ኢያሱ 21 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 21:1-45

ለሌዋውያን የተመደቡ ከተሞች

21፥4-39 ተጓ ምብ – 1ዜና 6፥54-80

1የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ ሌሎቹ የእስራኤል ነገድ አባቶች ዘንድ ቀረቡ፤ 2በከነዓን ምድር በሴሎም፣ “እግዚአብሔር የምንኖርባቸውን ከተሞች፣ ከብቶቻችን ከሚሰማሩባቸው ቦታዎች እንድትሰጡን በሙሴ በኩል አዝዞልን ነበር” አላቸው።

3ስለዚህ እስራኤላውያን ከወረሱት ምድር ላይ የሚከተሉትን ከተሞችና መሰማሪያዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለሌዋውያኑ ሰጡ።

4የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

5ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

6ለጌርሶን ዝርያዎች ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌም ነገድ ጐሣዎችና ባሳን ውስጥ ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።

7ለሜራሪ ዝርያዎች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ከተሞች ተመደቡላቸው።

8ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው።

9ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች ደግሞ ከዚህ በታች በስም የተጠቀሱትን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው። 10እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤

11እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋር ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 12ይሁን እንጂ በከተማዪቱ ዙሪያ ያሉትን ዕርሻዎችና መንደሮች ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። 13እንደዚሁም ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነ ማሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤ 14ደግሞም የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ 15ሖሎንን፣ ዳቤርን፣ 16ዐይንን፣ ዮጣንና ቤትሳሚስን ከነ ማሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።

17ከብንያም ነገድ፣

ገባዖን፣ ጌባዕ፣ 18ዓናቶትና አልሞን የተባሉትን አራት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

19ለካህናቱ ለአሮን ዝርያዎች ከነ ማሰማሪያቸው የተሰጧቸው ከተሞች ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

20የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

21በተራራማው በኤፍሬም ምድርም ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣ 22ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነ መሠማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው።

23እንዲሁም ከዳን ነገድ፣

ኤልተቄን፣ ገባቶን፤ 24ኤሎንና ጋትሪሞን ከነ መሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው።

25ከምናሴ ነገድ፣

እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው።

26እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው።

27የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሣዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤

ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣

በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፤

28ከይሳኮር ነገድ፣

ቂሶን፣ ዳብራት፣ 29የርሙትና ዐይን ጋኒም፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

30ከአሴር ነገድ፣

ሚሽአል፣ ዓብዶን፣ 31ሔልቃትና ረአብ እነዚህ አራት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፤

32ከንፍታሌም ነገድ፣

በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፤

33ለጌድሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነ መሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

34የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤

ከዛብሎን ነገድ፣

ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣ 35ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፤

36ከሮቤል ነገድ፣

ቦሶር፣ ያሀጽ፣ 37ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፤

38ከጋድ ነገድ፣

በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣ 39ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው፦

40የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

41እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነ መሰማሪያዎቻቸው በአጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበሯቸው፤ ማሰማሪያ የሌለው ከተማ አልነበረም።

43ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት። 44እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቷቸዋልና። 45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከሰጠው መልካም የተስፋ ቃል አንዳችም አልቀረም፤ ሁሉም ተፈጽሟል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约书亚记 21:1-45

分给利未人的城邑

1-2利未人的众族长到迦南示罗见祭司以利亚撒的儿子约书亚以色列各支派的首领,说:“耶和华借着摩西曾吩咐你们把一些城邑分给我们住,让我们可以在城郊牧养牲畜。” 3以色列人便按照耶和华的吩咐,从他们的产业中把以下的城邑及城郊分给了利未人。

4利未哥辖宗族中大祭司亚伦的子孙从犹大西缅便雅悯支派的产业中抽签得了十三座城。 5哥辖宗族中其他的人也从以法莲玛拿西半个支派的产业中抽签得了十座城。 6革顺的子孙从以萨迦亚设拿弗他利和在巴珊玛拿西半个支派的产业中抽签得了十三座城。 7米拉利的子孙按宗族从吕便迦得西布伦支派的产业中抽签得了十二座城。

8以色列人照耶和华对摩西的吩咐,把这些城邑及其草场用抽签的方式分给利未人。

9-10利未支派哥辖宗族中亚伦的子孙得到第一签,以下是从犹大西缅两支派的产业中抽出来分给他们的土地: 11犹大山区的基列·亚巴及其草场,亚巴原是亚衲人的祖先,基列·亚巴就是希伯仑12而城周围的田地和乡村已经分给耶孚尼的儿子迦勒作产业。

13以色列人把避难城希伯仑分给祭司亚伦的子孙,并把立拿14雅提珥以实提莫15何仑底璧16亚因淤他伯·示麦共九座城及其草场分给了他们。这都是从犹大西缅两支派分出来的。 17便雅悯支派的产业中分给他们的城有:基遍迦巴18亚拿突亚勒们四座城及其草场。 19亚伦的子孙中做祭司的共分到十三座城邑及其草场。

20利未哥辖宗族其他的子孙从以法莲支派的产业中分到的城邑有: 21以法莲山区的避难城示剑基色22基伯先伯·和仑共四座城及其草场。 23支派的产业中分给他们的城邑有:伊利提基基比顿24亚雅仑迦特·临门四座城及其草场。 25他们从玛拿西半个支派的产业中分到他纳迦特·临门两座城及其草场。 26以上是哥辖其他的子孙所分到的十座城及其草场。

27以色列人分给利未支派中革顺子孙的城邑有:玛拿西半个支派中巴珊哥兰避难城和比·施提拉及其草场,共两座城; 28以萨迦支派的基善大比拉29耶末隐·干宁四座城及其草场; 30亚设支派的米沙勒押顿31黑甲利合四座城及其草场; 32拿弗他利支派的哈末·多珥加珥坦加利利的避难城基低斯三座城及其草场。 33革顺人按宗族共分到十三座城邑及其草场。 34其余的利未人,就是米拉利的子孙所分到的城邑有:西布伦支派的约念加珥他35丁拿拿哈拉四座城及其草场; 36吕便支派的比悉雅杂37基底莫米法押四座城及其草场; 38迦得支派的玛哈念基列的避难城拉末39希实本雅谢四座城及其草场。 40利未人中米拉利的子孙按宗族所分到的城邑共有十二座。

41利未人从以色列各支派共分到四十八座城及其草场, 42这些城周围都有草场,城城如此。

43这样,耶和华把从前起誓赐给以色列人祖先的整个地区都赐给了以色列人,以色列人都分到土地,住了下来。 44耶和华照着给他们祖先的应许,使他们四境安宁,没有仇敌能抵挡他们。耶和华将所有仇敌都交在了他们手中。 45耶和华给以色列人的美好应许没有一句落空,全部实现了。