1የኬልቅያስ ልጅ፣ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አባቱ በብንያም አገር በዓናቶት ከሚገኙት ካህናት አንዱ ነበረ። 2የእግዚአብሔር ቃል የይሁዳ ንጉሥ፣ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 3ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ንግሠ ዘመን፤ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ንግሠ ዘመን፤ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት መጨረሻ ድረስ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ሄደበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።
የኤርምያስ መጠራት
4የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፤
5“በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤
ከመወለድህ በፊት ለየሁህ፤1፥5 ወይም መረጥሁህ
ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።”
6እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ።
7እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ትናገራለህ፤ 8እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር።
9እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰና እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ፤ 10እንግዲህ፣ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድትገለብጥ፣ እንድታንጽና እንድትተክል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾምሁህ።”
11የእግዚአብሔር ቃል፣ “ኤርምያስ ሆይ፣ ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ።
እኔም፣ “የለውዝ በትር አያለሁ” አልሁ።
12እግዚአብሔርም፣ “ትክክል አይተሃል፤ ቃሌን እፈጽመው ዘንድ እተጋለሁና”1፥12 እተጋለሁ ለሚለው የዕብራይስጡ አነባበብ የለውዝ በትር ከሚለው ጋር ይመሳሰላል። አለኝ።
13ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ።
እኔም፣ “አንድ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ ነው” አልሁ።
14እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ከሰሜን በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ድንገት መዓት ይወርድባቸዋል። 15እነሆ፤ የሰሜን መንግሥታትን ሕዝቦች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤
“ንጉሦቻቸው ይመጣሉ፤
ዙፋናቸውን በኢየሩሳሌም መግቢያ በሮች፣
በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉ፣
በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ይዘረጋሉ።
16እኔን በመተው ክፋት ስለ ሠሩ፣
ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑ፣
እጆቻቸው የሠሯቸውን ስላመለኩ፣
በሕዝቤ ላይ ፍርድን ዐውጄአለሁ።
17“አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥተህም ያዘዝሁን ሁሉ ንገራቸው፤ አትፍራቸውም፤ አለዚያ በፊታቸው አስፈራሃለሁ። 18እነሆ፤ ዛሬ በመላዪቱ ምድር ላይ አስነሣሃለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ነገሥታት፣ አለቆቿን፣ ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ መቋቋም እንድትችል የተመሸገ ከተማ፣ የብረት ምሰሶና የናስ ቅጥር አድርጌሃለሁ። 19ይዋጉሃል፤ ዳሩ ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም” ይላል እግዚአብሔር።
1希勒迦的儿子耶利米是便雅悯境内亚拿突城的一位祭司,以下是他的话。 2犹大王亚们的儿子约西亚执政第十三年,耶和华的话传给了耶利米。 3从犹大王约西亚的儿子约雅敬开始执政,一直到约西亚的另一个儿子西底迦做犹大王的第十一年五月,就是耶路撒冷的居民被掳之日,耶和华的话常常传给耶利米。
耶利米蒙召
4耶和华对我说:
5“我还没有使你在母腹中成形,就认识你;
你还未出生,我已使你圣洁,
立你做万国的先知。”
6我回答说:“主耶和华啊,我太年轻,不懂得怎样说话。” 7耶和华却说:
“不要说你太年轻,
我派你去谁那里,
你就去谁那里;
我吩咐你说什么,
你就说什么。
8谁也不要怕,
因为我与你同在,
我必拯救你。
这是耶和华说的。”
9然后,耶和华伸手摸我的口,对我说:“看啊,我已把我的话放在你口中。 10今日,我派你到列邦列国去拔掉、拆除、毁灭、推翻、建造和栽植。”
两个异象
11耶和华又对我说:“耶利米,你看见什么?”我说:“我看见一根杏树枝。” 12耶和华说:“不错。我必实现我说过的话。”
13耶和华又对我说:“你看见什么?”我回答说:“我看见一锅煮沸的水,从北方倾倒下来。” 14耶和华说:“不错。因为有灾祸要从北方降临到这地方的一切居民。 15我要召来北方各国,他们要在耶路撒冷的城门自立王位,攻打耶路撒冷周围的城墙和犹大各城邑。这是耶和华说的。 16我要审判他们,因为他们犯罪作恶,背弃我,给别的神明烧香,又跪拜自己制造的神像。 17现在,你要做好准备,去把我吩咐你的话告诉他们。不要惧怕他们,不然我将使你在他们面前充满恐惧。 18看啊,今天我已使你成为坚城、铁柱、铜墙,来对抗整个犹大,对抗犹大的君王、首领、祭司和境内的众民。 19他们必攻击你,但绝不能胜过你,因为我与你同在,我必拯救你。这是耶和华说的。”