ኤርምያስና ጳስኮር
1በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አለቃ የነበረው፣ የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር እነዚህን ነገሮች ኤርምያስ እንደ ተነበየ በሰማ ጊዜ፣ 2ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው። 3በማግስቱም ጳስኮር ኤርምያስን ከተጠረቀበት ግንድ አወጣው፤ ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ከእንግዲህ ማጎርሚሳቢብ20፥3 ማጎርሚሳቢብ ማለት ዙሪያ-ገባው ሽብር ማለት ነው። ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም፤ 4እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ባልንጀሮችህን ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል። 5የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ። 6ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ባልንጆሮችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”
የኤርምያስ ማጕረምረም
7እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤20፥7 ወይም ሐሳቤን አስለወጥኸኝ እኔም ተታለልሁ፤
አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤
ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤
ሁሉም ተዘባበቱብኝ።
8በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤
“ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤
ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣
ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ።
9ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የእርሱን ስም አላነሣም፤
በስሙም አልናገርም” ብል፣
ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣
በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤
ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤
ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።
10“በየቦታው ሽብር አለ፤
አውግዙት፤ እናውግዘው፤”
ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤
መውደቄን በመጠባበቅ፣
ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣
“ይታለል ይሆናል፣
ከዚያም እናሸንፈዋለን፤
እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
11ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤
ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤
ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤
ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
12ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤
ጕዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁና
ስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ።
13ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤
የችግረኛውን ነፍስ፣
ከክፉዎች እጅ ታድጓልና።
14የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤
እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።
15“ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል” ብሎ፣
ለአባቴ የምሥራች የነገረ፣
ደስ ያሰኘውም ሰው የተረገመ ይሁን።
16ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣
እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤
በማለዳ ዋይታን፣
በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤
17እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣
ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣
ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና።
18ችግርና ሐዘንን ለማየት፣
ዘመኔንም በውርደት ለመፈጸም፣
ለምን ከማሕፀን ወጣሁ?
1Now Pashur the son of Immer the priest, who was also chief governor in the house of the LORD, heard that Jeremiah prophesied these things. 2Then Pashur smote Jeremiah the prophet, and put him in the stocks that were in the high gate of Benjamin, which was by the house of the LORD. 3And it came to pass on the morrow, that Pashur brought forth Jeremiah out of the stocks. Then said Jeremiah unto him, The LORD hath not called thy name Pashur, but Magor-missabib.20.3 Magor-missabib: that is, Fear round about 4For thus saith the LORD, Behold, I will make thee a terror to thyself, and to all thy friends: and they shall fall by the sword of their enemies, and thine eyes shall behold it: and I will give all Judah into the hand of the king of Babylon, and he shall carry them captive into Babylon, and shall slay them with the sword. 5Moreover I will deliver all the strength of this city, and all the labours thereof, and all the precious things thereof, and all the treasures of the kings of Judah will I give into the hand of their enemies, which shall spoil them, and take them, and carry them to Babylon. 6And thou, Pashur, and all that dwell in thine house shall go into captivity: and thou shalt come to Babylon, and there thou shalt die, and shalt be buried there, thou, and all thy friends, to whom thou hast prophesied lies.
7¶ O LORD, thou hast deceived me, and I was deceived: thou art stronger than I, and hast prevailed: I am in derision daily, every one mocketh me.20.7 was deceived: or, was enticed 8For since I spake, I cried out, I cried violence and spoil; because the word of the LORD was made a reproach unto me, and a derision, daily. 9Then I said, I will not make mention of him, nor speak any more in his name. But his word was in mine heart as a burning fire shut up in my bones, and I was weary with forbearing, and I could not stay.
10¶ For I heard the defaming of many, fear on every side. Report, say they, and we will report it. All my familiars watched for my halting, saying, Peradventure he will be enticed, and we shall prevail against him, and we shall take our revenge on him.20.10 All…: Heb. Every man of my peace 11But the LORD is with me as a mighty terrible one: therefore my persecutors shall stumble, and they shall not prevail: they shall be greatly ashamed; for they shall not prosper: their everlasting confusion shall never be forgotten. 12But, O LORD of hosts, that triest the righteous, and seest the reins and the heart, let me see thy vengeance on them: for unto thee have I opened my cause. 13Sing unto the LORD, praise ye the LORD: for he hath delivered the soul of the poor from the hand of evildoers.
14¶ Cursed be the day wherein I was born: let not the day wherein my mother bare me be blessed. 15Cursed be the man who brought tidings to my father, saying, A man child is born unto thee; making him very glad. 16And let that man be as the cities which the LORD overthrew, and repented not: and let him hear the cry in the morning, and the shouting at noontide; 17Because he slew me not from the womb; or that my mother might have been my grave, and her womb to be always great with me. 18Wherefore came I forth out of the womb to see labour and sorrow, that my days should be consumed with shame?