ኢሳይያስ 22 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 22:1-25

ስለ ኢየሩሳሌም የተነገረ ትንቢት

1ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤

እስቲ ምን ቢጨንቃችሁ ነው

ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?

2አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤

የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤

የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤

በጦርነትም አልሞቱም።

3መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤

ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤

ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣

ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።

4ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤

አምርሬ ላልቅስበት፣

ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣

ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።

5ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

በራእይ ሸለቆ፣

የመጯጯኺያ፣ የመረገጥና የሽብር፣

ቅጥሮችን የማፈራረስ፣

ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።

6ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣

ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤

ቂርም ጋሻዋን አነገበች።

7መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤

ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤

8የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።

በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣

የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤

9የዳዊት ከተማ

ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤

በታችኛውም ኵሬ፣

ውሃ አጠራቀማችሁ።

10በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤

ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።

11ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣

በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤

ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከታችሁም፤

ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።

12በዚያን ቀን ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣

ጠጕራችሁን እንድትነጩ

ማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።

13ነገር ግን እነሆ፤ ተድላና ደስታ፣

ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣

ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ፤

“እንብላ እንጠጣ፣

ነገ እንሞታለንና” አላችሁ።

14የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

15ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ሂድና ይህን መጋቢ፣

የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤

16‘እዚህ ምን ታደርጋለህ?

በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድታዘጋጅ፣

በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድትወቅር፣

ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’

17“አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤

እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።

18አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣

ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤

አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረት!

በዚያ ትሞታለህ፤

የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።

19ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤

ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።

20“በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤ 21መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። 22የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። 23በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን22፥23 ወይም፣ መቀመጫ ተብሎ መተርጐም ይችላል። ይሆናል። 24የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በእርሱ ላይ ይንጠለጠላል።

25“በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።

Japanese Contemporary Bible

イザヤ書 22:1-25

22

エルサレム陥落についての預言

1これは、エルサレムについてのことばです。

「いったい、どうしたというのでしょう。

だれもかれも、どこへ行こうとしているのでしょう。

屋上に駆け上り、何を見つめているのでしょう。

2町中が上を下への大騒ぎになっています。

あれほど繁栄していた優雅な都に、

足の踏み場もないほど死体が転がっています。

勇敢に戦い、戦死したのではなく、

疫病で倒れた人たちの死体なのです。

3指導者はわれ先に逃げ、あっさりと降伏します。

住民も脱出を図りますが、途中で捕虜になります。

4私を一人にして泣かせてください。

慰めないでください。

同胞が目の前で滅ぼされるのを見て、

どうして泣かずにおられましょう。

5ああ、胸の張り裂けそうな悲しみの日。

天の軍勢の主が与える混乱と恐怖の日。

エルサレムの城壁はくずれ落ち、

山々に断末魔の叫びがこだまします。

6-7エラム人は弓の名手、

シリヤ人は戦車をあやつる名人です。

さらに、キル人は盾を並べて逃げ場を絶ちます。

彼らは、最も美しい谷に押し寄せ、

城門の前にあふれます。

8神が防御の手を引いてしまったので、

あなたがたは武器を取りに兵器庫へ走ります。

9-11大急ぎで城壁を調べて、

修理が必要な箇所を探し、家々を見て回り、

ある家を壊して城壁を修理する材料にします。

また、二重になっている城壁の間に貯水池を造り、

下の池から水を引きます。

しかし、このような必死の努力も無駄になります。

ずっと前からこのような計画を立てていた神の助けを、

求めなかったからです。」

12天の軍勢の主である神はあなたがたに、

悔い改め、罪を犯したことを悲しんで頭をそり、

荒布で作った着物をまとうように

呼びかけました。

13ところがあなたがたは、歌と踊りと遊びに興じ、

飲み食いに明け暮れて、言います。

「さあ、大いに飲み、たらふく食べよう。

せいぜい愉快にやろうではないか。

何をやっても同じだ。

どうせ明日は死ぬのだから」と。

14全能の主は、『この罪は死ぬまで赦されない』と言います。

15-16天の軍勢の主である神は、

次のようにも語りました。

「さあ、宮殿を管理しているシェブナに言いなさい。

『おまえは岩を掘ってりっぱな墓を造ったが、

いったい自分を何者だと考えているのか。

17ああ、勇士よ。

おまえにこんなぜいたくな暮らしを許した主は、

おまえを放り投げ、捕虜として遠くへ連れて行く。

18神はおまえを手の中で丸めてまりのようにし、

草木も生えない遠くの不毛の地に投げ捨てる。

ああ、名声をほしいままにした者、国の恥さらしよ。

おまえはそこで死ぬのだ。

19わたしはおまえを追放し、

高い地位から引きずり下ろす。

20そのあとで、ヒルキヤの子である、

わたしのしもべエルヤキムを召し、

おまえの代わりとする。

21彼はおまえの長服を身に着け、

おまえの肩書きと権力を譲り受け、

エルサレムの住民とユダ国民の父となる。

22彼に、わたしの民を支配する権威を与える。

彼の言うことは何でもそのとおりになる。

誰ひとりその前に立ちはだかることはできない。

23-24わたしは彼を、わたしの民を支えるための、

しっかり打ち込まれた太い釘とする。

人々は彼に全権をゆだね、彼は家門の誉れとなる。』」

25しかし主はやがて、

壁にしっかり打ち込まれたこの太い釘を抜きます。

それはすっぽり抜け落ち、

支えていた物もいっせいにくずれ落ちます。

神がそう語ったからです。