ኢዮብ 38 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 38:1-41

እግዚአብሔር ተናገረ

1እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤

2“ዕውቀት በጐደለው ቃል፣

ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው?

3እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤

እኔ ልጠይቅህ፣

አንተም መልስልኝ።

4“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?

በርግጥ የምታስተውል ከሆንህ ንገረኝ።

5ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?

በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

6መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?

የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

7ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣

መላእክትም38፥7 ወይም፣ የእግዚአብሔር ልጆች እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።

8“ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣

በር የዘጋበት ማን ነው?

9ደመናውን ልብሱ፣

ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣

10ድንበር ወሰንሁለት፤

መዝጊያና መወርወሪያውን አበጀሁለት።

11‘እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ፤ ማለፍ ግን አትችልም፤

የዕቡይ ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ አልሁት።

12“ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዝዘህ ታውቃለህን?

ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?

13በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣

ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?

14ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ቅርጿ ይወጣል፤

ቅርጿ እንደ ልብስ ቅርጽ ጐልቶ ይታያል።

15ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤

ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል።

16“ወደ ባሕር ምንጭ ወርደህ ታውቃለህን?

ወይስ ወደ ጥልቀቱ ገብተህ በመሠረቱ ላይ ተመላልሰሃልን?

17የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን?

የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን?

18የምድርን ስፋት ታውቃለህን?

ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።

19“ወደ ብርሃን መኖሪያ የሚያደርሰው መንገድ የትኛው ነው?

የጨለማ መኖሪያስ ወዴት ነው?

20ወደ ማደሪያቸው ልትወስዳቸው ትችላለህን?

የመኖሪያቸውን መንገድ ታውቃለህ?

21ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣

አንተስ በርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!

22“ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን?

የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን?

23ይኸውም ለመከራ ጊዜ፣

ለጦርነትና ለውጊያ ቀን ያስቀመጥሁት ነው።

24መብረቅ ወደሚሠራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣

የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው?

25ለዝናብ መውረጃን፣

ለመብረቅም መንገድን ያበጀ ማን ነው?

26በዚህም ማንም የማይኖርበትን ምድር፣

ሰውም የሌለበትን ምድረ በዳ የሚያጠጣ፣

27ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣

ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?

28ዝናብ አባት አለውን?

የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?

29በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል?

የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?

30ውሆች እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤

የጥልቁ ገጽ እንደ በረዶ ይጋገራል።

31“ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጕም፣

ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን?

32ማዛሮት የተባለውን የከዋክብት ክምችት በወቅቱ38፥32 ወይም በወቅቱ የሚወጣ የንጋት ኮከብ ልታወጣ፣

ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ?

33የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ?

ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?

34“ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣

ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?

35መብረቆችን መስደድ ትችላለህ?

እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል?

36ለልብ38፥36 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ጥበብን፣

ለአእምሮም ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው?

37ትቢያ ሲጠጥር፣

ጓሎችም እርስ በርስ ሲጣበቁ፣

38ደመናትን ለመቍጠር ጥበብ ያለው ማን ነው?

የሰማያትንስ የውሃ ገንቦ ዘንበል ማድረግ ማን ይችላል?

39“ለአንበሳዪቱ ዐድነህ ግዳይ ታመጣለህን?

የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን?

40እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤

በደን ውስጥም ይጋደማሉ።

41ልጆቿ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፣

ምግብ ዐጥተው ሲንከራተቱ፣

ለቍራ መብልን የሚሰጥ ማን ነው?

