ኤርምያስ 12 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 12:1-17

የኤርምያስ ማጕረምረም

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣

አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው።

የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?

የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?

2አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰደዋል፤

አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል።

ሁልጊዜ አንተ በአፋቸው ላይ አለህ፤

ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

3ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤

ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ።

እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤

ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤

4ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣12፥4 ወይም ምድሪቱ የምታዝነው

የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው?

ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣

እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤

ደግሞም ሕዝቡ፣

“በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።

የእግዚአብሔር ምላሽ

5“ከእግረኞች ጋር ሮጠህ፣

እነርሱ ካደከሙህ፣

ከፈረሰኞች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?

በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣12፥5 ወይም በሰላም ምድር ከታመንህ

በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

6ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣

እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣

በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤

በመልካም ቢናገሩህም እንኳ

አትመናቸው።

7“ቤቴን እተዋለሁ፤

ርስቴን እጥላለሁ፤

የምወድዳትን እርሷን፣

አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ።

8ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳ

ተነሥታብኛለች፤

በእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤

ስለዚህ ጠላኋት።

9ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት፣

እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን?

ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤

እንዲቀራመቷትም አምጧቸው።

10ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤

ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤

ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣

ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።

11በፊቴ ባድማ፣

ደረቅና ወና ይሆናል፤

መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤

ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና።

12በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣

አጥፊዎች ይሰማራሉ፤

የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣

አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤

የሚተርፍም የለም።

13ስንዴን ይዘራሉ፤ እሾኽን ያጭዳሉ፤

ይደክማሉ፤ የሚያገኙት ግን የለም።

ከእግዚአብሔርም ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣

በመኸራችሁ ውጤት ታፍራላችሁ።”

14እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤ 15ከነቀልኋቸው በኋላ ግን መልሼ እምራቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውንም ወደ ገዛ አገራቸውና ወደ ገዛ ርስታቸው መልሼ አመጣቸዋለሁ። 16የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤ 17የማይሰማኝን ሕዝብ ግን ፈጽሜ እነቅለዋለሁ፤ አጠፋዋለሁም” ይላል እግዚአብሔር

New International Version

Jeremiah 12:1-17

Jeremiah’s Complaint

1You are always righteous, Lord,

when I bring a case before you.

Yet I would speak with you about your justice:

Why does the way of the wicked prosper?

Why do all the faithless live at ease?

2You have planted them, and they have taken root;

they grow and bear fruit.

You are always on their lips

but far from their hearts.

3Yet you know me, Lord;

you see me and test my thoughts about you.

Drag them off like sheep to be butchered!

Set them apart for the day of slaughter!

4How long will the land lie parched

and the grass in every field be withered?

Because those who live in it are wicked,

the animals and birds have perished.

Moreover, the people are saying,

“He will not see what happens to us.”

God’s Answer

5“If you have raced with men on foot

and they have worn you out,

how can you compete with horses?

If you stumble12:5 Or you feel secure only in safe country,

how will you manage in the thickets by12:5 Or the flooding of the Jordan?

6Your relatives, members of your own family—

even they have betrayed you;

they have raised a loud cry against you.

Do not trust them,

though they speak well of you.

7“I will forsake my house,

abandon my inheritance;

I will give the one I love

into the hands of her enemies.

8My inheritance has become to me

like a lion in the forest.

She roars at me;

therefore I hate her.

9Has not my inheritance become to me

like a speckled bird of prey

that other birds of prey surround and attack?

Go and gather all the wild beasts;

bring them to devour.

10Many shepherds will ruin my vineyard

and trample down my field;

they will turn my pleasant field

into a desolate wasteland.

11It will be made a wasteland,

parched and desolate before me;

the whole land will be laid waste

because there is no one who cares.

12Over all the barren heights in the desert

destroyers will swarm,

for the sword of the Lord will devour

from one end of the land to the other;

no one will be safe.

13They will sow wheat but reap thorns;

they will wear themselves out but gain nothing.

They will bear the shame of their harvest

because of the Lord’s fierce anger.”

14This is what the Lord says: “As for all my wicked neighbors who seize the inheritance I gave my people Israel, I will uproot them from their lands and I will uproot the people of Judah from among them. 15But after I uproot them, I will again have compassion and will bring each of them back to their own inheritance and their own country. 16And if they learn well the ways of my people and swear by my name, saying, ‘As surely as the Lord lives’—even as they once taught my people to swear by Baal—then they will be established among my people. 17But if any nation does not listen, I will completely uproot and destroy it,” declares the Lord.