ኤርምያስ 11 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 11:1-23

ያልተከበረው ኪዳን

1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ 2“የዚህን ኪዳን ቃል ስማ፤ ለይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሰዎች ንገራቸው፤ 3የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፤ ‘ለዚህ ኪዳን ቃል የማይታዘዝ ሰው የተረገመ ይሁን፤ 4ይህም ትእዛዝ የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫው ምድጃ ባወጣኋቸው ጊዜ ድምፄን ቢሰሙ፣ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቁ፣ እነርሱ ሕዝቤ፣ እኔም አምላካቸው እንድሆን የሰጠኋቸው ቃል ነው፤ 5ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የገባሁትን መሐላ እፈጽማለሁ።’ ”

እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ አሜን” ብዬ መለስሁ።

6እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባዮች ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘የዚህን ኪዳን ቃል ስሙ፤ አድርጉትም። 7የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ “ታዘዙኝ” በማለት ደጋግሜ አስጠነቀቅኋቸው። 8እነርሱ ግን የክፉ ልባቸውን እልኸኝነት ተከተሉ እንጂ አልታዘዙኝም፤ ጆሯቸውንም ወደ እኔ አላዘነበሉም፤ ስለዚህ እንዲከተሉት አዝዤአቸው ያላደረጉትን የዚህን ኪዳን ርግማን ሁሉ አመጣሁባቸው።’ ”

9እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “በይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዘንድ ዐድማ ተገኝቷል። 10ቃሌን መስማት ወዳልፈለጉት ወደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፤ ሊያገለግሏቸውም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ። የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳን አፈረሱ። 11ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሊያመልጡት የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ወደ እኔ ቢጮኹም አልሰማቸውም። 12የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም። 13ይሁዳ ሆይ፤ የአማልክትህ ቍጥር የከተሞችህን ብዛት ያህል ነው፤ አሳፋሪ ለሆነው ጣዖት፣ ለበኣል ማጠኛ የሠራችኋቸው መሠዊያዎቻችሁ ብዛት የኢየሩሳሌምን መንገዶች ያህል ነው።’

14“በተጨነቁ ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ልመና አታቅርብ፤ አትማጠን።

15“ወዳጄ፣ ከብዙዎች ጋር ተንኰሏን እየሸረበች፣

በቤቴ ውስጥ ምን ጕዳይ አላት?

ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ሊያስቀርልሽ ይችላልን?

እነዚህንስ በመፈጸም፣ ደስተኛ መሆን

ትችያለሽን?”11፥15 ወይም ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ያስቀርልሽ ይችል ይሆን? የዚያን ጊዜ ትደሰቻለሽ

16እግዚአብሔር፣ የተዋበ ፍሬ ያላት፣

የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎሽ ነበር፤

አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣

እሳት ያነድድባታል፤

ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ።

17የእስራኤልና የያዕቆብ ቤት ለበኣል በማጠን ባደረጉት ክፋት ስላስቈጡኝ፣ አንቺን የተከለሽ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉ ነገር ዐውጆብሻል።

በኤርምያስ ላይ የተደረገ ሤራ

18እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያን ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና። 19እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣

“ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ፤

ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤

ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ”

ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።

20ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣

በጽድቅም የምትፈርድ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤

ጕዳዬን ላንተ ትቻለሁና፤

በእነርሱ ላይ የምትፈጽመውን በቀል ልይ።

21“እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 22ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ እኔ እቀጣቸዋለሁ፤ ጕልማሶቻቸው በሰይፍ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ። 23በሚቀጡበት ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ መዓት ስለማመጣ፣ ከእነርሱ የሚተርፍ አንድም አይኖርም።’ ”

Thai New Contemporary Bible

เยเรมีย์ 11:1-23

พันธสัญญาถูกละเมิด

1พระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงเยเรมีย์ความว่า 2“จงฟังข้อกำหนดของพันธสัญญานี้ และแจ้งชนยูดาห์กับผู้ที่อาศัยอยู่ในกรุงเยรูซาเล็ม 3บอกพวกเขาว่าพระยาห์เวห์ พระเจ้าแห่งอิสราเอลตรัสว่า ‘คำสาปแช่งตกแก่ผู้ที่ไม่เชื่อฟังข้อกำหนดของพันธสัญญานี้ 4คือข้อกำหนดซึ่งเราได้บัญชาบรรพบุรุษของพวกเจ้า เมื่อเรานำพวกเขาออกมาจากอียิปต์ ออกจากเตาหลอมเหล็ก’ เรากล่าวว่า ‘จงเชื่อฟังเรา และทำตามสิ่งที่เราสั่งทุกประการ แล้วเจ้าจะเป็นประชากรของเราและเราจะเป็นพระเจ้าของเจ้า 5แล้วเราจะทำให้สำเร็จตามที่เราปฏิญาณไว้กับบรรพบุรุษของเจ้า คือยกดินแดนที่อุดมไปด้วยน้ำนมและน้ำผึ้งให้พวกเขา’ คือดินแดนที่เจ้าครอบครองอยู่ทุกวันนี้”

ข้าพเจ้าทูลตอบว่า “ข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้า ขอให้เป็นเช่นนั้นเถิด11:5 หรืออาเมน

6องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับข้าพเจ้าว่า “จงป่าวประกาศข้อความทั้งหมดนี้ในหัวเมืองต่างๆ ของยูดาห์ และตามถนนหนทางในเยรูซาเล็มว่า ‘จงฟังข้อกำหนดของพันธสัญญานี้และปฏิบัติตาม 7ตั้งแต่เรานำบรรพบุรุษของพวกเจ้าออกมาจากอียิปต์จนถึงทุกวันนี้ เราได้ตักเตือนพวกเขาครั้งแล้วครั้งเล่าว่า “จงเชื่อฟังเรา” 8แต่เขาไม่ฟังและไม่เคยใส่ใจ กลับทำตามทิฐิแห่งใจชั่วของเขา เราจึงนำคำสาปแช่งทั้งปวงตามพันธสัญญามายังเขา เราได้สั่งให้เขาปฏิบัติตาม แต่เขาไม่ยอมทำ’ ”

9แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับข้าพเจ้าว่า “ในหมู่ชนยูดาห์และชนเยรูซาเล็มมีการสมรู้ร่วมคิดกัน 10พวกเขาหวนกลับไปทำบาปตามบรรพบุรุษซึ่งไม่ยอมฟังคำของเรา เขาไปปรนนิบัตินมัสการพระอื่นๆ ทั้งพงศ์พันธุ์อิสราเอลและพงศ์พันธุ์ยูดาห์ ละเมิดพันธสัญญาระหว่างเรากับบรรพบุรุษของเขา 11ฉะนั้นองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า ‘เราจะนำภัยพิบัติมายังเขา ซึ่งเขาจะหนีไม่พ้น ถึงแม้เขาอ้อนวอนเรา เราก็จะไม่ฟัง 12หัวเมืองต่างๆ ของยูดาห์และชาวกรุงเยรูซาเล็มจะไปสวดอ้อนวอนเทพเจ้าต่างๆ ซึ่งตนเผาเครื่องหอมถวาย แต่พระเหล่านั้นจะไม่ช่วยพวกเขาเลยเมื่อภัยพิบัติมาถึง 13ยูดาห์เอ๋ย เจ้ามีเทพเจ้าหลายองค์เหมือนที่มีหลายเมืองเชียวนะ และแท่นบูชาที่เจ้าก่อขึ้นเพื่อเผาเครื่องหอมแก่พระบาอัลอันน่าอดสูก็มีมากมาย เหมือนถนนหนทางของเยรูซาเล็ม’

14“อย่าอธิษฐานเผื่อชนชาตินี้ ไม่ต้องอ้อนวอนหรือร้องขอเพื่อพวกเขา เพราะเราจะไม่ฟังเมื่อเขาร้องเรียกเราในยามทุกข์ยากลำบาก

15“ผู้เป็นที่รักของเรามาทำอะไรอยู่ในวิหารของเรานี้?

ในเมื่อนางทำตามแผนการชั่วหลายอย่าง

เครื่องสัตวบูชาจะช่วยให้เจ้าพ้นโทษทัณฑ์ได้หรือ?

เจ้าจึงหลงระเริง

ในความชั่วของเจ้า”

16องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสเรียกเจ้าว่าต้นมะกอกซึ่งงามดี

มีผลดกงาม

แต่ด้วยเสียงกึกก้องของพายุใหญ่

พระเจ้าจะให้ไฟเผามัน

และกิ่งก้านของมันก็หักโค่น

17พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ผู้ปลูกเจ้าทรงประกาศให้ภัยพิบัติตกแก่เจ้า เนื่องจากพงศ์พันธุ์อิสราเอลและยูดาห์ทำชั่ว ยั่วยุพระพิโรธโดยเผาเครื่องหอมถวายพระบาอัล

เยเรมีย์ถูกปองร้าย

18องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงเผยให้ข้าพเจ้าทราบถึงแผนการของพวกเขา ทรงให้ข้าพเจ้าทราบว่าพวกเขากำลังทำอะไรอยู่ 19ข้าพเจ้าเป็นเหมือนลูกแกะเชื่องๆ ถูกพาไปฆ่า ข้าพเจ้าไม่รู้ว่าพวกเขาคบคิดกันจะทำร้ายข้าพเจ้า เขากล่าวว่า

“ให้เราทำลายทั้งต้นและผลของมัน

ให้เรามาช่วยกันกำจัดเขาไปจากโลกนี้

เพื่อจะได้ไม่มีใครจดจำชื่อของเขาได้อีก”

20แต่พระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ผู้ทรงตัดสินอย่างเที่ยงธรรม

และทรงพิสูจน์ความคิดจิตใจ

โปรดให้ข้าพระองค์เห็นการแก้แค้นของพระองค์ตกแก่พวกเขา

เพราะข้าพระองค์มอบเรื่องของข้าพระองค์ไว้กับพระองค์

21“ฉะนั้น องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสเกี่ยวกับชาวอานาโธทที่มุ่งเอาชีวิตของเจ้าและขู่ว่า ‘อย่าเผยพระวจนะในพระนามขององค์พระผู้เป็นเจ้า มิฉะนั้นเจ้าต้องตายด้วยน้ำมือของเรา’ 22ฉะนั้นพระยาห์เวห์ผู้ทรงฤทธิ์ตรัสว่า ‘เราจะลงโทษพวกเขา คนหนุ่มๆ จะตายในสงคราม ลูกชายลูกสาวของพวกเขาจะตายเพราะอดอยาก 23จะไม่มีคนสักหยิบมือเดียวเหลือรอด เพราะเราจะนำภัยพิบัติมาสู่ชาวอานาโธทในปีแห่งการลงโทษพวกเขา’ ”