ኢዮብ 35 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 35:1-16

1ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤

2“ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’35፥2 ወይም፣ ጽድቄ ከእግዚአብሔር ጽድቅ ይበልጣል ማለትህ፣

ትክክል ይመስልሃልን?

3ደግሞ ‘ያገኘሁት35፥3 ወይም፣ ያገኘኸው ጥቅም ምንድን ነው?

ኀጢአት ባለ መሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።

4“ለአንተና አብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣

መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።

5ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤

ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።

6ኀጢአትህስ ቢበዛ እርሱን ምን ትጐዳዋለህ?

ኀጢአትህስ ቢበዛ ምን ያደርገዋል?

7ጻድቅ ብትሆንም ለእርሱ ምን ትሰጠዋለህ?

ከእጅህስ ምን ይቀበላል?

8ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤

ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።

9“ሰው ከጭቈና ብዛት የተነሣ ይጮኻል፤

ከኀያሉም ክንድ ሥር ለመውጣት ለርዳታ ይጣራል።

10ነገር ግን እንዲህ የሚል የለም፤ ‘ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው?

በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፣

11ከምድር እንስሳት ይልቅ የሚያስተምረን፣

ከሰማይ ወፎችም ይልቅ ጠቢባን የሚያደርገን፣ እርሱ የት አለ?’

12ከዐመፀኞች ትዕቢት የተነሣ፣

ሰዎች ሲጮኹ አይመልስላቸውም፤

13በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤

ሁሉን የሚችል አምላክ አያዳምጣቸውም።

14ጕዳይህን ፊቱ አቅርበህ፣

ብዙ ጠብቀኸው፣

ግን እንዳላየኸው ስትናገር፣

ታዲያ፣ አንተን እንዴት ይስማህ!

15ደግሞም፣ ቍጣው ቅጣት እንደማያስከትል፣

ኀጢአትንም35፥15 ሴማኮስ፣ ቴዎዴሽንና ቩልጌት ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ነገር ግን በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም ከቍጥር እንደማያስገባ ተናግረሃል።

16ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፤

ዕውቀት አልባ ቃላትም ያበዛል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约伯记 35:1-16

1以利户又说:

2“你在上帝面前自以为义,

你认为这合理吗?

3你还说,‘这与我何干?

我不犯罪又有何益处?’

4我要答复你和你的朋友。

5要抬头观看诸天,

瞻望头顶的穹苍。

6你若犯罪,与上帝何妨?

你若罪恶累累,对祂有何影响?

7你若为人公义,与祂何益?

祂从你手上能得什么好处?

8你的罪恶只能伤害你的同类,

你的公义只能令世人受益。

9“人们因饱受压迫而呼求,

因强权者的压制而求救。

10但无人问,‘创造我的上帝在哪里?

祂使人夜间欢唱,

11使我们比地上的走兽聪明,

比天上的飞鸟有智慧。’

12他们因恶人的嚣张而呼求,

上帝却不回答。

13上帝必不垂听虚妄的呼求,

全能者必不理会。

14更何况你说你看不见祂,

你的案子已呈上,在等祂裁决。

15你还说祂没有发怒降罚,

也不理会罪恶。

16约伯啊,这尽是虚言,

是一大堆无知的话。”