ኤርምያስ 31 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 31:1-40

1“በዚያ ዘመን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለእስራኤል ነገድ ሁሉ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”

2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣

በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤

እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።”

3እግዚአብሔር ከሩቅ31፥3 ወይም እግዚአብሔር ከጥንት ወይም ከቀድሞ ተገለጠልን ተገለጠልን፤ እንዲህም አለን፤

“በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤

ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ።

4የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና ዐንጽሻለሁ፤

አንቺም ትታነጺአለሽ፤

ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣

ከሚፈነጥዙት ጋር ትፈነድቂአለሽ።

5እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣

ወይን ትተክያለሽ፤

አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤

በፍሬውም ደስ ይላቸዋል።

6ጠባቂዎች፣ በኤፍሬም ኰረብቶች ላይ፣

‘ኑ፤ ወደ ጽዮን፣

ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ!’

ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣል።”

7እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤

ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤

ምስጋናችሁን አሰሙ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣

ሕዝብህን አድን’ በሉ።

8እነሆ፤ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ፤

ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤

በመካከላቸውም ዕውሮችና ዐንካሶች፣

ነፍሰ ጡርና በምጥ ላይ ያሉ ሴቶች ይገኛሉ፤

ታላቅም ሕዝብ ሆነው ይመለሳሉ።

9እያለቀሱ ይመጣሉ፤

እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤

እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣

ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣

በውሃ ምንጭ ዳር፣

በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።

10“ሕዝቦች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤

ሩቅ ባሉ የባሕር ጠረፎችም፣

‘እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤

መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል’ ብላችሁ ዐውጁ።

11እግዚአብሔር ያዕቆብን ይዋጀዋልና፤

ከእርሱም ከሚበረቱት እጅ ይታደገዋልና።

12መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤

በእግዚአብሔርም ልግስና፣

በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣

በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤

ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤

ከእንግዲህም አያዝኑም።

13ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤

ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤

ልቅሷቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤

ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ።

14ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤

ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤”

ይላል እግዚአብሔር

15እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ዋይታና መራራ ልቅሶ

ከራማ ተሰማ፤

ልጆቿ የሉምና፣

ራሔል አለቀሰች፤

መጽናናትም እንቢ አለች።”

16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ድምፅሽን ከልቅሶ፣

ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክይ፤

ድካምሽ ያለ ዋጋ አይቀርምና፤”

ይላል እግዚአብሔር

“ከጠላት ምድር ይመለሳሉ፤

17ስለዚህ ወደ ፊት ተስፋ አለሽ”

ይላል እግዚአብሔር

“ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።

18“የኤፍሬምን የሲቃ እንጕርጕሮ በርግጥ ሰምቻለሁ፤

‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤

እኔም ተቀጣሁ።

አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣

መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።

19ከአንተ ከራቅሁ በኋላ፣

ተመልሼ ተጸጸትሁ፤

ባስተዋልሁም ጊዜ፣

ጭኔን መታሁ፤

የወጣትነት ውርደቴን ተሸክሜአለሁና

ዐፈርሁ፤ ቀለልሁም።’

20ኤፍሬም የምወድደው፣

ደስም የምሰኝበት ልጄ አይደለምን?

ብዙ ጊዜ ተቃውሜው ብናገርም፣

መልሼ ስለ እርሱ ዐስባለሁ፤

አንጀቴ ይላወሳል፤

በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

21“የጐዳና ምልክት አቁሚ፤

መንገድ አመልካች ትከዪ፤

የምትሄጂበትን መንገድ፣

አውራ ጐዳናውን አስተውዪ፤

ድንግሊቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሺ፤

ወደ ከተሞችሽም ግቢ።

22አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤

እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ?

እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤

ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።31፥22 ወይም መፈለግ ትጀምራለች ወይም መጠበቅ ትጀምራለች

23የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምርኳቸውን በመለስሁላቸው ጊዜ፣31፥23 ወይም ዕድል ፈንታቸውን በመለስሁላቸው እነርሱ በይሁዳ ምድርና በከተሞቿ፣ ‘አንተ የጽድቅ ማደሪያ ቅዱስ ተራራ ሆይ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ!’ የሚል አነጋገር እንደ ገና ይጠቀማሉ። 24ገበሬዎችና ዘላን ከብት አርቢዎች በይሁዳና በከተሞቿ በአንድነት ይኖራሉ። 25የዛለችውን ነፍስ ዐድሳለሁ፤ የደከመችውንም አበረታለሁ።”

