ኢሳይያስ 39 – NASV & HTB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 39:1-8

ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች

1በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት። 2ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበለ፤ ለእነርሱም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ያለውን ብሩን፣ ወርቁን፣ ቅመማ ቅመሙን፣ ምርጡን ዘይት እንዲሁም የጦር መሣሪያውን በሙሉ፣ ያለውንም ንብረት አንዳች ሳያስቀር አሳያቸው። በቤተ መንግሥቱም ሆነ በግዛቱ ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው ነገር አልነበረም።

3ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው።

ሕዝቅያስም፣ “ወደ እኔ የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።

4ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው።

ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ።

5ኢሳይያስም ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ 6እነሆ፤ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹትም ሁሉ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፤ አንዳች የሚተርፍ ነገር የለም፤ ይላል እግዚአብሔር7ከአብራክህ ከሚከፈሉት፣ ከዘርህ፣ ከአንተ ከሚወለዱት ልጆች ተወስደው፣ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥት ጃንደረባዎች ይሆናሉ።”

8ሕዝቅያስም፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” አለው፤ “በዘመኔ ሰላምና ጸጥታ ከኖረ ዘንድ” ብሎ ዐስቦ ነበርና።

Het Boek

Jesaja 39:1-8

De afgezanten uit Babel

1Korte tijd later stuurde Merodach-Baladan, de zoon van Baladan en koning van Babel, Hizkia een geschenk en zijn beste wensen, want hij had gehoord dat Hizkia van een zware ziekte was genezen. 2Hizkia stelde dit gebaar erg op prijs en leidde de afgezanten uit Babel rond in het paleis. Hij liet hen zijn schatkamers zien, die gevuld waren met zilver, goud, specerijen en parfums. Ook zijn wapenvoorraad en al zijn andere schatten liet hij zien. 3Toen kwam de profeet Jesaja bij de koning en vroeg: ‘Wat hebben die mannen gezegd? Waar komen zij vandaan?’ ‘Zij komen uit het verre Babel,’ gaf Hizkia als antwoord. 4‘Wat hebben zij in uw paleis gezien?’ vroeg Jesaja. Hizkia antwoordde: ‘Ik heb hun al mijn bezittingen laten zien, al mijn kostbare schatten.’ 5Toen zei Jesaja tegen hem: ‘Luister naar deze boodschap van de Here van de hemelse legers: 6“Er komt een tijd dat alles wat u hebt, alle schatten die uw voorouders hebben verzameld, naar Babel zal worden weggevoerd. Niets zal er overblijven. 7Ook enkele van uw eigen zonen zullen worden weggevoerd om dienst te doen in het paleis van de koning van Babel.” ’ 8‘Het woord van de Here dat u hebt gesproken, is goed,’ zei Hizkia, want hij dacht bij zichzelf: ‘Gedurende mijn leven zal er in elk geval vrede heersen!’