ኤርምያስ 35 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 35:1-19

የሬካባውያን ታማኝነት

1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ፣ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 2“ወደ ሬካባውያን ሄደህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣቸው፤ ወደ አንዱም ክፍል አስገብተህ የሚጠጡትን ወይን ጠጅ ስጣቸው።”

3ስለዚህ የካባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቹን ሁሉ፣ የሬካባውያንን ወገን በአጠቃላይ ሄጄ ጠራኋቸው፤ 4ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤ 5በሬካባውያንም ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ማድጋዎችን አቀረብሁ፤ ዋንጫዎችንም ሰጥቻቸው፣ “በሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኋቸው።

6እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፤ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤ ‘እናንተና ዘራችሁ ከቶ የወይን ጠጅ አትጠጡ፤ 7ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ፤ ሁልጊዜ በድንኳን ኑሩ እንጂ ከእነዚህ ነገሮች አንዱም አይኑራችሁ፤ ይህም ሲሆን እንደ መጻተኛ በሆናችሁበት ምድር ረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።’ 8እኛም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ ፈጽመናል፤ እኛና ሚስቶቻችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ ጠጥተን አናውቅም፤ 9የምንቀመጥበትም ቤት አልሠራንም፤ የወይን ቦታ፣ የዕርሻ ስፍራ ወይም የእህል ዘር የለንም። 10በድንኳን ኖረናል፤ አባታችን ኢዮናዳብ ያዘዘንንም ሁሉ ጠብቀናል። 11ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይህችን ምድር በወረረ ጊዜ፣ ‘ኑ፤ ከባቢሎን35፥11 ወይም ከለዳውያን ሰራዊትና ከሶርያ ሰራዊት ሸሽተን ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ ተባባልን፤ ስለዚህም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” 12የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ 13“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሂድ፤ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ቃሌን ትጠብቁ ዘንድ ከዚህ አትማሩምን?’ ይላል እግዚአብሔር14‘የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዘዛቸው፤ ይህም ትእዛዝ ተጠብቋል፤ የአባታቸውን ትእዛዝ ስለ ጠበቁ እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ እናንተ ግን እኔ ደጋግሜ ብናገራችሁም፤ አልታዘዛችሁኝም። 15አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሜ ወደ እናንተ ላክሁ፤ እነርሱም፣ “እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ምግባራችሁን አስተካክሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር ትኖሩ ዘንድ ሌሎቹን አማልክት ለማገልገል አትከተሉ” አልኋችሁ። እናንተ ግን ጆሯችሁን ወደ እኔ አላዘነበላችሁም፤ አልሰማችሁኝምም። 16የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠብቀዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አልታዘዘኝም።’

17“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤ በተናገርኋቸው ጊዜ፣ አልሰሙኝምና በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝም።’ ”

18ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስለ ጠበቃችሁ፤ መመሪያውን ስለ ተከተላችሁ፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ ስለ ፈጸማችሁ’ 19የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን የሚያገለግለኝ ሰው ለዘላለም አይታጣም።’ ”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

耶利米書 35:1-19

順服的利甲族和悖逆的猶大人

1猶大約西亞的兒子約雅敬執政期間,耶和華對耶利米說: 2「你去利甲族那裡,邀請他們到耶和華殿的一間廂房,給他們酒喝。」 3於是,我將哈巴洗尼雅的孫子、雅利米雅的兒子雅撒尼亞,以及雅撒尼亞的弟兄和兒子等利甲全族的人, 4領到耶和華的殿,進入上帝的僕人伊基大利之子哈難眾兒子的房間。這房間靠近官長的房間,在殿門守衛沙龍的兒子瑪西雅的房間上面。 5我把盛滿酒的杯和壺擺在利甲全族面前,請他們喝酒。 6他們卻說:「我們不喝酒,因為我們的祖先利甲的兒子約拿達曾吩咐我們和我們的子孫永遠不可喝酒、 7蓋房、撒種、栽植葡萄或擁有葡萄園,一輩子都要住帳篷,以便在異鄉長久居住。 8我們遵守他的一切吩咐,我們和我們的妻子兒女從不喝酒, 9不蓋房,也沒有葡萄園、田地和種子。 10我們住帳篷,遵守我們祖先約拿達的一切吩咐。 11但當巴比倫尼布甲尼撒進攻這裡的時候,我們決定來耶路撒冷躲避迦勒底亞蘭的軍隊。因此,我們現在住在耶路撒冷。」

12耶和華對耶利米說: 13「這是以色列的上帝——萬軍之耶和華的話,你去把我的話告訴猶大人和耶路撒冷的居民,『耶和華說,你們要聽從我的教導。 14利甲的兒子約拿達吩咐他的子孫不可喝酒,他們直到現在都不喝酒。但我屢次告誡你們,你們卻不聽我的話。 15我再三差遣我的僕人——眾先知勸你們改邪歸正,不要追隨、祭拜別的神明,以便你們可以在我賜給你們和你們祖先的土地上安居樂業,你們卻充耳不聞,毫不理會。 16利甲的兒子約拿達的子孫尚且聽從他們祖先的吩咐,你們卻不聽從我的話。 17因此,以色列的上帝——萬軍之耶和華說,我要給猶大耶路撒冷的居民降下我說過的災禍。因為我對他們說話,他們不聽;我呼喚他們,他們不理會。』」

18然後,耶利米利甲族人說:「以色列的上帝——萬軍之耶和華說,『你們聽從祖先利甲的兒子約拿達的吩咐,遵守他的一切命令, 19因此,利甲的兒子約拿達的子孫必永遠事奉我。這是以色列的上帝——萬軍之耶和華說的。』」