ኢዮብ 34 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 34:1-37

1ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤

2“እናንት ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤

ዐዋቂዎችም አድምጡኝ።

3ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣

ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል።

4የሚበጀንን እንምረጥ፣

መልካሙንም አብረን እንወቅ።

5“ኢዮብ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤

እግዚአብሔር ግን ፍትሕ ነሣኝ፤

6እውነተኛ ብሆንም፣

እንደ ውሸታም ተቈጥሬአለሁ፤

በደል ባይኖርብኝም፣

በማይፈወስ ቍስል ተመትቻለሁ።’

7ፌዝን እንደ ውሃ የሚጠጣት፣

እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?

8ከክፉ አድራጊዎች ጋር ይተባበራል፤

ከኀጢአተኞችም ጋር ግንባር ይፈጥራል።

9‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣

ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።

10“ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤

ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣

በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።

11ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤

እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል።

12በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤

ሁሉን የሚችል አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።

13ምድርን እንዲገዛ የሾመው አለን?

የዓለምስ ሁሉ ባለቤት ያደረገው ማን ነው?

14እርሱ መንፈሱን መልሶ ቢወስድ፣

እስትንፋሱንም ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣

15ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣

ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።

16“ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤

እኔ የምለውንም አድምጥ።

17ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን?

አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?

18ነገሥታትን ‘የማትረቡ ናችሁ፣’

መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’

የሚላቸው እርሱ አይደለምን?

19ሁሉም የእጁ ሥራ ስለሆኑ፣

እርሱ ለገዦች አያደላም፤

ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።

20እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤

ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤

ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።

21“ዐይኖቹ የሰውን አካሄድ ይመለከታሉ፤

ርምጃውንም ሁሉ ይከታተላሉ።

22ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፣

ጨለማ ስፍራ ወይም የሞት ጥላ የለም።

23ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣

እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።

24ያለ ምንም ጥያቄ ኀያላንን ያንኰታኵታል፤

ሌሎችንም በቦታቸው ይሾማል።

25እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣

በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤

እነርሱም ይደቅቃሉ።

26ስለ ክፋታቸውም፣

በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤

27እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤

መንገዱንም ችላ ብለዋል።

28የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤

የመከረኞችን ጩኸት ሰማ።

29እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?

ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?

እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤

30ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣

ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።

31“ሰው ለእግዚአብሔር እንዲህ ቢል የተሻለ ነበር፤

‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤

32ማየት ያልቻልሁትን አስተምረኝ፤

ኀጢአት ሠርቼ እንደ ሆነም፣ ደግሜ አልሠራም።’

33ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤

እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን?

መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤

እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።

34“አስተዋዮች ይናገራሉ፤

የሚሰሙኝም ጠቢባን እንዲህ ይሉኛል፤

35‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤

ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’

36ምነው ኢዮብ እስከ መጨረሻ በተፈተነ ኖሮ!

እንደ ክፉ ሰው መልሷልና፤

37በኀጢአቱም ላይ ዐመፅን ጨምሯል፤

በመካከላችን ሆኖ በንቀት አጨብጭቧል፤

በእግዚአብሔርም ላይ ብዙ ተናግሯል።”

Ketab El Hayat

أيوب 34:1-37

1وَأَضَافَ أَلِيهُو قَائِلاً: 2«اسْتَمِعُوا إِلَى أَقْوَالِي أَيُّهَا الْحُكَمَاءُ، وَأَصْغُوا إِلَيَّ يَا ذَوِي الْمَعْرِفَةِ، 3لأَنَّ الأُذُنَ تُمَحِّصُ الأَقْوَالَ كَمَا يَتَذَوَّقُ الْحَنَكُ الطَّعَامَ. 4لِنَتَدَاوَلْ فِيمَا بَيْنَنَا لِنُمَيِّزَ مَا هُوَ أَصْوَبُ لَنَا، وَنَتَعَلَّمَ مَعاً مَا هُوَ صَالِحٌ.

5يَقُولُ أَيُّوبُ: ’إِنِّي بَارٌّ، وَلَكِنَّ اللهَ قَدْ تَنَكَّرَ لِحَقِّي، 6وَمَعَ أَنِّي مُحِقٌّ فَأَنَا أُدْعَى كَاذِباً، وَمَعَ أَنِّي بَرِيءٌ فَإِنَّ سَهْمَهُ أَصَابَنِي بِجُرْحٍ مُسْتَعْصٍ‘. 7فَمَنْ هُوَ نَظِيرُ أَيُّوبَ الَّذِي يَجْرَعُ الْهُزْءَ كَالْمَاءِ، 8يُوَاظِبُ عَلَى مُعَاشَرَةِ فَاعِلِي الإِثْمِ، وَيَأْتَلِفُ مَعَ الأَشْرَارِ، 9لأَنَّهُ يَقُولُ: لَا يَنْتَفِعُ الإِنْسَانُ شَيْئاً مِنْ إِرْضَاءِ اللهِ.

10لِذَلِكَ أَصْغُوا إِلَيَّ يَا ذَوِي الْفَهْمِ: حَاشَا لِلهِ أَنْ يَرْتَكِبَ شَرّاً أَوْ لِلْقَدِيرِ أَنْ يَقْتَرِفَ خَطَأً، 11لأَنَّهُ يُجَازِي الإِنْسَانَ بِمُوْجِبِ أَعْمَالِهِ، وَبِمُقْتَضَى طَرِيقِهِ يُحَاسِبُهُ. 12إِذْ حَاشَا لِلهِ أَنْ يَرْتَكِبَ شَرّاً، وَالْقَدِيرِ أَنْ يُعَوِّجَ الْقَضَاءَ. 13مَنْ وَكَّلَ اللهَ بِالأَرْضِ؟ وَمَنْ عَهِدَ إِلَيْهِ بِالْمَسْكُونَةِ؟ 14إِنِ اسْتَرْجَعَ رُوحَهُ إِلَيْهِ وَاسْتَجْمَعَ نَسَمَتَهُ إِلَى نَفْسِهِ 15فَالْبَشَرُ جَمِيعاً يَفْنَوْنَ مَعاً، وَيَعُودُ الإِنْسَانُ إِلَى التُّرَابِ.

