ኢሳይያስ 24 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 24:1-23

እግዚአብሔር ምድርን ፈጽሞ ያጠፋታል

1እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድርን ባድማ ያደርጋታል፤

ፈጽሞ ያጠፋታል፤

የፍርስራሽ ክምር ያደርጋታል፤

ነዋሪዎቿንም ይበትናል።

2ነገሩ ሁሉ አንድ ዐይነት ይሆናል፤

በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣

በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣

በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣

በገዥው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣

በተበዳሪው ላይ የሚሆነው በአበዳሪው፣

በብድር ከፋይ ላይ የሚሆነው በብድር ሰጪው ይሆናል።

3ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤

ጨርሶም ትበዘበዛለች፤

እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሯልና።

4ምድር ትደርቃለች፤ ትረግፋለች፤

ዓለም ትዝላለች፤ ትረግፋለች፤

የምድርም መሳፍንት ይዝላሉ።

5ምድር በሕዝቧ ትረክሳለች፤

ሕግን ጥሰዋል፤

ሥርዐትን ተላልፈዋል፤

ዘላለማዊውንም ኪዳን አፍርሰዋል።

6ስለዚህ ርግማን ምድርን ትበላለች፤

ሕዝቦቿም ስለ በደላቸው ይቀጣሉ፤

ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ተቃጥለዋል፤

በጣም ጥቂት የሆኑት ቀርተዋል።

7አዲሱ የወይን ጠጅ ዐለቀ፤ የወይኑም ተክል ደረቀ፤

ደስተኞችም ሁሉ አቃሰቱ።

8የከበሮ ደስታ ጸጥ አለ፤

የጨፋሪዎች ጩኸት አበቃ፤

ደስ የሚያሰኘውም በገና እረጭ አለ።

9ከእንግዲህ እየዘፈኑ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤

መጠጡም ለሚጠጡት ይመርራል።

10የፈራረሰችው ከተማ ባድማ ሆነች፤

የየቤቱም መግቢያ ተዘጋ።

11በየአደባባዩ የወይን ጠጅ ያለህ እያሉ ይጮኻሉ፤

ደስታው ሁሉ ወደ ሐዘን ይለወጣል፤

ሐሤቱም ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፍቷል።

12ከተማዪቱ ፈጽማ ፈርሳለች፤

በሮቿም ደቅቀው ወድቀዋል።

13የወይራ ዛፍ ሲመታ፣

የወይንም ዘለላ ሲቈረጥ ቃርሚያ እንደሚቀር ሁሉ፣

በምድሪቱ ላይ፣

በሕዝቦችም ላይ እንዲሁ ይሆናል።

14ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፤ በደስታም ይጮኻሉ፤

ከምዕራብም የእግዚአብሔርን ክብር ያስተጋባሉ።

15ስለዚህ በምሥራቅ ለእግዚአብሔር ክብር ስጡ፤

ከባሕር ደሴቶችም፣

የእስራኤልን አምላክ፣ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ አድርጉ።

16“ለጻድቁ ክብር ይሁን” የሚል ዝማሬ፣

ከምድር ዳርቻ ሰማን፤

እኔ ግን፣ “ከሳሁ፤ መነመንሁ፤

ወዮልኝ!

