ኤርምያስ 27 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 27:1-22

የይሁዳ በናቡከደነፆር ሥር መውደቅ

1በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ27፥1 ጥቂት የዕብራይስጥ ጽሑፎችና የሱርሰት ትርጕም (ኤር 27፥312 እና 28፥1 ይመ)፣ አንዳንድ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ኢዮአቄም ይላሉ (አብዛኛዎቹ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ይህ ጥቅስ ቍጥር የላቸውም)። ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የዕንጨት ቀንበር ሠርተህ በጠፍር ማነቆ አያይዘውና በዐንገትህ አስገባው፤ 3ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት ሰዎች በኩል ለኤዶም፣ ለሞዓብ፣ ለአሞን፣ ለጢሮስና ለሲዶና ነገሥታት መልእክት ላክ። 4ለጌቶቻቸውም እንዲያሳውቁ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለጌቶቻችሁ ይህን ንገሯቸው፤ 5በታላቁ ኀይሌና በተዘረጋው ክንዴ ምድርን፣ በላይዋ የሚኖሩትን ሰዎችና እንስሳት ፈጥሬአለሁ፤ ለምወድደውም እሰጣለሁ። 6አሁንም እነዚህን አገሮች ሁሉ ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣለሁ፤ የዱር አራዊት እንኳ እንዲገዙለት አደርጋለሁ። 7የእርሱ አገር በተራው ለሌሎች እስከሚገዛበት ጊዜ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ለእርሱ፣ ለልጁና ለልጅ ልጁ ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት እርሱን ይገዙታል።

8“ ‘ “ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር የማይገዛ፣ ዐንገቱንም ከቀንበሩ በታች ዝቅ የማያደርግ ማንኛውንም ሕዝብ ወይም መንግሥት በእጁ እስከማጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሠፍትም እቀጣዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር9ስለዚህ፣ ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያታችሁን፣ ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልመኞቻችሁን፤ መናፍስት ጠሪዎቻችሁንና መተተኞቻቸሁን አትስሙ፤ 10ከምድራችሁ እንድትፈናቀሉ፣ እኔም እንዳሳድዳችሁና እንዳጠፋችሁ የሐሰት ትንቢት ይነግሯችኋልና። 11ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዐንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሕዝብ በገዛ ምድሩ እንዲቀርና እያረሰም በዚያ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።” ’ ”

12ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህንኑ መልእክት እንዲህ ብዬ ነገርሁት፤ “ዐንገታችሁን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዝቅ አድርጉ፤ እርሱንና ሕዝቡን አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ። 13አንተና ሕዝብህ፣ እግዚአብሔር ለባቢሎን ንጉሥ አልገዛም ያለውን ሕዝብ ባስጠነቀቀበት በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ለምን ታልቃላችሁ? 14ሐሰተኛ ትንቢት ስለሚነግሯችሁ፣ ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሙ፤ 15‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”

16እኔም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልሁ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ ከባቢሎን ቶሎ ይመለሳል’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሟቸው፤ የሚነግሯችሁ የሐሰት ትንቢት ነውና። 17ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ባለመታዘዛችሁስ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ? 18እውነተኞች ነቢያት ከሆኑና በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ ወደ ሰራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር እስቲ ይማልዱ! 19የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህች ከተማ ስለ ቀሩት ዐምዶች፣ ከናስ ስለ ተሠራው ትልቁ ገንዳ፣ ስለ ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎችና ስለ ሌሎቹም ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፤ 20የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣27፥20 ኢኮንያን የኢዮአኪን ሌላው አቻ ስም ነው። ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ መኳንንት ጋር ማርኮ ወደ ባቢሎን በወሰደ ጊዜ እነዚህ በከተማዪቱ የቀሩ ዕቃዎች ስለሆኑ፣ 21በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች፣ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 22‘ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቀመጣሉ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በዚያ ጊዜም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’ ”

New International Version – UK

Jeremiah 27:1-22

Judah to serve Nebuchadnezzar

1Early in the reign of Zedekiah27:1 A few Hebrew manuscripts and Syriac (see also 27:3,12 and 28:1); most Hebrew manuscripts Jehoiakim (most Septuagint manuscripts do not have this verse.) son of Josiah king of Judah, this word came to Jeremiah from the Lord: 2this is what the Lord said to me: ‘Make a yoke out of straps and crossbars and put it on your neck. 3Then send word to the kings of Edom, Moab, Ammon, Tyre and Sidon through the envoys who have come to Jerusalem to Zedekiah king of Judah. 4Give them a message for their masters and say, “This is what the Lord Almighty, the God of Israel, says: ‘Tell this to your masters: 5with my great power and outstretched arm I made the earth and its people and the animals that are on it, and I give it to anyone I please. 6Now I will give all your countries into the hands of my servant Nebuchadnezzar king of Babylon; I will make even the wild animals subject to him. 7All nations will serve him and his son and his grandson until the time for his land comes; then many nations and great kings will subjugate him.

8‘ “ ‘If, however, any nation or kingdom will not serve Nebuchadnezzar king of Babylon or bow its neck under his yoke, I will punish that nation with the sword, famine and plague, declares the Lord, until I destroy it by his hand. 9So do not listen to your prophets, your diviners, your interpreters of dreams, your mediums or your sorcerers who tell you, “You will not serve the king of Babylon.” 10They prophesy lies to you that will only serve to remove you far from your lands; I will banish you and you will perish. 11But if any nation will bow its neck under the yoke of the king of Babylon and serve him, I will let that nation remain in its own land to till it and to live there, declares the Lord.’ ” ’

12I gave the same message to Zedekiah king of Judah. I said, ‘Bow your neck under the yoke of the king of Babylon; serve him and his people, and you will live. 13Why will you and your people die by the sword, famine and plague with which the Lord has threatened any nation that will not serve the king of Babylon? 14Do not listen to the words of the prophets who say to you, “You will not serve the king of Babylon,” for they are prophesying lies to you. 15“I have not sent them,” declares the Lord. “They are prophesying lies in my name. Therefore, I will banish you and you will perish, both you and the prophets who prophesy to you.” ’

16Then I said to the priests and all these people, ‘This is what the Lord says: do not listen to the prophets who say, “Very soon now the articles from the Lord’s house will be brought back from Babylon.” They are prophesying lies to you. 17Do not listen to them. Serve the king of Babylon, and you will live. Why should this city become a ruin? 18If they are prophets and have the word of the Lord, let them plead with the Lord Almighty that the articles which remain in the house of the Lord and in the palace of the king of Judah and in Jerusalem will not be taken to Babylon. 19For this is what the Lord Almighty says about the pillars, the bronze Sea, the movable stands and the other articles that are left in this city, 20which Nebuchadnezzar king of Babylon did not take away when he carried Jehoiachin27:20 Hebrew Jeconiah, a variant of Jehoiachin son of Jehoiakim king of Judah into exile from Jerusalem to Babylon, along with all the nobles of Judah and Jerusalem – 21yes, this is what the Lord Almighty, the God of Israel, says about the things that are left in the house of the Lord and in the palace of the king of Judah and in Jerusalem: 22“They will be taken to Babylon and there they will remain until the day I come for them,” declares the Lord. “Then I will bring them back and restore them to this place.” ’