ኢሳይያስ 49 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 49:1-26

የእግዚአብሔር ባሪያ

1እናንት ደሴቶች ስሙኝ፤

እናንት በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤

በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤

ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።

2አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤

በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤

የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤

በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ።

3እርሱም፣ “እስራኤል፤ አንተ ባሪያዬ ነህ፤

በአንተ ክብሬን እገልጣለሁ” አለኝ።

4እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤

ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጕልበቴን ጨረስሁ፤

ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣

ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ።

5በእግዚአብሔር ዐይን ፊት ከብሬአለሁ፤

አምላኬ ጕልበት ሆኖልኛል፤

ባሪያው እንድሆን ከማሕፀን የሠራኝ፣

ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፣

እስራኤልን ወደ እርሱ እንድሰበስብ ያደረገኝ፣

እግዚአብሔር አሁንም እንዲህ ይላል፤

6እርሱም፣

“ባሪያዬ መሆንህ፣

የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣

የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤

ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣

ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።

7እግዚአብሔር

ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣

ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣

የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤

“ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤

ልዑላንም አይተው፤ ይሰግዳሉ፤

ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣

እግዚአብሔር ታማኝ ነው።”

የእስራኤል እንደ ገና መቋቋም

8እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በወደድሁ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤

በድነትም ቀን እረዳሃለሁ።

ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣

ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣

ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣

እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤

9የተማረኩትን፣ ‘ኑ ውጡ’

በጨለማ ያሉትን፣ ‘ነጻ ሁኑ’ እንድትል አድርጌሃለሁ።

“በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤

በተራቈተውም ኰረብታ ሁሉ ላይ መሰማሪያ ያገኛሉ።

10አይራቡም፤ አይጠሙም፤

የምድረ በዳ ትኵሳት ወይም የፀሓይ ቃጠሎ አይጐዳቸውም።

የሚራራላቸው ይመራቸዋል፤

በውሃ ምንጭ ዳርም ያሰማራቸዋል።

11ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤

ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።

12እነሆ፤ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤

አንዳንዶች ከሰሜን ሌሎች ከምዕራብ፣

የቀሩት ደግሞ ከሲኒም49፥12 የማሶሬቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፣ የሙት ባሕር ጥቅልሎች ግን፣ አስዋን ይላሉ። ይመጣሉ።”

13ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤

ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤

ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ፤

እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤

ለተቸገሩትም ይራራልና።

14ጽዮን ግን፣ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤

ጌታም ረስቶኛል” አለች።

15“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን?

ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን?

ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣

እኔ ግን አልረሳሽም።

16እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤

ቅጥሮችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።

17ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ፤

ያፈራረሱሽም ከአንቺ ይሸሻሉ።

18ዐይንሽን ቀና አድርጊ፤ ዙሪያውንም ተመልከቺ፤

ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ።

በሕያውነቴ እምላለሁ፤

እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤

እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊያቸዋለሽ” ይላል እግዚአብሔር

19“ፈራርሰሽ ባድማ ብትሆኚ፣

ምድርሽ ፈጽሞ ቢጠፋ፣

ዛሬ ለሕዝብሽ ጠባብ ብትሆኚም እንኳ፣

የዋጡሽ ከአንቺ ይርቃሉ።

20በሐዘንሽ ዘመን የወለድሻቸው ልጆች፣

ጆሮሽ እየሰማ፣

‘ይህ ቦታ በጣም ጠብቦናል፤

የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይሉሻል።

21በልብሽም እንዲህ ትያለሽ፣

‘እነዚህን የወለደልኝ ማን ነው?

እኔ ሐዘንተኛና መካን፣

የተሰደድሁና የተጠላሁ ነበርሁ፤

እነዚህን ማን አሳደጋቸው?

ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤

ታዲያ፣ እነዚህ ከየት መጡ?’ ”

22ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ አሕዛብን በጥቅሻ እጣራለሁ፤

ዐርማዬንም ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ፤

ወንዶች ልጆችሽን በዕቅፋቸው ያመጡልሻል፤

ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሙልሻል።

23ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ፣

እቴጌዎቻቸው ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤

በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤

የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ፤

አንቺም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤

እኔን ተስፋ የሚያደርጉም አያፍሩም።”

24ከተዋጊ ብዝበዛ ማስጣል፣

ከጨካኝስ49፥24 የሙት ባሕር ጥቅሎች፣ ቩልጌትና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም 25 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ ከጻድቅስ ይላል። ምርኮኞችን ማዳን ይቻላልን?

25እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤

“ከተዋጊዎች ላይ ምርኮኞች በርግጥ ይወሰዳሉ፤

ከጨካኞችም ላይ ምርኮ ይበዘበዛል፤

ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፤

ልጆችሽንም እታደጋለሁ።

26አስጨናቂዎችሽ የራሳቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤

በወይን ጠጅ እንደሚሰከር ሁሉ፣ በገዛ ደማቸው ይሰክራሉ።

ከዚያም የሰው ዘር ሁሉ፣

እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣

ታዳጊሽም የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以赛亚书 49:1-26

主的仆人

1众海岛啊,听我说!

远方的众民啊,要留心听!

我还没有出生,

耶和华就呼召我;

我还没有离开母腹,

祂就点我的名。

2祂使我的口像利剑,

用祂的手护庇我;

祂使我成为磨亮的箭,

把我藏在祂的箭囊中。

3祂对我说:“以色列啊,

你是我的仆人,

我要借着你彰显我的荣耀。”

4但我说:“我虚耗精力,

徒劳无功。

然而,耶和华必公正地待我,

我的报酬在我的上帝那里。”

5我在母腹之中,耶和华便塑造我做祂的仆人,

叫我领雅各归向祂,

以色列人召集到祂那里。

我在耶和华眼中是尊贵的,

我的上帝是我的力量。

6祂对我说:“我不仅要你做我的仆人,

去复兴雅各的众支派,

使以色列的余民重归故土,

我还要使你成为外族人的光,

好把我的救恩带到地极。”

7以色列的救赎主和圣者——耶和华对受藐视、

被本国人憎恨、

遭官长奴役的那位说:

“因为拣选你的以色列的圣者耶和华是信实的,

君王必在你面前肃然起立,

首领必在你面前俯伏下拜。”

以色列的复兴

8耶和华说:

“在悦纳的时候,我应允了你;

在拯救的日子,我帮助了你。

我要保护你,

使你做我跟民众立约的中保,

复兴家园,

分配荒凉的产业。

9你要对被囚禁的人说,

‘出来吧!’

要对暗牢中的人说,

‘你们自由了。’

他们在路上必有吃的,

光秃的山岭必有食物。

10他们不再饥渴,

也不再被热风和烈日灼伤,

因为怜悯他们的那位必引导他们,

领他们到泉水边。

11我要使我的群山变为通途,

修筑我的大路。

12看啊,他们必从远方来,

有的来自北方,有的来自西方,

还有的来自希尼49:12 希尼”可能指遥远的东方或南方某地。。”

13诸天啊,要欢呼!

大地啊,要快乐!

群山啊,要歌唱!

因为耶和华必安慰祂的子民,

怜悯祂受苦的百姓。

14锡安说:“耶和华撇弃了我,

主把我忘了。”

15耶和华说:“母亲岂能忘记自己吃奶的婴儿,

不怜悯自己亲生的孩子?

就算有母亲忘记,

我也不会忘记你。

16看啊,我已经把你铭刻在我的手掌上,

你的墙垣在我的看顾之下。

17你的儿女必很快回来,

毁灭和破坏你的必离你而去。

18举目四下看看吧,

你的儿女正聚集到你这里。

我凭我的永恒起誓,

你必把他们作为饰物戴在身上,

如新娘一样用他们妆扮自己。

这是耶和华说的。

19“你那曾经荒废、凄凉、

遭到毁坏之地现在必容不下你的居民,

那些吞灭你的人必远远地离开你。

20你流亡期间所生的子女必在你耳边说,

‘这地方太小了,

再给我们一些地方住吧。’

21你会在心里问,‘我丧失了儿女、

不再生育、流亡在外、漂流不定,

谁给我生了这些儿女?

谁把他们养大?

我孤身一人,

他们是从哪里来的?’”

22主耶和华说:

“我必向列国招手,

向万民竖立我的旗帜,

他们必抱着你的儿子、

背着你的女儿回来。

23列王必做你的养父,

王后必做你的褓姆。

他们必向你俯伏下拜,

舔你脚上的尘土。

那时你便知道我是耶和华,

信靠我的必不致失望。”

24勇士抢去的能夺回来吗?

暴君掳走的能救回来吗?

25但耶和华说:

“勇士掳去的必被夺回,

暴君抢去的必被救出。

我必与你的敌人争战,

拯救你的儿女。

26我要使那些欺压你的人吞吃自己的肉,

喝自己的血喝得酩酊大醉,

好像喝酒一样。

那时候,世人都必知道我耶和华是你的救主,

是你的救赎主,

雅各的大能者。”