ኢሳይያስ 10 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 10:1-34

1ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣

ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!

2የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣

የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣

መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣

ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!

3በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል?

ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ?

ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ?

ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?

4ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፣

ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም።

ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም።

እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

የእግዚአብሔር ፍርድ በአሦር ላይ

5“የቍጣዬ በትር ለሆነ፣

የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!

6ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣

እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣

አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣

በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።

7እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤

በልቡም ይህ አልነበረም፤

ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣

ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።

8እንዲህም ይል ነበር፤

‘የጦር አዛዦቼ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?’

9ካልኖ እንደ ከርከሚሽ፣

ሐማት እንደ አርፋድ፣

ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደሉምን?

10የጣዖታትን መንግሥታት፣

ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ መንግሥታት የሚበልጡትን እጄ እንደ ያዘች ሁሉ፣

11በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፣

በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?”

12ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤ 13የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤

“ ‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤

ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና።

የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤

ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤

ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ።10፥13 ወይም፣ ኀይላቸውን አዋረድሁ።

14ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣

እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤

ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣

እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤

ክንፉን ያራገበ የለም፤

አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ”

15መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን?

መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን?

በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣

ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።

16ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤

ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት

ይለኰሳል።

17የእስራኤል ብርሃን እሳት፣

ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል፤

በአንድ ቀንም

እሾኹንና ኵርንችቱን እሳት ይበላዋል፤

18ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣

የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣

ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል።

19በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች በጣም ጥቂት ናቸው፤

ሕፃን ልጅ እንኳ ቈጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል።

የተረፉት የእስራኤል ዘሮች

20በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፣

ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፣

ከእንግዲህ ወዲህ

በመታቸው ላይ አይታመኑም፤

ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ፣

በእውነት ይታመናሉ።

21የተረፉት ይመለሳሉ፣10፥21 በዚህና በ22 ላይ ዕብራይስጡ፣ ሼር ጃሹብ ይላል።

ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።

22እስራኤል ሆይ፤

ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፣

የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ።

ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጇል።

23ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል።

24ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

እንዲህ ይላል፤

“በጽዮን የምትኖሩ ሕዝቤ ሆይ፤

ግብፅ እንዳደረገብህ ሁሉ በትር ያነሡብህን፣

በሽመል የደበደቡህን አሦራውያንን አትፍራቸው።

25በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤

በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”

26የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፣

በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤

በግብፅ እንዳደረገውም ሁሉ፣

በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።

27በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣

ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤

ከውፍረትህም የተነሣ

ቀንበሩ ይሰበራል።10፥27 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ ቀንበሩ ከትከሻህ ላይ ይሰበራል ይላል።

28ወደ ዐያት ይገባሉ፣

በሚግሮን ያልፋሉ፤

ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።

29መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤

“በጌባዕ ሰፍረን እናድራለን።”

ራማ ደነገጠች፤

የሳኦል ከተማ ጊብዓ ሸሸች።

30የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺ!

ላይሻ ሆይ፤ አድምጪ!

ምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ ስሚ!

31ማድሜናህ በሽሽት ላይ ነች፤

የጌቢም ሕዝብ ሊደበቅ ይሮጣል።

32በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤

እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣

በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ

በዛቻ ነቀነቁ።

33እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

በታላቅ ኀይል ቅርንጫፎችን ይቈራርጣል፤

ረዣዥም ዛፎች ይገነደሳሉ፤

ከፍ ከፍ ያሉትም ይወድቃሉ።

34ጥቅጥቅ ያለውን ደን በመጥረቢያ ይቈራርጣል፤

ሊባኖስም በኀያሉ ፊት ይወድቃል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以赛亚书 10:1-34

1制定不义律例、起草不公法令的人啊,

你们有祸了!

2你们冤枉穷人,

夺去我子民中困苦者的权利,

掳掠寡妇,抢劫孤儿。

3在惩罚的日子,

当灾祸从远方临到你们头上时,

你们怎么办?

