ኢዮብ 2 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 2:1-13

ሁለተኛው የኢዮብ ፈተና

1በሌላ ቀን ደግሞ፤ መላእክት2፥1 የዕብራይስጡ የእግዚአብሔር ልጆች ይላል። በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ። ሰይጣንም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ሊቆም መጣ። 2እግዚአብሔር ሰይጣንን፣ “ከወዴት መጣህ?” አለው።

ሰይጣንም፣ “በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት” ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።

3እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም፤ ያለ ምክንያት እንዳጠፋው ብትወተውተኝም፣ ይኸው ፍጹምነቱን እንደ ጠበቀ ነው” አለው።

4ሰይጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል፤ 5እስቲ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፤ በርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”

6እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።

7ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጕሩ በክፉ ቍስል መታው። 8ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።

9ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው።

10እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደማታስተውል2፥10 እንደማታስተውል ተብሎ የተተረጐመው የዕብራይስጥ ቃል፣ ግብረ ገባዊ ሕጸጽን ያመለክታል። ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።”

በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።

ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች

11ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ። 12እነርሱም ከሩቅ ሆነው ሲመለከቱት እርሱ መሆኑን ሊለዩ አልቻሉም፤ በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ልብሳቸውንም ቀድደው በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ። 13ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከእርሱ ጋር መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሥቃዩ ታላቅ መሆኑንም ስለ ተረዱ፣ አንዳች ቃል የተናገረው አልነበረም።

New International Version

Job 2:1-13

1On another day the angels2:1 Hebrew the sons of God came to present themselves before the Lord, and Satan also came with them to present himself before him. 2And the Lord said to Satan, “Where have you come from?”

Satan answered the Lord, “From roaming throughout the earth, going back and forth on it.”

3Then the Lord said to Satan, “Have you considered my servant Job? There is no one on earth like him; he is blameless and upright, a man who fears God and shuns evil. And he still maintains his integrity, though you incited me against him to ruin him without any reason.”

4“Skin for skin!” Satan replied. “A man will give all he has for his own life. 5But now stretch out your hand and strike his flesh and bones, and he will surely curse you to your face.”

6The Lord said to Satan, “Very well, then, he is in your hands; but you must spare his life.”

7So Satan went out from the presence of the Lord and afflicted Job with painful sores from the soles of his feet to the crown of his head. 8Then Job took a piece of broken pottery and scraped himself with it as he sat among the ashes.

9His wife said to him, “Are you still maintaining your integrity? Curse God and die!”

10He replied, “You are talking like a foolish2:10 The Hebrew word rendered foolish denotes moral deficiency. woman. Shall we accept good from God, and not trouble?”

In all this, Job did not sin in what he said.

11When Job’s three friends, Eliphaz the Temanite, Bildad the Shuhite and Zophar the Naamathite, heard about all the troubles that had come upon him, they set out from their homes and met together by agreement to go and sympathize with him and comfort him. 12When they saw him from a distance, they could hardly recognize him; they began to weep aloud, and they tore their robes and sprinkled dust on their heads. 13Then they sat on the ground with him for seven days and seven nights. No one said a word to him, because they saw how great his suffering was.