ኤርምያስ 17 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 17:1-27

1“የይሁዳ ኀጢአት በብረት ብርዕ፣

በሾለ የአልማዝ ጫፍ፣ ተጽፏል፤

በልባቸው ጽላት፣

በመሠዊያቸውም ቀንዶች ላይ ተቀርጿል።

2ልጆቻቸው እንኳ ሳይቀሩ፣

በለመለሙ ዛፎች ሥር፣

ከፍ ባሉ ኰረብቶችም ላይ ያሉትን፣

መሠዊያቸውንና አሼራ የተባለችውን ጣዖት ምስል17፥2 ወይም የአሼራ ዐጸድ ያስባሉ።

3በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣

በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣17፥3 ወይም በምድሪቱ ያሉ ተራራዎችን

ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣

መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣

ለብዝበዛ አደርገዋለሁ።

4በገዛ ጥፋትህ፣

የሰጠሁህን ርስት ታጣለህ፤

በማታውቀውም ምድር፣

ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ፤

ለዘላለም የሚነድደውን፣

የቍጣዬን እሳት ጭረሃልና።”

5እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በሰው የሚታመን፣

በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣

ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው።

6በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤

መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤

ሰው በሌለበት በጨው ምድር፣

በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።

7“ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚታመን፣

መታመኛውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።

8በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣

ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣

ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤

ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤

በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤

ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”

9የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነው፤

ፈውስም የለውም፤

ማንስ ሊረዳው ይችላል?

10“እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣

እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት፣

ልብን እመረምራለሁ፤

የአእምሮንም ሐሳብ እፈትናለሁ።”

11ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣

ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤

በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤

በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል።

12የመቅደሳችን ስፍራ፣

ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።

13የእስራኤል ተስፋ እግዚአብሔር ሆይ፤

ጥለውህ የሚሄዱ ሁሉ ያፍራሉ፤

ፊታቸውን ከአንተ የሚመልሱ በምድር ውስጥ ይጻፋሉ፤

የሕይወትን ውሃ ምንጭ፣

እግዚአብሔርን ትተዋልና።

14እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈውሰኝ፤ እፈወሳለሁ፤

አድነኝ እኔም እድናለሁ፤

አንተ ምስጋናዬ ነህና።

15እነርሱ ደጋግመው፣

የእግዚአብሔር ቃል የት አለ?

እስቲ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።

16እረኛ ሆኜ አንተን ከማገልገል ወደ ኋላ አላልሁም፤

ክፉ ቀን እንዳልተመኘሁ ታውቃለህ፤

ከአንደበቴ የሚወጣውም በፊትህ ግልጽ ነው።

17አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤

በመከራ ቀን መሸሸጊያዬ አንተ ነህ።

18አሳዳጆቼ ይፈሩ፤

እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤

እነርሱ ይደንግጡ፤

እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤

ክፉ ቀን አምጣባቸው፤

በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።

ሰንበትን ማክበር

19እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ሄደህ የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ በር በሌሎቹም የኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም፤ 20እንዲህም በላቸው፤ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ፤ የይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 21እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳታስገቡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። 22አባቶቻችሁን እንዳዘዝኋቸው ሰንበትን አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ከየቤታችሁ ሸክም ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ።” 23እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብም አላሉም፤ እንዳይሰሙና እንዳይገሠጹም ዐንገታቸውን አደነደኑ። 24ነገር ግን በጥንቃቄ ብትታዘዙኝ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡ፣ የሰንበትንም ቀን ምንም ሳትሠሩ ብትቀድሱት፣ 25በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንታቸው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤ በፈረሶችና በሠረገሎች ተቀምጠው በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ታጅበው ይመጣሉ፤ ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ትሆናለች። 26ሰዎች ከይሁዳ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ ከብንያምም አገር፣ ከቈላውና ከደጋው አገር እንዲሁም ከኔጌቭ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ። 27ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 17:1-27

犹大的罪与罚

1犹大人的罪是用铁笔记录的,用钻石镌刻的,写在了他们心坎上和祭坛角上。 2他们的儿女没有忘记绿树下、高岗上、 3山野间的丘坛和亚舍拉神像。因为他们境内的罪恶,我必使敌人掳掠他们的财宝和神庙。 4他们必失去我赐给他们的产业,被敌人掳到异乡做奴隶,因为他们激起了我的怒火,永难熄灭。”

5耶和华说:

“信靠世人、倚靠血肉之躯、

背叛耶和华的人该受咒诅!

6这样的人毫无福乐,

像沙漠中的灌木。

他要住在旷野中干旱无人的盐碱地。

7信靠耶和华、倚靠耶和华的人有福了!

8这样的人像一棵栽在水边的树,

根扎入水中,

不怕炎热,不怕干旱,

绿叶如荫,不断结果。

9“人心比什么都诡诈,

无可救药,

谁能识透呢?

10我耶和华鉴察人心,

察看人的意念,

按照人的行为报应人。”

11谋取不义之财的人就像孵其他鸟蛋的鹧鸪,

他中年便会失去不义之财,

最后成了愚昧之人。

12我们的圣殿是从太初就矗立在高处的荣耀宝座。

13耶和华啊,你是以色列的盼望。

背弃你的人必蒙羞,

背叛你的人必像写在尘土上的名字一样消逝,

因为他们背弃了耶和华——活水的源泉。

14耶和华啊,

你医治我,我必痊愈;

你拯救我,我必脱离危难,

因为你是我所赞美的。

15人们常讥讽我说:“耶和华说的那些事在哪里?

怎么还没有实现呢?”

16但我并没有逃避牧养你子民的工作,

也没有求你降祸给他们。

你知道我说的每一句话。

17你是我患难中的避难所,

求你不要使我恐惧。

18愿你使那些迫害我的人蒙羞,

不要使我蒙羞;

愿你使他们惊慌,

不要使我惊慌。

求你使他们大祸临头,

彻底毁灭他们。

遵守安息日

19耶和华对我说:“你去站在犹大君王出入的城门前和耶路撒冷的各城门前, 20宣告,‘从这些城门进出的犹大君王、百姓以及耶路撒冷的居民啊,你们都要听耶和华的话。 21耶和华说,如果你们想保住性命,就要小心,不要在安息日带货物进耶路撒冷的城门, 22也不要从家中运出货物,不要在安息日做任何工作。要按照我对你们祖先的吩咐守安息日为圣日。 23然而,他们却不听,毫不理会,顽固不化,不肯受教。

24“‘耶和华说,你们要留心听我的话,在安息日不可运货物进耶路撒冷的城门,不可做任何工作,要守安息日为圣日。 25这样,坐大卫宝座的君王及其官员必乘车骑马和犹大人以及耶路撒冷的居民从城门出入。这城必永远有人居住。 26人们必带着燔祭、平安祭、素祭、乳香和感恩祭从犹大的城邑、耶路撒冷四周、便雅悯地区、丘陵、山区和南地去耶和华的殿。 27但如果你们不听我的话,不守安息日为圣日,仍在安息日运货物进耶路撒冷的城门,我必在各城门点起无法扑灭的大火,烧毁耶路撒冷的宫殿。’”