16فَإِنْ كُنْتَ مِنْ أُولِي الْفَهْمِ، فَاسْتَمِعْ إِلَى هَذَا، وَأَنْصِتْ لِمَا أَقُولُ: 17أَيُمْكِنُ لِمُبْغِضِ الْعَدْلِ أَنْ يَحْكُمَ؟ أَتَدِينُ الْبَارَّ الْقَدِيرَ؟ 18الَّذِي يَقُولُ لِلْمَلِكِ: أَنْتَ عَدِيمُ الْقِيمَةِ، وَلِلنُّبَلاءِ: أَنْتُمْ أَشْرَارٌ؟ 19الَّذِي لَا يُحَابِي الأُمَرَاءَ، وَلا يُؤْثِرُ الأَغْنِيَاءَ عَلَى الْفُقَرَاءِ، لأَنَّهُمْ جَمِيعاً عَمَلُ يَدَيْهِ. 20فِي لَحْظَةٍ يَمُوتُونَ، تُفَاجِئُهُمُ الْمَنِيَّةُ فِي مُنْتَصَفِ اللَّيْلِ، تَتَزَعْزَعُ الشُّعُوبُ فَيَفْنَوْنَ، وَيُسْتَأْصَلُ الأَعِزَّاءُ مِنْ غَيْرِ عَوْنٍ بَشَرِيٍّ، 21لأَنَّ عَيْنَيْهِ عَلَى طُرُقِ الإِنْسَانِ وَهُوَ يُرَاقِبُ خَطْوَاتِهِ. 22لَا تُوجَدُ ظُلْمَةٌ، وَلا ظِلُّ مَوْتٍ، يَتَوَارَى فِيهِمَا فَاعِلُو الإِثْمِ، 23لأَنَّهُ لَا يَحْتَاجُ أَنْ يَفْحَصَ الإِنْسَانَ مَرَّةً أُخْرَى حَتَّى يَدْعُوهُ لِلْمُثُولِ أَمَامَهُ فِي مُحَاكَمَةٍ. 24يُحَطِّمُ الأَعِزَّاءَ مِنْ غَيْرِ إِجْرَاءِ تَحْقِيقٍ، وَيُقِيمُ آخَرِينَ مَكَانَهُمْ 25لِذَلِكَ هُوَ مُطَّلِعٌ عَلَى أَعْمَالِهِمْ، فَيُطِيحُ بِهِمْ فِي اللَّيْلِ فَيُسْحَقُونَ. 26يَضْرِبُهُمْ لِشَرِّهِمْ عَلَى مَرْأَى مِنَ النَّاسِ، 27لأَنَّهُمُ انْحَرَفُوا عَنِ اتِّبَاعِهِ، وَلَمْ يَتَأَمَّلُوا فِي طُرُقِهِ، 28فَكَانُوا سَبَباً فِي ارْتِفَاعِ صُرَاخِ الْبَائِسِ إِلَيْهِ، وَاللهُ يَسْتَجِيبُ اسْتِغَاثَةَ الْمِسْكِينِ. 29فَإِنْ هَيْمَنَ بِسَكِينَتِهِ فَمَنْ يَدِينُهُ؟ وَإِنْ وَارَى وَجْهَهُ فَمَنْ يُعَايِنُهُ؟ سَوَاءٌ أَكَانُوا شَعْباً أَمْ فَرْداً 30لِكَيْ لَا يَسُودَ الْفَاجِرُ، لِئَلّا تَعْثُرَ الأُمَّةُ.

31هَلْ قَالَ أَحَدٌ للهِ: لَقَدْ تَحَمَّلْتُ الْعِقَابَ فَلَنْ أَعُودَ إِلَى الإِسَاءَةِ؟ 32عَلِّمْنِي مَا لَا أَرَاهُ، وَإِنْ كُنْتُ قَدْ أَثِمْتُ فَإِنَّنِي عَنْهُ أَرْتَدِعُ. 33أَيُجْزِيكَ اللهُ إِذاً بِمُقْتَضَى رَأْيِكَ إِذَا رَفَضْتَ التَّوْبَةَ؟ لأَنَّ عَلَيْكَ أَنْتَ أَنْ تَخْتَارَ لَا أَنَا، فَأَخْبِرْنِي بِمَا تَعْرِفُ. 34إِنَّ ذَوِي الْفَهْمِ يُعْلِنُونَ، وَالْحُكَمَاءَ الَّذِينَ يُنْصِتُونَ إِلَى كَلامِي يَقُولُونَ لِي: 35إِنَّ أَيُّوبَ يَتَكَلَّمُ بِجَهْلٍ، وَكَلامُهُ يَفْتَقِرُ إِلَى التَّعَقُّلِ. 36يَا لَيْتَ أَيُّوبَ يُمْتَحَنُ أَقْسَى امْتِحَانٍ، لأَنَّهُ أَجَابَ كَمَا يُجِيبُ أَهْلُ الشَّرِّ. 37لَكِنَّهُ أَضَافَ إِلَى خَطِيئَتِهِ عِصْيَاناً، إِذْ يُصَفِّقُ بَيْنَنَا بِاحْتِقَارٍ، مُثَرْثِراً بِأَقْوَالٍ ضِدَّ اللهِ!»