ኢያሱ 9 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 9:1-27

የገባዖን ሰዎች የፈጸሙት ማታለል

1በዮርዳኖስ ምዕራብ ባለው በተራራማው አገር፣ በቈላማው ምድር እንዲሁም እስከ ሊባኖስ በሚደርሰው በመላው በታላቁ ባሕር9፥1 የሜድትራኒያን ባሕር ነው። ዳርቻ የነበሩት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያን፣ የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ 2ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ።

3የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ላይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፣ 4ለማታለል ፈለጉ፤ ስለዚህም ያረጀ ስልቻና የተጣፈ አሮጌ የወይን ጠጅ አቍማዳ በአህያ የጫነ9፥4 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ነገር ግን አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የቩልጌት፣ የሱርስቱ ትርጕም እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ቅጅ፣ “የሚያስፈልጋቸውን ነገር አዘጋጁ፤ በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ” ይላሉ። መልእክተኛ መስለው ሄዱ። 5ሰዎቹም ያረጀና የተጠጋገነ ነጠላ ጫማ አድርገዋል፤ አሮጌ ልብስ ለብሰዋል፤ ለስንቅ የያዙት እንጀራም በሙሉ የደረቀና የሻገተ ነበር። 6ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ኢያሱንና የእስራኤልን ሰዎች፣ “የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ” አሏቸው።

7የእስራኤልም ሰዎች ለኤዊያውያኑ፣ “እናንተ የምትኖሩት እዚሁ ቅርብ ቢሆንስ? ታዲያ ከእናንተ ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንገባለን?” አሏቸው።

8እነርሱም ኢያሱን፣ “እኛ ባሪያዎችህ ነን” አሉት።

ኢያሱ ግን፣ “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

9እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “እኛ ባሪያዎችህ የአምላካህን የእግዚአብሔርን ዝና ሰምተን፣ እጅግ ሩቅ ከሆነ አገር መጥተናል፤ ዝናውንና በግብፅ ያደረገውንም ሁሉ ሰምተናል፤ 10እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ባሉት በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለትም በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፣ አስታሮትን ይገዛ በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ነው። 11ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፣ ‘ለመንገዳችሁ የሚሆን ስንቅ ያዙ፤ ሄዳችሁም ተገናኟቸው፤ እኛ ባሮቻችሁ እንሆናለን፤ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ በሏቸው’ አሉን። 12ይህ የያዝነው እንጀራ ወደ እናንተ ለመምጣት ከቤታችን በተነሣንበት ቀን ትኵስ ነበር፤ አሁን ግን እንዴት እንደ ደረቀና እንደ ሻገተ ተመልከቱ። 13እነዚህ የወይን ጠጅ አቍማዳዎቻችን ያን ጊዜ ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን እንዴት እንደ ተቀዳደዱ ተመልከቱ፤ ልብሳችንና ጫማችንም ብዙ መንገድ በመጓዛችን ዐልቀዋል።”

14የእስራኤልም ሰዎች ከስንቃቸው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ጕዳዩ ግን እግዚአብሔርን አልጠየቁም ነበር። 15ኢያሱም በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸውን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ የጉባኤውም መሪዎች ይህንኑ በመሐላ አጸኑላቸው።

16እስራኤላውያን ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ሰሙ። 17ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደ ተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ። 18ሆኖም እስራኤላውያን አልወጓቸውም፤ የጉባኤው መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ነበርና።

ማኅበሩም ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጕረመረሙ፤ 19ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጕዳት ልናደርስባቸው አንችልም። 20እንዲህ እናደርግላቸዋለን፤ የገባንላቸውን መሐላ በማፍረስ ቍጣ እንዳይደርስብን፣ በሕይወት እንዲኖሩ እንዲሁ እንተዋቸዋለን፤ 21ነገር ግን ለማኅበረ ሰቡ በሙሉ ዕንጨት እየቈረጡ ውሃ እየቀዱ ይኑሩ።” ስለዚህ መሪዎቹ የገቡላቸው ቃል ተጠበቀ።

22ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እዚሁ አጠገባችን መኖራችሁ የታወቀ ሆኖ ሳለ፣ ‘የምንኖረው ከእናንተ በራቀ ስፍራ ነው’ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው? 23ስለዚህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ ጥቂቶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ምንጊዜም ዕንጨት ቈራጭ፣ ውሃ ቀጂ ባሮች ትሆናላችሁ።”

24እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው፣ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በርግጥ ለእኛ ለባሪያዎችህ ተነግሮናል፤ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይወታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል። 25እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።”

26ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤላውያን እጅ አዳናቸው፤ እነርሱም አልገደሏቸውም። 27በዚያችም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር ለሆነው መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ ዕንጨት ቈራጮችና ውሃ ቀጂዎች አደረጋቸው።

Swedish Contemporary Bible

Josua 9:1-27

Josua anfaller kungarna i söder

1När kungarna på västra sidan om Jordan, i bergsbygden, i Låglandet och utmed Medelhavskusten, så långt upp som till Libanon, hettiterna, amoréerna, kanaanéerna, perisséerna, hivéerna och jevuséerna hörde vad som hänt, 2slöt de sig samman för att strida mot Josua och Israel.

