ኢያሱ 15 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 15:1-63

ለይሁዳ ነገድ የተመደበው ድርሻ

15፥15-19 ተጓ ምብ – መሳ 1፥11-15

1ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል።

2የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር15፥2 በዚህና በቍጥር 5 ላይ የሙት ባሕር ማለት ነው። ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤ 3ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን ዐልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤ 4በአድሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል። እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው15፥4 ዕብራይስጡ ወስናችሁ ይላል። ይህ ነው።

5በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል።

በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና 6ሽቅብ ወደ ቤትሖግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜናዊው ቤትዓረባ በኩል አድርጎ የሮቤል ልጅ የቦሀን ድንጋይ እስካለበት ይደርሳል። 7ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተ ሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል። 8እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል። 9ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል። 10ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል። 11ደግሞም በአቃሮን ሰሜናዊ ተረተር አድርጎ ወደ ሽክሮን ይታጠፍና በበኣላ ተራራ ላይ ዐልፎ እስከ የብኒኤል ይደርሳል፤ ከዚህ በኋላ ወሰኑ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

12የምድሪቱ ምዕራባዊ ወሰን የታላቁ ባሕር15፥12 በዚህና በቍጥር 47 ላይ የተጠቀሰው የሜድትራንያን ባሕር ነው። ጠረፍ ነው።

እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለውን የይሁዳን ሕዝብ በዙሪያው የከበቡት ወሰኖቹ እነዚሁ ናቸው።

13ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ። 14ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ዘሮች ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ከኬብሮን አሳደዳቸው፤ 15ከዚያም በዳቤር ሕዝብ ላይ ዘመተ፤ ዳቤር ቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበር። 16ካሌብ፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዝ ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ። 17ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።

18ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባቷ ላይ የዕርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው።15፥18 ዕብራይስጥና አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ብዙ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ግን (መሳ 1፥14 ይመ) አጥብቆ ነገራት ያላሉ። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

19እርሷም፣ “እባክህ፤ በጎ ነገር አድርግልኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጉድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።

20ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤

21በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤

ቀብስኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣ 22ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣ 23ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣ 24ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣ 25ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር 26አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣ 27ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣ 28ሐጸር ሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ 29በኣላ፣ ዒዪም፣ ዓጼም፣ 30ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሔርማ፣ 31ጺቅላግ፣ ማድማና፣ ሳንሳና 32ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው።

33በምዕራቡ በኰረብታዎች ግርጌ ያሉት ደግሞ እነዚህ ናቸው፤

ኤሽታኦል፤ ጾርዓ፣ አሽና 34ዛኖዋ፣ ዓይንገኒም፣ ታጱዋ፣ ዓይናም፣ 35የርሙት፣ ዓዶላም፣ ሰኰት፣ ዓዜቃ፣ 36ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው።

37ጽናን፣ ሐዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣ 38ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣ 39ለኪሶ፣ ቦጽቃት፣ ዔግሎን፣ 40ከቦን፣ ለሕማስ፣ ኪትሊሽ፣ 41ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው።

42ልብና፣ ዔትር፣ ዓሻን 43ይፍታሕ፣ አሽና፣ ንጺብ፣ 44ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው።

45አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋር፣ 46እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣ 47አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋር፣ ጋዛ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋር።

48በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤

ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ 49ደና፣ ዳቤር የምትባለው ቂርያትስና 50ዓናብ፣ ኤሽትሞዓ፣ ዓኒም፣ 51ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

52አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣ 53ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ 54ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያትአርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

55ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ 56ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣ 57ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

58ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣ 59ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

60ቂርያትይዓሪም የተባለችው ቂርያ ትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

61በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤

ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣ 62ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

63ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约书亚记 15:1-63

犹大支派分到的土地

1犹大支派按宗族抽签分到的土地,南到以东的边界,到旷野的最南端。 2南面的边界始于盐海南端的海湾, 3沿亚克拉滨山坡南面,经,北上至加低斯·巴尼亚南面,经过希斯仑亚达珥,再绕过甲加4押们埃及小河,直到地中海岸。

