和华说:

哈马亚珥拔惊恐不安,

因为他们听见了坏消息。

他们心惊胆战,像大海一样无法平静。

24大马士革丧失勇气,转身逃命。

她像分娩的妇人一样惊恐不安,

充满痛苦和忧愁。

25我所喜悦的名城为何还没有被撇弃?

26城中的青年将倒毙街头,

那时所有的战士都要灭亡。

这是万军之耶和华说的。

27我要焚烧大马士革的城墙和便·哈达的宫殿。”

审判基达和夏琐的预言

28论到被巴比伦尼布甲尼撒打败的基达夏琐的各城邦,耶和华说:

迦勒底人啊,去攻打基达

消灭那些东方人吧!

29你们要抢走他们的帐篷、

幔子、器皿、羊群和骆驼。

他们必听见呼喊声,

‘真恐怖!四面都是敌人。’

30夏琐的居民啊,快逃命吧!

逃得远远的藏起来,

因为巴比伦尼布甲尼撒已计划攻击你们,

准备消灭你们。

这是耶和华说的。

31迦勒底人啊,

上去攻打那安逸无忧、无门无闩、独居一方的国家吧!

这是耶和华说的。

32他们的骆驼必被掳去,

大群的牲畜必成为战利品。

我要把剃去鬓发的人驱散到四方,

使灾祸从四面八方临到他们。

这是耶和华说的。

33夏琐要永远荒凉,

杳无人迹,

成为豺狼出没的地方。”

审判以拦的预言

34犹大西底迦执政初期,耶和华告诉了耶利米先知有关以拦的事。 35万军之耶和华说:“看啊,我要摧毁以拦的弓箭手——他们的精锐之师。 36我要使敌人从四面八方如风而来,把以拦人驱散到四方,使他们流落到列国。 37我要让仇敌击溃他们,我要发烈怒降祸给他们,用刀剑追杀他们,直到彻底消灭他们。这是耶和华说的。 38我要在以拦设立我的宝座,消灭那里的君王和官长。这是耶和华说的。 39但将来有一天,我要使被掳的以拦人重建家园。这是耶和华说的。”