ከዳተኞች አሳልፈው ሰጡ፤

ከዳተኞች በክሕደታቸው አሳልፈው ሰጡ” አልሁ።

17በምድር የምትኖር ሕዝብ ሆይ፤

ሽብር፣ ጕድጓድና ወጥመድ ይጠብቁሃል።

18ከሽብር ድምፅ የሚሸሽ፣

ወደ ጕድጓድ ይገባል፤

ከጕድጓድ የወጣም፣

በወጥመድ ይያዛል።

የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፤

የምድርም መሠረት ተናወጠ።

19ምድር ተከፈለች፤

ምድር ተሰነጠቀች፤

ምድር ፈጽማ ተናወጠች።

20ምድር እንደ ሰካራም ዞረባት፤

ነፋስ እንደሚወዘውዘውም ጐጆ ሆነች፣

የዐመፅዋ ሸክም ከባድ ስለሆነ ትወድቃለች፤

እንደ ገናም አትነሣም።

21በዚያ ቀን እግዚአብሔር

በላይ በሰማያት ያሉትን ኀይሎች፣

በታችም በምድር ያሉትን ነገሥታት ይቀጣቸዋል።

22በጕድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣

በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤

በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል24፥22 ወይም፣ ይላቀቃሉ

ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ።

23የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣

በሽማግሌዎቹም ፊት በክብሩ ይነግሣል፤

ጨረቃ ትሸማቀቃለች፤ ፀሓይም ታፍራለች።

Ketab El Hayat

إشعياء 24:1-23

تدمير الرب للأرض

1هَا إِنَّ الرَّبَّ يُخْرِبُ أَرْضَ يَهُوذَا وَيُقْفِرُهَا وَيَقْلِبُ وَجْهَهَا وَيُشَتِّتُ سُكَّانَهَا. 2وَمَا يَقَعُ عَلَى الشَّعْبِ يَقْعُ عَلَى الْكَاهِنِ أَيْضاً، وَالسَّيِّدُ كَالْعَبْدِ وَالسَّيِّدَةُ كَأَمَتِهَا وَالْبَائِعُ كَالْمُشْتَرِي، وَالْمُقْتَرِضُ كَالْمُقْرِضِ، وَالدَّائِنُ كَالْمَدِينِ. 3وَيَحُلُّ الْخَرَابُ بِالأَرْضِ وَتُنْهَبُ نَهْباً، لأَنَّ الرَّبَّ قَدْ تَكَلَّمَ بِهَذَا الْقَضَاءِ. 4وَتَنُوحُ الأَرْضُ وَتَذْوِي، وَتَضْنَى الْمَسْكُونَةُ وَتَذْبُلُ، وَيَحْزَنُ مَعَهَا عُظَمَاؤُهَا.

5تَدَنَّسَتِ الأَرْضُ تَحْتَ سُكَّانِهَا، لأَنَّهُمْ تَعَدَّوْا عَلَى الشَّرِيعَةِ، وَنَقَضُوا الْفَرَائِضَ وَنَكَثُوا الْعَهْدَ الأَبَديَّ، 6لِذَلِكَ الْتَهَمَتِ اللَّعْنَةُ الأَرْضَ، وَعُوقِبَ أَهْلُهَا بِإِثْمِهِمْ، فَاحْتَرَقَ سُكَّانُ الأَرْضِ وَلَمْ يَبْقَ مِنْهُمْ سِوَى قِلَّةٍ. 7قَدِ انْتَحَبَتِ الْخَمْرَةُ، وَذَبُلَتِ الْكَرْمَةُ، وَأَنَّ جَمِيعُ ذَوِي الْقُلَوبِ الطَّرِبَةِ. 8خَرَسَ طَرَبُ الدُّفُوفِ، كَفَّ ضَجِيجُ الْمُبْتَهِجِينَ، وَصَمَتَ مَرَحُ الْعُودِ. 9لَا يَعُودُونَ يَشْرَبُونَ الْخَمْرَ مَعَ الْغِنَاءِ، وَيَكُونُ الْمُسْكِرُ مُرّاً لِشَارِبِيهِ. 10قَدْ تَدَمَّرَتْ مَدِينَةُ الْفَوْضَى، وَأُغْلِقَ كُلُّ بَيْتٍ، فَلا يَقْدِرُ أَحَدٌ عَلَى الدُّخُولِ. 11تَرْتَفِعُ صَرْخَةٌ فِي الأَزِقَّةِ طَلَباً لِلْخَمْرَةِ الْمَفْقُودَةِ. زَالَ كُلُّ فَرَحٍ، وَتَلاشَى السُّرُورُ مِنَ الأَرْضِ 12بَقِيَ الْخَرَابُ فِي الْمَدِينَةِ، وَتَحَطَّمَتِ الْبَوَّابَاتُ فَأَصْبَحَتْ رَدْماً. 13وَهَكَذَا يَحْدُثُ فِي وَسَطِ الأَرْضِ بَيْنَ الأُمَمِ، فَيَكُونُونَ كَشَجَرَةِ زَيْتُونٍ نُفِضَتْ، أَوْ كَاللُّقَاطِ الْمُتَبَقِّي بَعْدَ قِطَافِ الْعِنَبِ.