26በዚህ ጊዜ ከእንቅልፌ ነቅቼ ዙሪያዬን ተመለከትሁ፤ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆኖልኝ ነበር።

27“እነሆ፤ የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት” ይላል እግዚአብሔር፤ “በሰውና በእንስሳት ዘር የምሞላበት ጊዜ ይመጣል፤ 28ልነቅላቸውና ላፈርሳቸው፣ ልገለብጣቸውና ላጠፋቸው፣ መከራም ላመጣባቸው እንደ ተጋሁ ሁሉ፣ ላንጻቸውና ልተክላቸው ደግሞ እተጋለሁ” ይላል እግዚአብሔር29“በዚያ ዘመን ሰዎች ዳግመኛ፣

“ ‘አባቶች በበሉት ጐምዛዛ የወይን ፍሬ፣

የልጆች ጥርስ ጠረሰ’

የሚለውን ምሳሌ አይናገሩም። 30ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል።

31“ከእስራኤል ቤትና፣

ከይሁዳ ቤት ጋር” ይላል እግዚአብሔር

“አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት፣

ጊዜ ይመጣል።

32ከግብፅ አወጣቸው ዘንድ፣

እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣

ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን

አይደለም፤31፥32 የዕብራይስጡ፣ የሰብዓ ሊቃናትና የሱርሰት ትርጕሞች እኔም ዘወር አልሁባቸው ይላሉ።

የእነርሱ ባል31፥32 31፥32 ወይም የእነርሱ ጌታ ሆኜ ሳለሁ፣

ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።”

ይላል እግዚአብሔር

33“ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣

ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር

“ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤

በልባቸውም እጽፈዋለሁ።

እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤

እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

34ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣

ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤

ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣

ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤”

ይላል እግዚአብሔር

“በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤

ኀጢአታቸውንም መልሼ አላስብም።”

35በቀን እንድታበራ፣

ፀሓይን የመደበ፣

በሌሊት እንዲያበሩ፣

ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣

የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣

ባሕሩን የሚያናውጥ፣

ስሙ የሰራዊት ጌታ የሆነ፣

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

36“ይህ ሥርዐት በፊቴ ከተሻረ፣”

ይላል እግዚአብሔር

“በዚያ ጊዜ የእስራኤልም ዘር በፊቴ፣

መንግሥት መሆኑ ለዘላለም ይቀራል።”

37እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በላይ ያሉትን ሰማያትን መለካት፣

በታችም ያሉትን የምድር መሠረቶች መመርመር ከተቻለ፣

በዚያ ጊዜ የእስራኤልን ዘር ሁሉ፣

ስላደረጉት ነገር ሁሉ እጥላቸዋለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

38“እነሆ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ በር ድረስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ይህች ከተማ ለእግዚአብሔር የምትሠራበት ጊዜ ይመጣል፤ 39መለኪያ ገመዱም ከዚያ ጀምሮ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኰረብታ፣ ዐልፎም ወደ ጎዓ ይዘረጋል። 40ሬሳና ዐመድ የሚጣልበት ሸለቆ በሙሉ፣ በምሥራቅ በኩል የቄድሮንን ሸለቆ ይዞ እስከ ፈረስ በር የሚደርሰው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ከተማዪቱ አትነቀልም፤ አትፈርስምም።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 31:1-40

以色列人必回归

1耶和华说:“那时,我要做以色列各宗族的上帝,他们必做我的子民。

2“逃脱刀兵之灾的以色列人必在旷野蒙恩,

找到安息之所。

这是耶和华说的。”

3从前,耶和华向以色列显现,说:

“我以永远不变的爱爱你,

我以慈爱吸引你到我身边。

4以色列人啊,

我要重建你们的家园,

你们要再次拿起铃鼓与欢乐的人一同跳舞。

5你们将在撒玛利亚的山上重新栽种葡萄园,

享受园中的果实。

6有一天,看守园子的人要在以法莲的山上呼喊,

‘我们上锡安朝见我们的上帝耶和华吧!’”

7耶和华说:

“你们要为雅各欢呼歌唱,

向列国之首喝采。

你们要传扬颂赞,说,

‘耶和华啊,

求你拯救以色列剩余的子民!’

