ኤርምያስ 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 16:1-21

የጥፋት ቀን

1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ 2“በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አይኑሩህ፤” 3በዚህች ምድር ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ እንዲሁም ስለ እናቶቻቸው ስለ አባቶቻቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ 4“በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጕድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።”

5እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “በረከቴን፣ ፍቅሬንና ምሕረቴን ከዚህ ሕዝብ አርቄአለሁና፤ ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ታለቅስና ታዝንም ዘንድ አትሂድ” ይላል እግዚአብሔር6“ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፤ አይለቀስላቸውም፤ ሰውነቱን የሚቧጥጥላቸው፣ ጠጕሩንም የሚላጭላቸው አይገኝም፤ 7ሐዘንተኞችን ለማጽናናት የዕዝን እንጀራ የሚያመጣ አይኖርም፤ አባትም ሆነ እናት የሞተባቸውንም ለማጽናናት መጠጥ የሚያቀርብ አይገኝም።

8“ከእነርሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣት ድግስ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ 9የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’

10“ይህን ሁሉ ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ ሰዎቹ፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ ለምን ዐወጀ? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኀጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁህ፣ 11እንዲህ ትላቸዋለህ፤ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉኝ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ ስላገለገሏቸውና ስላመለኳቸው ነው፤ ትተውኝ ኰበለሉ፤ ሕጌንም አልጠበቁም። 12እናንተም ደግሞ ከአባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አድርጋችኋል፤ እያንዳንዳችሁ እኔን በመታዘዝ ፈንታ የልባችሁን ክፋት ምን ያህል በእልኸኝነት እንደምትከተሉ ተመልከቱ። 13ስለዚህ ከዚህች ምድር አውጥቼ፣ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤ ምሕረትንም አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።’

14“ስለዚህ ሰዎች፣ ‘እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር15“ነገር ግን፣ ‘እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነርሱን ከበተነባቸው ከሌሎች አገሮች ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!’ ይላሉ፤ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋቸው ምድር እመልሳቸዋለሁና።

16“አሁን ግን ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እነርሱም ያጠምዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ ዐዳኞችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ከየተራራው፣ ከየኰረብታው ሁሉ ከየዐለቱም ስንጣቂ ዐድነው ይይዟቸዋል። 17ዐይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፤ በፊቴ የተገለጡ ናቸው፤ ኀጢአታቸውም ከዐይኔ የተሰወረ አይደለም። 18ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለ ሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”

19ብርታቴና ምሽጌ፣

በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤

አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣

ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤

“አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣

የሐሰት አማልክትን ወረሱ።

20ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ያበጃሉን?

ያደርጉ ይሆናል፤ እንዲህ ዐይነቶቹ ግን አማልክት አይደሉም።”

21“ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤

ኀይሌንና ታላቅነቴን፣

አሁን አስተምራቸዋለሁ፤

እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር

እንደ ሆነ ያውቃሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 16:1-21

耶和华降灾难的日子

1耶和华对耶利米说: 2“你不可在这地方娶妻,也不可生儿育女。 3至于在这地方出生的孩子和他们的父母,耶和华说, 4‘他们必死于恶疾,无人哀悼,无人埋葬,他们好像地上的粪便。他们必死于战争和饥荒,尸首必成为飞鸟和走兽的食物。’” 5耶和华对我说:“你不要进入丧家为他们哀悼悲伤,因为我已收回我赐给这百姓的平安、慈爱和怜悯。这是耶和华说的。 6他们无论尊卑都要死在这里,无人埋葬,无人哀悼,也无人为他们的死而割伤身体、剃光头发。 7无人用食物和酒安慰哀悼者,甚至无人给丧父或丧母者一杯安慰酒。 8你不可进入宴乐之家与他们同坐吃喝。” 9以色列的上帝——万军之耶和华说:“在这百姓有生之年,我要使这地方的欢乐声和新郎新娘的欢笑声从他们眼前消失。

10“当你把这些话告诉他们的时候,他们会质问你,‘耶和华为什么给我们降这大灾难?我们有什么罪?我们哪里得罪了我们的上帝耶和华?’ 11你要对他们说,‘耶和华说,你们的祖先背弃我,去跟随、供奉、祭拜别的神明;他们背弃我,不遵守我的律法。 12可是,你们的行为比他们更邪恶,一意孤行,不听从我。 13所以,我要把你们从这里驱逐到你们和你们祖先都不认识的地方,你们在那里要日夜供奉别的神明,因为我不再恩待你们。’”

14耶和华说:“时候将到,那时人不再凭把以色列人带出埃及的耶和华起誓, 15而是凭把他们从流放之地——北方和列国领回来的永活的耶和华起誓。因为我必领他们回到我赐给他们祖先的地方。”

16耶和华说:“看啊,我要召来许多渔夫把他们捕捞上来,我要召来许多猎人去各山岭和岩穴猎取他们。 17因为我鉴察他们的一切行为,他们无法隐藏,他们的罪恶逃不过我的眼晴。 18首先,我要让他们因自己的罪与恶而受加倍的报应,因为他们用没有生命气息的可憎偶像玷污我的土地,使可厌之物充满我的产业。”

19耶和华啊,你是我的力量,

是我的堡垒,

是我患难时的避难所。

万国都要从地极来朝见你,

说:“我们祖先所拜的神像虚假无用,一无是处。

20难道人可以为自己制造神明吗?

其实那些神明并不是真神。”

21耶和华说:“看啊,这一次我要让他们知道我的权柄和能力,让他们知道我是耶和华。”