Ketab El Hayat

أيوب 38:1-41

الله يتكلم

1ثُمَّ قَالَ الرَّبُّ لأَيُّوبَ مِنَ الْعَاصِفَةِ: 2«مَنْ ذَا الَّذِي يُظْلِمُ الْقَضَاءَ بِكَلامٍ مُجَرَّدٍ مِنَ الْمَعْرِفَةِ؟ 3اشْدُدْ حَقَوَيْكَ كَرَجُلٍ لأَسْأَلَكَ فَتُجِيبَنِي 4أَيْنَ كُنْتَ عِنْدَمَا أَسَّسْتُ الأَرْضَ؟ أَخْبِرْنِي إِنْ كُنْتَ ذَا حِكْمَةٍ. 5مَنْ حَدَّدَ مَقَايِيسَهَا، إِنْ كُنْتَ حَقّاً تَعْرِفُ؟ أَوْ مَنْ مَدَّ عَلَيْهَا خَيْطَ الْقِيَاسِ؟ 6عَلَى أَيِّ شَيْءٍ اسْتَقَرَّتْ قَوَاعِدُهَا؟ وَمَنْ وَضَعَ حَجَرَ زَاوِيَتِهَا؟ 7بَيْنَمَا كَانَتْ كَوَاكِبُ السَّمَاءِ تَتَرَنَّمُ مَعاً وَمَلائِكَةُ اللهِ تَهْتِفُ بِفَرَحٍ.

8مَنْ حَجَزَ الْبَحْرَ بِبَوَّابَاتٍ، عِنْدَمَا انْدَفَقَ مِنْ رَحِمِ الأَرْضِ، 9حِينَ جَعَلْتُ السُّحُبَ لِبَاساً لَهُ وَالظُّلْمَةَ قِمَاطَهُ، 10عِنْدَمَا عَيَّنْتُ لَهُ حُدُوداً، وَأَثْبَتُّ بَوَّابَاتِهِ وَمَغَالِيقَهُ فِي مَوَاضِعِهَا، 11وَقُلْتُ لَهُ: إِلَى هُنَا تُخُومُكَ فَلا تَتَعَدَّاهَا، وَهُنَا يَتَوَقَّفُ عُتُوُّ أَمْوَاجِكَ؟

12هَلْ أَمَرْتَ مَرَّةً الصُّبْحَ فِي أَيَّامِكَ، وَأَرَيْتَ الْفَجْرَ مَوْضِعَهُ، 13لِيَقْبِضَ عَلَى أَكْنَافِ الأَرْضِ وَيَنْفُضَ الأَشْرَارَ مِنْهَا؟ 14تَتَشَكَّلُ كَطِينٍ تَحْتَ الْخَاتَمِ، وَتَبْدُو مَعَالِمُهَا كَمَعَالِمِ الرِّدَاءِ. 15يَمْتَنِعُ النُّورُ عَنِ الأَشْرَارِ، وَتَتَحَطَّمُ ذِرَاعُهُمُ الْمُرْتَفِعَةُ.

16هَلْ غُصْتَ إِلَى يَنَابِيعِ الْبَحْرِ، أَمْ دَلَفْتَ إِلَى مَقَاصِيرِ اللُّجَجِ؟ 17هَلِ اطَّلَعْتَ عَلَى أَبْوَابِ الْمَنِيَّةِ، أَمْ رَأَيْتَ بَوَّابَاتِ ظِلالِ الْمَوْتِ؟ 18هَلْ أَحَطْتَ بِعَرْضِ الأَرْضِ؟ أَخْبِرْنِي إِنْ كُنْتَ بِكُلِّ هَذَا عَلِيماً.

19أَيْنَ الطَّرِيقُ إِلَى مَقَرِّ النُّورِ، وَأَيْنَ مُسْتَقَرُّ الظُّلْمَةِ؟ 20حَتَّى تَقُودَهَا إِلَى تُخُومِهَا وَتَعْرِفَ سُبُلَ مَسْكَنِهَا؟ 21حَقّاً أَنْتَ تَعْرِفُهَا لأَنَّكَ آنَئِذٍ كُنْتَ قَدْ وُلِدْتَ وَعِشْتَ أَيَّاماً طَوِيلَةً!