8看啊,我要从北方,

从地极招聚他们,

其中有瞎子、跛子、孕妇和产妇,

他们要成群结队地回到这里。

9我必引领他们回来,

他们必一路含泪祷告。

我要使他们走在溪水边,

行在平坦的路上,

他们必不会跌倒,

因为我是以色列的父亲,

以法莲是我的长子。

10“列国啊,你们要听耶和华的话,

要在远方的海岛宣扬,

‘祂从前驱散以色列人,

如今必再聚集、保护他们,

好像牧人看守自己的羊群一样。’

11耶和华必拯救雅各的子孙,

从强敌手中救出他们。

12他们必来到锡安山上欢呼,

为耶和华所赐的五谷、新酒、

油、羔羊和牛犊而欢欣。

他们就像水源充足的田园,

一无所缺。

13那时,少女要欢然起舞,

老人和青年要一起快乐。

我要使他们转忧为喜,

我要安慰他们,使他们欢喜,

不再忧愁。

14我要使祭司有充足的供应,

使我的子民饱享美物。

这是耶和华说的。”

15耶和华说:

“在拉玛有痛哭哀号的声音,

拉结在为儿女哀痛,

不肯接受安慰,

因为他们都死了。”

16耶和华说:

“不要哭泣,不要流泪,

因为你的劳苦必有回报,

你的儿女必从敌国回来。

这是耶和华说的。

17你将来必有盼望,

你的儿女必重返家园。

这是耶和华说的。

18我听见以法莲31:18 以法莲”是北国以色列的主要支派,常用来代指北国以色列。在为自己悲叹,

‘我们就像未经驯服的牛犊,

你管教我们,使我们顺服,

求你使我们回到你身边,

重新复兴,

因为你是我们的上帝耶和华。

19我们曾经离开你,

但我们后悔了;

我们醒悟之后捶胸顿足,

痛悔不已,

因早年的所作所为而羞愧难当。’”

20耶和华说:“以法莲不是我的爱子吗?

他不是我喜悦的孩子吗?

我虽然常常责备他,

但仍然惦记着他。

我深深地想念他,

我必怜悯他。

21以色列人啊,

你们要为自己设置路标,

竖起路牌,

牢记你们走过的大道。

以色列人啊,

回来吧!回到你们的城邑吧!

22不忠贞的子民啊!

你们四处流浪要到何时呢?

耶和华在地上行了一件新事——女子将要护卫男子。”

23以色列的上帝——万军之耶和华说:“我使被掳的犹大人回到故乡后,他们要在犹大各城邑再次呼喊,

“‘公义的居所啊,

圣山啊,愿耶和华赐福给你!’

24“农夫和牧人必住在犹大的各城邑。 25我要使疲乏的人振作起来,使苦闷的人快乐起来。”

26这时,我醒过来,觉得这一觉实在香甜。

27耶和华说:“看啊,时候将到,我要使以色列犹大人丁兴旺,牲畜繁多。 28我曾决意铲除、拆毁、推翻、剿灭他们,降灾给他们,将来我必塑造、栽培他们。这是耶和华说的。 29那时,人再不会说,

“‘父亲吃酸葡萄,

儿子的牙酸倒了。’

30因为各人都要承担自己的罪,谁吃酸葡萄,谁的牙酸倒。” 31耶和华说:“看啊,时候将到,我要与以色列家和犹大家另立新约, 32这约不同于我与他们祖先所立的约,就是我牵着他们祖先的手领他们离开埃及时所立的。虽然我是他们的丈夫,他们却违背了我的约。这是耶和华说的。”

33耶和华说:“那些日子以后,我将与以色列家立这样的约,我要把我的律法放在他们脑中,写在他们心上。我要做他们的上帝,他们要做我的子民。 34谁都无需再教导他的邻居和弟兄,说,‘你要认识耶和华’,因为他们无论尊卑都必认识我。我要赦免他们的过犯,忘掉他们的罪恶。这是耶和华说的。”

35使阳光白天照耀、

星月晚上发光、

大海波涛汹涌的万军之耶和华说:

36“只要天地之律还在,

以色列邦国必永续不断。

这是耶和华说的。”

37耶和华说:

“正如无人能量度高天,

探测大地的根基,

同样我也决不会因以色列人的所作所为而弃绝他们。

这是耶和华说的。”

38耶和华说:“看啊,时候将到,从哈楠业楼直到角门,整个耶路撒冷城要重建起来归给耶和华。 39城界要向外延伸到迦立山,再转到歌亚40甚至抛尸、倒灰的整个山谷,以及从汲沦溪到东边马门拐角的所有田地都要归给耶和华作圣地,永不再被倾覆、毁灭。”