5东面以盐海南端到约旦河口为边界。

北界从约旦河口的海湾开始, 6伯曷拉,经过伯·亚拉巴北面,直到吕便的儿子波罕所立的大石; 7亚割谷往北到底璧,到谷南亚都冥隘口对面的吉甲,经隐·示麦泉,直到隐·罗结8然后再沿着欣嫩子谷而上,直到耶布斯,即耶路撒冷的南面,再到欣嫩谷西面、利乏音谷北端的山顶; 9从山顶到尼弗多亚泉,到以弗仑山的各城,直到巴拉,即基列·耶琳10巴拉向西绕到西珥山,到耶琳山北坡,即基撒仑,到伯·示麦,经亭拿11再到以革伦山北坡,转向施基仑,经巴拉山和雅比聂,直到地中海。

12西面的边界是地中海沿岸。以上是犹大人根据宗族所得地业的四界。

13约书亚又照耶和华的吩咐,在犹大支派所分到的土地之中划出基列·亚巴,即希伯仑,分给耶孚尼的儿子迦勒亚巴亚衲人的祖先。 14迦勒赶走了住在那里的亚衲族的三个族长,即示筛亚希幔挞买15再从那里起兵攻打底璧底璧以前的名字是基列·西弗16迦勒说:“谁攻取基列·西弗,我就把女儿押撒嫁给他。” 17迦勒的兄弟基纳斯的儿子俄陀聂攻取了那城,迦勒便把女儿押撒嫁给他。 18押撒出嫁的时候,劝丈夫向她父亲要一块田。她刚下驴,迦勒便问她:“你想要什么?” 19押撒答道:“请你赐福给我,你既然把南地给了我,就求你也把水泉赐给我。”迦勒就把上泉和下泉都给了她。

20以下是犹大支派按宗族所得的产业: 21在最南面靠近以东的城邑有甲薛以得雅姑珥22基拿底摩拿亚大达23基低斯夏琐以提楠24西弗提链比亚绿25夏琐·哈大他加略·希斯仑——即夏琐26亚曼示玛摩拉大27哈萨·迦大黑实门伯·帕列28哈萨·书亚别示巴比斯约他29巴拉以因以森30伊勒多腊基失何珥玛31洗革拉麦玛拿三撒拿32利巴勿实忻亚因临门,共二十九座城及其附近的乡村。

33在丘陵地带有以实陶琐拉亚实拿34撒挪亚隐·干宁他普亚以楠35耶末亚杜兰梭哥亚西加36沙拉音亚底他音基底拉基底罗他音,共十四座城及其附近的乡村。

37还有洗楠哈大沙麦大·迦得38底连米斯巴约帖39拉吉波斯加伊矶伦40迦本拉幔基提利41基低罗伯·大衮拿玛玛基大,共十六座城及其附近的乡村。

42还有立拿以帖亚珊43益弗他亚实拿尼悉44基伊拉亚革悉玛利沙,共九座城及其附近的乡村。

45还有以革伦及其附近的城邑和乡村。

46还有以革伦到地中海一带所有靠近亚实突的城邑和乡村, 47亚实突及其附近的城邑和乡村,迦萨及其附近的城邑和乡村,直到埃及小河和地中海沿岸。

48在山区有沙密雅提珥梭哥49达拿基列·萨拿——即底璧50亚拿伯以实提莫亚念51歌珊何伦基罗,共十一座城及其附近的乡村。

52还有亚拉度玛以珊53雅农伯·他普亚亚非加54宏他基列·亚巴——即希伯仑洗珥,共九座城及其附近的乡村。

55还有玛云迦密西弗淤他56耶斯列约甸撒挪亚57该隐基比亚亭拿,共十座城及其附近的乡村。

58还有哈忽伯·夙基突59玛腊伯·亚诺伊勒提君,共六座城及其附近的乡村。

60还有基列·巴力——即基列·耶琳拉巴两座城及其附近的乡村。

61在旷野有伯·亚拉巴密丁西迦迦62匿珊、盐城、隐·基底,共六座城及其附近的乡村。

63犹大人没能把住在耶路撒冷耶布斯人赶出去,他们至今仍然跟犹大人一同居住。