22هَلْ دَخَلْتَ إِلَى مَخَازِنِ الثَّلْجِ، أَمْ رَأَيْتَ خَزَائِنَ الْبَرَدِ، 23الَّتِي ادَّخَرْتُهَا لأَوْقَاتِ الضِّيقِ، لِيَوْمِ الْمَعْرَكَةِ وَالْحَرْبِ؟ 24مَا هُوَ السَّبِيلُ إِلَى مَوْضِعِ انْتِشَارِ النُّورِ، أَوْ أَيْنَ تَتَوَزَّعُ الرِّيحُ الشَّرْقِيَّةُ عَلَى الأَرْضِ؟ 25مَنْ حَفَرَ قَنَوَاتٍ لِسُيُولِ الْمَطَرِ، وَمَمَرّاً لِلصَّوَاعِقِ، 26لِيُمْطِرَ عَلَى أَرْضٍ مُقْفِرَةٍ لَا إِنْسَانَ فِيهَا، 27لِيُرْوِيَ الأَرْضَ الْخَرِبَةَ، وَلِيَسْتَنْبِتَ الأَرْضَ عُشْباً؟

28هَلْ لِلْمَطَرِ أَبٌ؟ وَمَنْ أَنْجَبَ قَطَرَاتِ النَّدَى؟ 29وَمِنْ أَيِّ أَحْشَاءٍ خَرَجَ الْجَمَدُ، وَمَنْ وَلَدَ صَقِيعَ السَّمَاءِ؟ 30تَتَجَلَّدُ الْمِيَاهُ كَحِجَارَةٍ وَيَتَجَمَّدُ وَجْهُ الْغَمْرِ.

31هَلْ تَرْبِطُ سَلاسِلَ الثُّرَيَّا، أَمْ تَفُكُّ عُقَدَ الْجَوْزَاءِ؟ 32هَلْ تَهْدِي كَوَاكِبَ الْمَنَازِلِ فِي فُصُولِهَا، أَمْ تَهْدِي النَّعْشَ مَعَ بِنَاتِهِ؟ 33هَلْ تَعْرِفُ أَحْكَامَ السَّمَاوَاتِ، أَمْ أَسَّسْتَ سُلْطَتَهَا عَلَى الأَرْضِ؟ 34هَلْ تَرْفَعُ صَوْتَكَ آمِراً الْغَمَامَ فَيَغْمُرَكَ فَيْضُ الْمِيَاهِ؟ 35هَلْ فِي وُسْعِكَ أَنْ تُطْلِقَ الْبُرُوقَ فَتَمْضِيَ وَتَقُولَ لَكَ: هَا نَحْنُ طَوْعَ أَمْرِكَ؟ 36مَنْ أَضْفَى عَلَى الْغُيُومِ حِكْمَةً وَأَنْعَمَ عَلَى الضَّبَابِ بِالْفَهْمِ؟ 37مَنْ لَهُ الْحِكْمَةُ لِيُحْصِيَ النُّجُومَ، وَمَنْ يَصُبُّ الْمَاءَ مِنْ مَيَازِيبِ السَّمَاءِ، 38حِينَ يَتَلَبَّدُ التُّرَابُ وَتَتَمَاسَكُ كُتَلُ الطِّينِ؟

عجائب عالم الحيوان

39هَلْ تَصْطَادُ الْفَرِيسَةَ لِلَّبُؤَةِ، أَمْ تُشْبِعُ جُوعَ الأَشْبَالِ، 40حِينَ تَتَرَبَّصُ فِي الْعَرَائِنِ وَتَكْمُنُ فِي أَوْجَارِهَا؟ 41مَنْ يُزَوِّدُ الْغُرَابَ بِصَيْدِهِ إِذْ تَنْعَبُ فِرَاخُهُ مُسْتَغِيثَةً بِاللهِ، وَتَهِيمُ لاِفْتِقَارِهَا إِلَى الْقُوتِ؟