Givons invånare lurar Josua

3Men när invånarna i Givon hörde vad Josua hade gjort med Jeriko och Aj, 4beslöt de att försöka rädda sig med list. De skickade iväg sändebud till Josua med åsnor lastade med gamla säckar, utslitna, spruckna och lappade vinsäckar. 5Sändebuden tog på sig slitna, lagade sandaler och gamla, utslitna kläder. Deras färdkost var torrt och smuligt bröd. 6När de kom fram till lägret i Gilgal, sa de till Josua och männen i Israel: ”Vi kommer från ett avlägset land. Slut förbund med oss!”

7”Hur ska vi kunna veta att ni inte bor här i närheten?” svarade israeliterna hivéerna. ”Hur ska vi då kunna sluta något förbund med er?”

8”Vi är dina tjänare”, svarade de. ”Men vad är ni då för ena?” frågade Josua. ”Var kommer ni ifrån?” 9”Vi, dina tjänare, kommer från ett land mycket långt borta”, fortsatte de. ”Vi har hört talas om Herrens, er Guds, makt och om allt han gjorde i Egypten 10och vad han gjorde med de amoreiska kungarna på andra sidan Jordan, Sichon, kungen i Heshbon, och Og, Bashans kung, som regerade i staden Ashtarot. 11Därför sa de äldste och folket till oss: ’Förbered er för en lång resa och gå till israeliterna och säg att vi är beredda att bli deras tjänare och ingå förbund med dem.’ 12Det här brödet var varmt och kom direkt ur ugnen när vi gav oss iväg, men som ni ser är det nu torrt och smuligt. 13De här vinsäckarna var nya när vi fyllde dem, men nu är de gamla och spruckna och våra kläder och skor har hunnit bli utslitna under vår långa resa.”

14Männen tog då av deras mat9:14,15 Att äta tillsammans var en del av ritualen då man ingick förbund. och brydde sig inte om att fråga Herren. 15Josua slöt ett fredsförbund med dem där han lovade att de skulle få leva och ledarna i menigheten bekräftade det med en ed.

16Tre dagar efter att de slutit förbund kom det fram att männen i själva verket var givoniter, nära grannar9:16 Givon låg norr om Jerusalem. till Israel. 17Israeliterna drog då omedelbart iväg och nådde efter tre dagar fram till deras städer, Givon, Kefira, Beerot och Kirjat-Jearim. 18Men på grund av den ed som Israels ledare hade avlagt inför Herren, Israels Gud, kunde de inte anfalla städerna. Israeliterna klagade högljutt på sina ledare, 19men deras ledare svarade: ”Vi har avlagt en ed inför Herren att vi inte ska anfalla dem och det löftet måste vi hålla. 20Vi måste låta dem få leva, för om vi bryter eden, kommer Herrens vrede över oss.”

21De fortsatte: ”Låt dem leva, men de får hugga ved och bära vatten åt hela menigheten.” Det blev som ledarna lovat dem.

22Josua sammankallade deras ledande män och frågade: ”Varför ljög ni för oss och påstod att ni bodde långt borta i ett avlägset land när ni bor här alldeles intill oss? 23Nu kommer en förbannelse att vila över er. Från den här stunden ska ni alltid tjäna som slavar som hugger ved och bär vatten i tjänst för min Guds hus.”

24”Vi, dina tjänare, hade fått reda på att Herren, din Gud, sagt till sin tjänare Mose att han skulle ge detta land åt er och utrota alla som bor här”, svarade de. ”Vi var rädda för våra liv, det var därför vi gjorde så här. 25Men nu är vi helt i dina händer och du kan göra med oss vad du vill.”

26Josua tillät inte israeliterna att döda dem, 27utan de fick bli vedhuggare och vattenbärare åt menigheten och vid Herrens altare på den plats Herren skulle välja ut. Detta är fortfarande deras uppgift.9:27 Förbundet varade i många hundra år. Givoniterna var med och byggde upp Jerusalem efter hemkomsten från Babylon cirka tusen år senare. Se Neh 3:7.