ኤርምያስ 44 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 44:1-30

ጣዖትን ማምለክ ያስከተለው ጥፋት

1በግብፅ ሰሜናዊ ክፍል በሚግዶል፣ በጣፍናስና በሜምፎስ44፥1 ዕብራይስጡ ኖፍ ይላል። እንዲሁም በግብፅ ደቡባዊ ክፍል44፥1 ዕብራይስጡ ከጳትሮስ ይላል። ስለሚኖሩት የአይሁድ ሕዝብ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 2“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ታላቅ ጥፋት አይታችኋል፤ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ ሆነው ይታያሉ፤ 3ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል። 4እኔም፣ ‘ይህን የምጠላውን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ’ በማለት አገልጋዮቼን ነቢያትን ደጋግሜ ላክሁባቸው። 5እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብም አላሉም፤ ከክፋታቸው አልተመለሱም፤ ለሌሎችም አማልክት ማጠን አልተውም። 6ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ነደደ፤ ዛሬ እንደሚታዩትም ማንም የማይኖርባቸው ፍርስራሾች አደረጋቸው።

7“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ዘር እንዳይቀርላችሁ ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት በይሁዳ እንዳይገኙ ለምን እንዲህ ዐይነት ታላቅ ጥፋት በራሳችሁ ላይ ታመጣላችሁ? 8ልትኖሩባት በመጣችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠን፣ እጆቻችሁ ባበጇቸው ነገሮች ለምን ታስቈጡኛላችሁ? በምድር ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የርግማንና የመዘባበቻ ምልክት ለመሆን ራሳችሁን ታጠፋላችሁን? 9በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም መንገዶች አባቶቻችሁ የይሁዳ ነገሥታትና ሚስቶቻቸው፣ እንዲሁም እናንተና ሚስቶቻችሁ ያደረጋችሁትን ክፋት ረስታችሁታልን? 10እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ክብርን አልሰጡኝም፤ በእናንተና በአባቶቻችሁ ፊት ያኖርሁትንም ሕጌንና ሥርዐቴን አልተከተሉም።’

11“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቈርጬ ተነሥቻለሁ። 12ሄደው በግብፅ ለመቀመጥ የወሰኑትን የይሁዳ ቅሬታዎች ሁሉ እነጥቃለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅ ምድር በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በራብ ያልቃሉ፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ይሆናሉ። 13ኢየሩሳሌምን እንደ ቀጣሁ፣ በግብፅ የሚኖሩትን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እቀጣለሁ፤ 14ወደ ግብፅ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በስተቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ”

15ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ወንዶች ሁሉና በዚያ የነበሩት ሴቶች ሁሉ ይህም ማለት በሰሜንና በደቡብ ግብፅ44፥15 ዕብራይስጡ በግብፅና በጳጥሮስ ይላል። የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ እንዲህ አሉት፤ 16“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን መልእክት አንሰማም፤ 17እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለ ሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስስላታለን። በዚያን ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም። 18ነገር ግን ለሰማይዋ ንግሥት ማጠንና የመጠጥ ቍርባን ማፍሰስ ከተውን ወዲህ ሁሉን ነገር ዐጥተናል፤ በሰይፍና በራብም እያለቅን ነው።”

19ሴቶቹም፣ “ለሰማይዋ ንግሥት በምናጥንበትና የመጠጥ ቍርባን በምናፈስስበት ጊዜ፣ በምስሏ ዕንጐቻ ስንጋግርና የመጠጥ ቍርባን ስናፈስስላት ባሎቻችን አያውቁም ነበርን?” አሉ።

20ኤርምያስ ይህን መልስ ለሰጠው ሕዝብ፣ ለወንዶችና ለሴቶች ሁሉ እንዲህ አለ፤ 21“እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁና ባለሥልጣኖቻችሁ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ያጠናችሁትን እግዚአብሔር የማያስታውሰውና የዘነጋው ይመስላችኋልን? 22እግዚአብሔር ክፉ አድራጎታችሁንና አስጸያፊ ተግባራችሁን ሊታገሥ ባለመቻሉ፣ ዛሬ እንደ ሆነው ምድራችሁ የርግማን ምልክትና ሰው የማይኖርበት ባዶ ምድረ በዳ ሆኗል። 23ዕጣን በማጠን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና ቃሉን ስላልጠበቃችሁ ሕጉን፣ ሥርዐቱንና ትእዛዙን ስላላከበራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ጥፋት መጥቶባችኋል።”

