ኢዮብ 21 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 21:1-34

ኢዮብ

1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“ቃሌን በጥንቃቄ ስሙ፤

የምታጽናኑኝም በዚህ ይሁን፤

3ንግግሬን በትዕግሥት አድምጡ፤

ከተናገርሁ በኋላ፣ መሣለቅ ትችላላችሁ።

4“በውኑ ቅርታዬ በሰው ላይ ነውን?

ትዕግሥት ማጣትስ አይገባኝምን?

5ተመልከቱኝና ተገረሙ፤

አፋችሁን በእጃችሁ ለጕሙ።

6ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤

ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።

7ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ?

ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?

8ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣

ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤

9ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤

የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።

10ኮርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤

ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።

11ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤

ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።

12በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤

በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።

13ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤

በሰላምም21፥13 ወይም በፍጥነት ማለት ነው። ወደ መቃብር21፥13 በዕብራይስጡ፣ ሲኦል ይላል። ይወርዳሉ።

14እግዚአብሔርንም እንዲህ ይሉታል፤ ‘አትድረስብን!

መንገድህንም ማወቅ አንፈልግም።

15እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?

ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’

16ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤

ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ።

17“የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?

የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣

መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?

18በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣

በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?

19እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤

ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤

20ዐይኖቹ የራሱን ውድቀት ይዩ፤

ሁሉን ከሚችል አምላክ21፥17-20 17፡18 ቃለ አጋኖዎች ሲሆኑ፣ 19፡20 ደግሞ ብያኔዎች ናቸው። ቍጣ ይጠጣ።

21ሰው ወራቱ በተገባደደ ጊዜ፣

ለቀሪ ቤተ ሰቡ ምን ይገድደዋል?

22“ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርድ አምላክ፣

ዕውቀትን ሊያስተምረው የሚችል አለን?

23አንድ ሰው በፍጹም ተድላ ደስታ እየኖረ፣

በሙሉ ብርታቱም እያለ ይሞታል፤

24ሰውነቱ21፥24 የዚህ ቃል የዕብራይስጡ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። በምቾት፣

ዐጥንቱም በሥብ ተሞልቶ እያለ በሞት ይለያል።

25ሌላው ሰው ደግሞ አንዳች መልካም ነገር ሳያይ፣

በተመረረች ነፍስ ይሞታል፤

26ሁለቱም በዐፈር ውስጥ አንድ ላይ ይተኛሉ፤

ትልም ይወርሳቸዋል።

27“እነሆ፣ ምክራችሁን፣

በእኔ ላይ ያሤራችሁትንም ተረድቻለሁ።

28እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣

ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤

29መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን?

የነገሯችሁንስ ነገር በጥሞና አላዳመጣችሁምን?

30ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣

በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ21፥30 ወይም ለመቅሠፍት ቀን ተጠብቆ እንደሚቈይ ማለት ነው። አታውቁምን?

31ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?

የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?

32ወደ መቃብር ይወስዱታል፤

ለመቃብሩም ጠባቂ ይደረግለታል።

33የሸለቈው ዐፈር ምቹ ይሆንለታል፤

ሰው ሁሉ ይከተለዋል፤

ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝብ21፥33 ወይም ስፍር ቍጥር እንደ ሌለው ሕዝብ ማለት ነው። በፊቱ ይሄዳል።

34“መልሳችሁ ከሐሰት በስተቀር ሌላ አይገኝበትም!

ታዲያ፣ በማይረባ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約伯記 21:1-34

約伯的回答

1約伯回答說:

2「你們仔細聽我說,

便是給我的慰藉。

3請容忍我把話說完,

之後任憑你們嘲笑。

4我豈是向人抱怨?

我有理由不耐煩。

5你們看到我會大吃一驚,

嚇得用手掩口。

6我一想到自己,就心驚膽戰,

渾身發抖。

7為何惡人活著,得享長壽,

勢力強大?

8他們的兒孫圍繞膝前,

他們得見後代茁壯成長。

9他們家中平安無懼,

他們不被上帝杖打。

10他們的公牛繁殖力強,

他們的母牛從不掉胎。

11他們讓孩童像羊群一樣走到戶外,

盡情地歡跳。

12他們伴著鈴鼓和豎琴歌唱,

在笛聲中歡喜不已。

13他們一生幸福,

安然下到陰間。

14他們對上帝說,『離開我們,

我們不想學習你的道。

15全能者是誰,竟要我們事奉祂?

向祂禱告有何益處?』

16看啊,他們的幸福不在他們手中;

因此,我決不苟同他們的想法。

17「惡人的燈何曾熄滅?

災難何曾臨到他們?

上帝何曾發怒使他們受苦?

18他們何曾像風中的碎稭,

像被暴風捲去的糠秕?

19你們說上帝會把懲罰留給他們的兒女,

我認為不如報應在他們本人身上,

讓他們親自領教。

20願他們親眼看見自己滅亡。

願他們喝下全能者的烈怒。

21因為他們的歲月一旦度盡,

又怎會關心身後的家人?

22「上帝既審判身居高位者,

誰還能傳授知識給祂?

23有人至死仍充滿活力,

盡享平靖安逸。

24他營養充足,

骨骼健壯。

25有人至死心中苦痛,

從未嚐過幸福的滋味。

26二者都埋入塵土,

被蛆蟲覆蓋。

27我知道你們的想法,

並那些冤枉我的詭計。

28你們問,『權貴的房子如今何在?

惡人住的帳篷今在何方?』

29難道你們沒有問過旅客,

不接受他們的說法?

30就是惡人在災難之日得到倖免,

在上帝發怒之日得以逃脫。

31誰會當面斥責他們的惡行,

因其所作所為而報應他們?

32他們被抬入墳墓後,

還有人看守墓地。

33他們在谷中的沃土安息,

送葬的人前呼後擁,不計其數。

34你們的空談怎能安慰我?

你們的回答純屬荒謬。」