ኢሳይያስ 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 9:1-21

ሕፃን ተወለደልን

1ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤

2በጨለማ የሚኖር ሕዝብ

ታላቅ ብርሃን አየ፤

በሞት ጥላ9፥2 ወይም፣ በጨለማ ምድር። ምድር ለኖሩትም

ብርሃን ወጣላቸው።

3ሕዝብን አበዛህ፤

ደስታቸውንም ጨመርህ፤

ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣

ምርኮንም ሲከፋፈሉ

ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣

እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

4ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣

የከበዳቸውን ቀንበር፣

በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣

የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

5የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣

በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣

ለእሳት ይዳረጋል፤

ይማገዳልም።

6ሕፃን ተወልዶልናል፤

ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤

አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።

ስሙም፣ ድንቅ መካር፣9፥6 ወይም፣ ድንቅ፣ መካር።

ኀያል አምላክ፣

የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

7ለመንግሥቱ ስፋት፣

ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤

ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣

መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤

ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።

በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤

አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት

ይህን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ

8ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤

በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

9ሕዝቡ በሙሉ፣

ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች

ይህን ያውቃሉ፤

በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

10“ጡቦቹ ወድቀዋል፤

እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤

የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤

እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

11ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤

በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤

ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

12ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤

አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል።

ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤

እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

13ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣

የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸንበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

15ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣

ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

16ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤

የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

17ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤

አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤

የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።

ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤

እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

18እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤

እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤

ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤

ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።

19በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤

ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር

ማገዶ ይሆናል፤

ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

20በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤

ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤

በግራም በኩል ይበላሉ፤

ነገር ግን አይጠግቡም፤

እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን9፥20 ወይም፣ ክንዱን ሥጋ ይበላል።

21ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤

በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤

ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤

እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以賽亞書 9:1-21

未來的君王

1但那些受過痛苦的人必不再遇見黑暗。從前,耶和華使西布倫人和拿弗他利人住的地方受人藐視,日後必使這些地方,即約旦河對岸、沿海一帶、外族人居住的加利利得到榮耀。

2走在黑暗中的人必看見大光,

活在死亡陰影下的人必被光照亮。

3耶和華啊,你必使以色列成為大國,

人民都喜氣洋洋,

在你面前歡喜快樂,

好像豐收時那樣歡喜,

如同瓜分戰利品時那樣快樂。

4因為你必折斷他們負的軛和欺壓者的棍棒,

好像昔日你毀滅米甸人一樣;

5戰士的靴子和染血的征袍都要被丟進火裡燒掉。

6必有一個嬰兒為我們誕生,

有一個孩子要賜給我們。

祂必統治我們,

祂被稱為奇妙的策士、全能的上帝、永存的父、和平的君。

7祂的國必長治久安。

祂必坐在大衛的寶座上以公平和公義治國,

使國家永固。

萬軍之耶和華必熱切地成就此事。

耶和華要審判以色列

8主已發言責備雅各家,

他的責備落在以色列

9住在以法蓮撒瑪利亞以色列人都知道。

他們驕傲自大地說:

10「磚牆倒塌了,

我們可以鑿石重建;

桑樹砍倒了,

我們可以再種香柏樹。」

11因此耶和華必驅使敵人來攻擊他們。

12東有亞蘭人,西有非利士人,

他們必吞噬以色列

雖然如此,耶和華的怒氣還沒有止息,

祂的懲罰還沒有停止。

13以色列人沒有歸向萬軍之耶和華,

也不尋求祂。

14因此,耶和華要在一日之間剷除以色列的頭和尾。

15頭是指他們的長老和首領,

尾是指教人虛謊之事的假先知。

16這些帶領者使百姓步入歧途、

走向滅亡。

17他們目無上帝,

行事邪惡,口出狂言。

所以,主不喜歡他們的青年,

也不憐憫他們的孤兒寡婦。

雖然如此,耶和華的怒氣還沒有止息,

祂降罰的手沒有收回。

18邪惡像燃燒的火焰,

焚毀荊棘和蒺藜,點燃密林,

煙柱旋轉上騰。

19萬軍之耶和華的烈怒必如火一般燒焦大地,

人們成為燒火的柴,

甚至弟兄彼此相煎。

20他們到處搶奪食物,

仍饑餓難忍,

甚至吃自己的骨肉9·20 骨肉」或譯「臂膀的肉」。

21以法蓮瑪拿西必自相殘殺,

又聯合起來攻打猶大

雖然如此,耶和華的怒氣還沒有止息,

祂降罰的手沒有收回。