24ኤርምያስም ለሕዝቡና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በግብፅ የምትኖሩ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 25የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተና ሚስቶቻችሁ፣ “ለሰማይዋ ንግሥት ለማጠንና የመጠጥ ቍርባን ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በርግጥ እንፈጽማለን” ብላችሁ የገባችሁትን ቃል በተግባር አሳይታችኋል።’

“እንግዲያውስ ወደ ኋላ አትበሉ፤ ቃል የገባችሁትን፣ ስእለታችሁንም ፈጽሙ። 26በግብፅ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብፅ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤ 27ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብፅ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ። 28ከሰይፍ አምልጠው፣ ከግብፅ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመለሱት በጣም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። በግብፅ ምድር ለመኖር የመጡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ፣ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማንኛችን ቃል እንደሚጸና ያውቃሉ።

29“ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር30እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ሊገድለው ለፈለገው ጠላቱ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።’ ”

Thai New Contemporary Bible

เยเรมีย์ 44:1-30

ภัยพิบัติเนื่องจากการกราบไหว้รูปเคารพ

1พระดำรัสซึ่งมีมาถึงเยเรมีย์เกี่ยวกับชาวยิวทั้งปวงที่อาศัยอยู่ในอียิปต์ล่าง ที่มิกดล ทาห์ปานเหส เมมฟิส44:1 ภาษาฮีบรูว่าโนฟ และอียิปต์ตอนบน44:1 ภาษาฮีบรูว่าในปัทโรสความว่า 2“พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ พระเจ้าแห่งอิสราเอลตรัสดังนี้ว่า เจ้าได้เห็นภัยพิบัติใหญ่หลวงซึ่งเราได้นำมายังเยรูซาเล็มและหัวเมืองทั้งปวงของยูดาห์แล้ว ทุกวันนี้ต้องตกอยู่ในสภาพถูกทิ้งร้างและปรักหักพัง 3เพราะความชั่วที่พวกเขาได้ทำ เขายั่วให้เราโกรธโดยเผาเครื่องหอมและนมัสการพระอื่นๆ ซึ่งเขาก็ดี เจ้าก็ดี หรือบรรพบุรุษของเจ้าทั้งหลายก็ดีล้วนไม่เคยรู้จักมาก่อน 4เราส่งผู้เผยพระวจนะผู้รับใช้ของเรามาเตือนเขาครั้งแล้วครั้งเล่าว่า ‘อย่าทำสิ่งที่น่าชิงชังที่เราเกลียดนี้!’ 5แต่เขาก็ไม่ฟังหรือใส่ใจ ไม่ยอมหันกลับจากความชั่วร้าย หรือหยุดเผาเครื่องหอมให้พระต่างๆ 6ฉะนั้นเราจึงเทโทสะเกรี้ยวกราดของเราให้มันโหมกระหน่ำลงมาเหนือหัวเมืองต่างๆ ของยูดาห์ และถนนหนทางในเยรูซาเล็ม และทำให้เมืองเหล่านี้กลายเป็นซากปรักหักพัง ถูกทิ้งร้างเหมือนที่เป็นอยู่ทุกวันนี้”

7“บัดนี้พระยาห์เวห์พระเจ้าผู้ทรงฤทธิ์ พระเจ้าแห่งอิสราเอลตรัสดังนี้ว่า เหตุใดพวกเจ้าจึงนำหายนะมาสู่ตนเองโดยพรากผู้คนทั้งหญิงและชาย ลูกเล็กเด็กแดงมาจากยูดาห์ ทำให้พวกเจ้าไม่เหลือสักหยิบมือเดียว? 8เหตุใดจึงยั่วเราให้โกรธด้วยรูปเคารพที่เจ้าสร้างขึ้น โดยการเผาเครื่องหอมแก่พระอื่นๆ ในแผ่นดินอียิปต์ซึ่งเจ้าได้มาอาศัยอยู่? เจ้าจะทำลายตัวเองและทำตัวให้ตกเป็นเป้าของคำสาปแช่งและเป็นคำเปรียบเปรยในหมู่ประชาชาติทั้งหลายในโลก 9เจ้าลืมความชั่วซึ่งเหล่าบรรพบุรุษและบรรดากษัตริย์กับราชินีแห่งยูดาห์ได้ทำแล้วหรือ? ตลอดจนความชั่วของเจ้าเองกับภรรยาในดินแดนยูดาห์และตามถนนหนทางในเยรูซาเล็ม 10จวบจนทุกวันนี้พวกเจ้าไม่ได้ถ่อมกายถ่อมใจ หรือยำเกรง หรือปฏิบัติตามบทบัญญัติและคำบัญชาซึ่งเราตั้งไว้ต่อหน้าเจ้ากับบรรพบุรุษของเจ้า