你们能跑到谁那里去求救呢?

你们能把财物藏在哪里呢?

4你们将不是被掳就是被杀。

虽然如此,耶和华的怒气还没有止息,

祂降罚的手没有收回。

主要审判亚述

5耶和华说:“亚述王有祸了!

他是我的愤怒之棍,

他手中拿着我发烈怒的杖。

6我要差遣他去攻打一个不虔敬的国家,

一个惹我发怒的民族,

去抢夺、掳掠他们的财物,

像践踏街上的泥土一样践踏他们。

7可是他却不这样想,

心里也不这样盘算,

他只想毁灭许多国家。

8他说,‘我的臣仆都要做藩王!

9迦勒挪岂不是和迦基米施一样吗?

哈马岂不是和亚珥拔一样吗?

撒玛利亚岂不是和大马士革一样吗?

它们不是都被我征服了吗?

10这些国家都在我的手中,

他们雕刻的偶像不胜过耶路撒冷撒玛利亚的偶像吗?

11我怎样毁灭撒玛利亚和它的偶像,

也必怎样毁灭耶路撒冷和它的偶像。’”

12主完成在锡安山和耶路撒冷要做的事后,必惩罚心里狂妄、眼目高傲的亚述王。

13因为亚述王说:

“我靠自己的力量和智慧成就了此事,

因为我很聪明。

我废除列国的疆界,

掳掠他们的财物,

像勇士一样征服他们的君王。

14我夺取列国的财物,

好像探囊取物;

我征服天下,

不过是手到擒来;

无人反抗,无人吭声。”

15然而,斧头怎能向舞动它的人自夸呢?

锯子怎能向用锯的人炫耀呢?

难道棍子可以挥动举它的人吗?

手杖可以举起它的主人吗?

16因此,主——万军之耶和华必使亚述王强健的士兵疾病缠身,

使火焰吞噬他的荣耀。

17以色列的光必成为火焰,

他们的圣者必成为烈火,

一日之间烧光亚述王的荆棘和蒺藜。

18他茂盛的树林和肥美的田园必被彻底摧毁,

犹如病人渐渐消亡。

19林中剩下的树木稀少,

连小孩子也能数清。

以色列的余民

20到那日,以色列的余民,就是雅各家的幸存者,将不再倚靠欺压他们的亚述,他们将真心倚靠耶和华——以色列的圣者, 21重新归向全能的上帝。 22以色列啊,你的人民虽多如海沙,将只有剩余的人归回。充满公义的毁灭之事已定。 23因为主——万军之耶和华必按所定的在整个大地上施行毁灭。

24因此,主——万军之耶和华说:“我锡安的子民啊,虽然亚述人像埃及人一样挥舞着棍棒毒打你们,你们不要惧怕。 25因为很快我就不再向你们发怒,我要向他们发怒,毁灭他们。” 26万军之耶和华要鞭打他们,就像在俄立磐石击杀米甸人,就像祂向海伸杖,使海水淹没埃及人。 27到那日,祂必除去亚述人加在你们肩头的重担和颈上的轭;那轭必因你们肥壮而折断。

28亚述大军攻占了亚叶

穿过米矶仑

把辎重存放在密抹

29他们过了关口,

迦巴宿营。

拉玛人战战兢兢,

扫罗的乡亲基比亚人仓皇逃跑。

30迦琳人啊,高声喊叫吧!

莱煞人啊,可怜的亚拿突人啊,

留心听吧!

31玛得米纳人逃跑,

基柄人躲藏。

32那时,亚述王必屯兵挪伯

向着锡安10:32 ”希伯来文是“女子”,可能是对锡安的昵称,下同16:152:262:11的山岭,

向着耶路撒冷的山丘摩拳擦掌。

33看啊,主——万军之耶和华要以大能削去树枝。

高大的树必被斩断,

挺拔的大树必被砍倒,

34茂密的树林必被铁斧砍掉,

黎巴嫩的大树也要倒在全能的上帝面前。