ኢዮብ 33 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 33:1-33

1“አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤

የምለውንም ሁሉ አድምጥ።

2እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤

አንደበቴም ይናገራል።

3ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤

ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።

4የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤

ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።

5የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤

ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።

6በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤

የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።

7እኔን መፍራት የለብህም፤

እጄም ሊከብድብህ አይገባም።

8“በርግጥ የተናገርኸውን ሰምቻለሁ፤

እንዲህም ስትል አድምጫለሁ፤

9‘ኀጢአት የሌለብኝ ንጹሕ ነኝ፤

ከበደል ነጻ ነኝ፤ እድፈትም የለብኝም፤

10እግዚአብሔር ግን ሰበብ ፈልጎብኛል፤

እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል፤

11እግሬን በግንድ አጣብቋል፤

እንቅስቃሴዬንም ሁሉ ይከታተላል።’

12“ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣

ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ።

13የሰውን አቤቱታ33፥13 ወይም፣ ለምግባሩ ምንም እንደማይመልስ እንደማይሰማ፣

ለምን ታማርርበታለህ?

14ሰው ባያስተውለውም፣

እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤

15ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣

ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣

በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል።

16በጆሯቸው ይናገራል፤

በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤

17ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤

ከትዕቢት ይጠብቃል፤

18ነፍሱን ከጕድጓድ፤33፥18 ወይም፣ ነፍሱን ከመቃብር

ሕይወቱንም ከሰይፍ33፥18 ወይም፣ ወንዝን ከመሻገር ጥፋት ያድናል።

19ደግሞም ሰው ታምሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣

በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤

20ያኔም ሕይወቱ መብልን ትጠላለች፤

ነፍሱም ምርጥ ምግብን ትጠየፋለች።

21እንዳልነበረ ሆኖ ሥጋው ይመነምናል፤

ተሸፍኖ የነበረው ዐጥንቱም ገጥጦ ይወጣል።

22ነፍሱ ወደ ጕድጓድ፣33፥22 ወይም፣ ነፍሱ ወደ ሞት

ሕይወቱም ወደ ሞት33፥22 ወይም፣ ወደ ሙታን መልእክተኞች ትቀርባለች።

23“ሆኖም ትክክለኛውን መንገድ ለሰው ያመለክት ዘንድ፣

መካከለኛም ይሆንለት ዘንድ፣

ከሺሕ አንድ መልአክ ቢገኝ፣

24ለሰውየውም በመራራት፣

‘ቤዛ አግኝቼለታለሁና፣

ወደ ጕድጓድ33፥24 ወይም፣ ወደ መቃብር እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው፣

25በዚህ ጊዜ ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤

ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።

26ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ሞገስም ያገኛል፤

የእግዚአብሔርን ፊት ያያል፤ ሐሤትም ያደርጋል፤

እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ቦታው ይመልሰዋል።

27ከዚያም ወደ ሰዎች መጥቶ እንዲህ ይላል፤

‘ኀጢአትን ሠርቻለሁ፤ ትክክል የሆነውን አጣምሜአለሁ፤

ነገር ግን የእጄን አላገኘሁም።

28ነፍሴ ወደ ጕድጓድ33፥28 ወይም፣ ወደ መቃብር እንዳልሄድ ታድጎኛል እንዳትወርድ፣

ታድጓታል፤ በሕይወትም ሆኜ ብርሃን አያለሁ።’

29“እግዚአብሔር ይህን ሁሉ፣

ሁለት ሦስት ጊዜ ለሰው ያደርጋል።

30ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ፣

ነፍሱን ከጕድጓድ33፥30 ወይም፣ ነፍሱን ከሞት ለመመለስ ነው ለመመለስ ነው።

31“ኢዮብ ሆይ፤ ልብ ብለህ ስማኝ፤

እኔ ልናገር፤ አንተ ዝም በል።

32የምትለው ካለህ፣ መልስ ስጠኝ፤

ትክክለኛነትህንም ማወቅ እፈልጋለሁና ተናገር፤

33አለዚያ፣ ዝም ብለህ ስማኝ፤

እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።”