11“ฉะนั้นพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ พระเจ้าแห่งอิสราเอลตรัสดังนี้ว่าเราตั้งใจจะนำภัยพิบัติมาเหนือเจ้าและทำลายล้างยูดาห์ให้หมดสิ้น 12เราจะลงโทษชนหยิบมือที่เหลือของยูดาห์ซึ่งตั้งใจจะมาตั้งรกรากในอียิปต์นี้ พวกเขาจะพินาศสิ้นในแผ่นดินอียิปต์เพราะสงครามหรือการกันดารอาหาร ตั้งแต่ผู้ต่ำต้อยที่สุดจนถึงผู้ยิ่งใหญ่ที่สุดจะตายเพราะสงครามหรือการกันดารอาหาร เขาจะกลายเป็นเป้าของการสาปแช่งและความสยดสยอง การดูหมิ่นเหยียดหยามและการตำหนิติเตียน 13เราจะลงโทษพวกที่อยู่ในแผ่นดินอียิปต์ด้วยสงคราม การกันดารอาหาร และโรคระบาดเหมือนที่เราได้ลงโทษเยรูซาเล็ม 14ไม่มีสักคนในคนหยิบมือที่เหลือของยูดาห์ซึ่งไปอยู่ที่แผ่นดินอียิปต์นั้นจะหนีรอดหรือรอดชีวิตกลับไปยังดินแดนยูดาห์ซึ่งเขาอยากกลับไปอยู่ จะไม่มีใครได้กลับไป เว้นแต่ผู้ลี้ภัยไม่กี่คน”

15แล้วผู้ชายทุกคนที่รู้ว่าภรรยาของตนได้เผาเครื่องหอมถวายเทพเจ้าต่างๆ พร้อมกับผู้หญิงทุกคนที่นั่นซึ่งมารวมตัวกันเป็นชนกลุ่มใหญ่ รวมทั้งบรรดาผู้อาศัยอยู่ในอียิปต์ตอนบนและตอนล่าง44:15 ภาษาฮีบรูว่าในอียิปต์และปัทโรส จึงตอบเยเรมีย์ว่า 16“เราจะไม่ฟังถ้อยคำซึ่งท่านอ้างพระนามพระยาห์เวห์มาพูดกับเรา! 17เราจะทำทุกอย่างตามที่เราได้พูดไว้อย่างแน่นอน คือเผาเครื่องหอมถวายเทวีแห่งสวรรค์และรินเครื่องดื่มบูชาถวายพระนาง เหมือนที่เรากับบรรพบุรุษ ตลอดจนเหล่ากษัตริย์ของเราและบรรดาข้าราชการได้ทำในหัวเมืองต่างๆ ของยูดาห์และตามถนนหนทางในเยรูซาเล็ม ครั้งนั้นเรามีอาหารกินเหลือเฟือและสุขสบายดี ไม่มีภัยอันตรายใดๆ 18แต่เมื่อเราเลิกเผาเครื่องหอมถวายองค์เทวีแห่งสวรรค์ เลิกถวายเครื่องดื่มบูชาแด่พระนาง เราก็ไม่เหลืออะไรและต้องพินาศเพราะสงครามและการกันดารอาหาร”

19พวกผู้หญิงพูดด้วยว่า “เมื่อเราเผาเครื่องหอมถวายเทวีแห่งสวรรค์ รินเครื่องดื่มบูชาถวายพระนาง และทำขนมรูปพระนางถวายนั้น สามีของเราไม่รู้ไม่เห็นหรือ?”

