ኤርምያስ 47 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 47:1-7

ስለ ፍልስጥኤማውያን የተነገረ መልእክት

1ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤

ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤

አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣

ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል።

ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤

የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤

3ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣

ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና

ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣

አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤

እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።

4ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣

ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣

ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣

ቀኑ ደርሷልና።

እግዚአብሔር በከፍቶር47፥4 ቀርጤስ ነው ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ

ተነሥቷል።

5ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፤

አስቀሎና አፏን ትይዛለች።

በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ቅሬታዎች ሆይ፤

እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?

6“ ‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤

የማታርፈው እስከ መቼ ነው?

ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤

ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።

7ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣

እንዲወጋ ሲያዝዘው፣

እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣

እንዴት ማረፍ ይችላል?”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 47:1-7

关于非利士的预言

1在法老攻打迦萨之前,耶和华告诉了耶利米先知有关非利士人的事。

2耶和华说:

“看啊,大水将从北方涨溢,

形成一道洪流,

淹没大地和地上的一切,

吞噬城邑和其中的居民。

人们必呼喊,

地上的居民必哀哭。

3一听见马蹄嗒嗒、

战车隆隆、车轮滚滚的声音,

做父亲的就吓得手脚发软,

无力照顾儿女。

4因为毁灭所有非利士人的日子到了,

铲除泰尔西顿剩余帮手的日子到了。

耶和华要灭绝迦斐托岛剩余的非利士人。

5迦萨一片荒凉,

亚实基伦沦为废墟。

谷中的余民啊!

你们要割伤身体到何时呢?

6你们大喊,‘耶和华的刀啊,

你何时才停下来呢?

求你入鞘吧!停下来吧!’

7但耶和华已命令它攻击亚实基伦和沿海一带,

它怎能停下来呢?”