14هَؤُلاءِ الْبَاقُونَ يَرْفَعُونَ أَصْوَاتَهُمْ وَيَهْتِفُونَ بِفَرَحٍ، وَيَشْدُونَ مِنَ الْغَرْبِ بِجَلالِ الرَّبِّ. 15لِذَلِكَ مَجِّدُوا الرَّبَّ فِي الْمَشْرِقِ، مَجِّدُوا اسْمَ الرَّبِّ إِلَهِ إسْرَائِيلَ فِي جَزَائِرِ الْبَحْرِ.

16مِنْ أَقَاصِي الْمَعْمُورَةِ سَمِعْنَا تَسَابِيحَ مَجْدٍ قَائِلَةً: «الْمَجْدُ لِلْبَارِّ». وَلَكِنِّي قُلْتُ: أَنَا هَالِكٌ! أَنَا هَالِكٌ وَيْلٌ لِي لأَنَّ الْخَونَةَ يُمَارِسُونَ الْخِيَانَةَ. الْخَوَنَةَ يُمَارِسُونَ الْخِيَانَةَ. 17فَالرُّعْبُ وَالْحُفْرَةُ وَالْفَخُّ عَلَيْكُمْ يَا سَاكِنِي الأَرْضِ. 18وَكُلُّ مَنْ يَهْرُبُ مِنْ صَوْتِ الرُّعْبِ يَقَعُ فِي الْحُفْرَةِ، وَمَنْ يَتَسَلَّقُ الْحُفْرَةَ نَاجِياً يَعْلَقُ بِالْفَخِّ، لأَنَّ الْهَلاكَ يَهْبِطُ عَلَيْكُمْ مِنَ السَّمَاءِ، وَتَتَزَلْزَلُ الأَرْضُ تَحْتَ أَقْدَامِكُمْ. 19فَالأَرْضُ مُتَصَدِّعَةٌ، وَالْمَسْكُونَةُ مُتَشَقِّقَةٌ وَمُتَزَلْزِلَةٌ. 20تَرَنَّحَتِ الأَرْضُ كَالسُّكَارَى، وَتَمَايَلَتْ كَخَيْمَةِ النَّاطُورِ وَنَاءَتْ تَحْتَ ثِقَلِ إِثْمِهَا فَتَهَاوَتْ وَلَمْ تَنْهَضْ.

21فِي ذَلِكَ الْيَوْمِ يُعَاقِبُ الرَّبُّ الْمَلائِكَةَ السَّاقِطِينَ فِي السَّمَاوَاتِ، وَالْمُلُوكَ الْمُتَغَطْرِسِينَ عَلَى الأَرْضِ، 22فَيُجْمَعُونَ مَعاً كَمَا يُجْمَعُ الأَسَارَى فِى الْجُبِّ، وَيُزَجُّونَ فِي سِجْنٍ مُغْلَقٍ، وَيَتِمُّ عِقَابُهُمْ بَعْدَ أَيَّامٍ عَدِيدَةٍ. 23ثُمَّ يَخْجَلُ الْقَمَرُ وَتُخْزَى الشَّمْسُ، لأَنَّ الرَّبَّ الْقَدِيرَ يَمْلِكُ عَلَى جَبَلِ صِهْيَوْنَ وَفِي أُورُشَلِيمَ، وَيَتَمَجَّدُ أَمَامَ شُيُوخِ شَعْبِهِ.