20เยเรมีย์จึงกล่าวแก่พวกผู้ชายผู้หญิงที่ตอบเขานั้นว่า 21องค์พระผู้เป็นเจ้าไม่ได้ทรงจดจำและคิดถึงเครื่องหอมต่างๆ ที่ท่านกับบรรพบุรุษ ตลอดจนกษัตริย์และข้าราชการกับประชาชนถวายในเมืองต่างๆ ของยูดาห์และตามถนนหนทางในเยรูซาเล็มหรือ? 22เมื่อองค์พระผู้เป็นเจ้าไม่อาจอดกลั้นพระทัยต่อการกระทำชั่วร้ายและสิ่งน่าชิงชังซึ่งท่านทำนั้นต่อไปได้ ดินแดนของท่านจึงตกเป็นเป้าของการสาปแช่ง เป็นดินแดนร้างไร้ผู้อยู่อาศัยดังเช่นทุกวันนี้ 23ก็เพราะท่านได้เผาเครื่องหอมและได้ทำบาปต่อองค์พระผู้เป็นเจ้า ไม่ได้เชื่อฟังพระองค์หรือปฏิบัติตามบทบัญญัติ กฎหมาย และพระบัญชาของพระองค์ ภัยพิบัตินี้จึงเกิดแก่ท่านตามที่ท่านเห็นอยู่ในขณะนี้”

24แล้วเยเรมีย์กล่าวกับประชาชนทั้งปวงรวมทั้งพวกผู้หญิงว่า “ชาวยูดาห์ทั้งปวงที่อยู่ในแผ่นดินอียิปต์ จงฟังพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้า 25พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ พระเจ้าแห่งอิสราเอลตรัสดังนี้ว่าเจ้าทั้งหลายกับภรรยาได้พิสูจน์ด้วยการทำตามสิ่งที่เจ้าสัญญาไว้ เมื่อเจ้ากล่าวว่า ‘เราจะทำตามที่สาบานไว้ว่าจะเผาเครื่องหอมและถวายเครื่องดื่มบูชาแก่เทวีแห่งสวรรค์อย่างแน่นอน’

“ถ้าอย่างนั้นก็จงทำต่อไป ทำตามที่เจ้าสัญญาไว้! ทำตามที่เจ้าสาบานไว้! 26แต่ชาวยิวทั้งปวงที่อยู่ในแผ่นดินอียิปต์นี้ จงฟังพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้าองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า ‘เราปฏิญาณไว้ด้วยนามอันยิ่งใหญ่ของเราว่า ชาวยูดาห์ซึ่งมาอาศัยอยู่ในอียิปต์นี้จะไม่มีสักคนได้เอ่ยนามของเราหรือปฏิญาณว่า “พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตทรงพระชนม์อยู่แน่ฉันใด” 27เพราะเรากำลังจับตาดูพวกเจ้าเพื่อลงโทษ ไม่ใช่เพื่อให้มีความสุข ชาวยิวในแผ่นดินอียิปต์จะพินาศเพราะสงครามและการกันดารอาหารจนกว่าจะถูกทำลายหมดสิ้น 28ผู้ที่รอดจากสงครามและได้กลับจากแผ่นดินอียิปต์ไปยังยูดาห์จะมีอยู่น้อยนัก แล้วเมื่อนั้นชนหยิบมือที่เหลือทั้งหมดจากยูดาห์ซึ่งมาอาศัยอยู่ในแผ่นดินอียิปต์นี้จะรู้ว่าถ้อยคำของเราหรือของเขากันแน่ที่เป็นจริง’

29องค์พระผู้เป็นเจ้าประกาศว่า ‘นี่คือหมายสำคัญที่ทำให้เจ้ารู้ว่าเราจะลงโทษเจ้าที่นี่แน่นอน เพื่อเจ้าจะรู้ว่าถ้อยคำที่เราได้ลั่นวาจาไว้ว่าจะนำภัยพิบัติมายังเจ้านั้นจะเป็นจริง’ 30องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า ‘เราจะมอบฟาโรห์โฮฟรากษัตริย์แห่งอียิปต์ไว้ในมือของศัตรูผู้หมายเอาชีวิตของเขา เหมือนที่เราได้มอบกษัตริย์เศเดคียาห์แห่งยูดาห์แก่กษัตริย์เนบูคัดเนสซาร์แห่งบาบิโลนศัตรูผู้หมายเอาชีวิตของเขา’ ”