አሞጽ 6 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

አሞጽ 6:1-14

ተዘልላ ላለችው እስራኤል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

1በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣

በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣

የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣

እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!

2ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤

ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤

ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጌትም ውረዱ፤

እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታታችሁ ይሻላሉን?

የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን?

3ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣

የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!

4በዝኆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤

በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣

ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣

ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤

5ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣

በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣

6በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣

ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣

ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!

7ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናችሁ፤

መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

እግዚአብሔር የእስራኤልን ትዕቢት ይጸየፋል

8ጌታ እግዚአብሔር

“የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤

ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤

ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣

አሳልፌ እሰጣለሁ”

ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር

9በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ። 10በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

11እነሆ፤ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጥቷልና፤

ታላላቅ ቤቶችን ያወድማቸዋል፤

ትንንሾቹንም ያደቅቃቸዋል።

12ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?

ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?

እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣

የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

13እናንተ ሎዶባርን6፥13 ትርጕሙ ምንም ማለት ነው። በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፣

“ቃርናይምን6፥13 ቃርናይም ትርጕሙ ቀንዶች ማለት ነው፤ ቀንድ የጥንካሬ ምልክት ነው። በራሳችን ብርታት ይዘናል” የምትሉ።

14ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣

“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እነሆ፤ እኔ ከሐማት መግቢያ6፥14 ወይም ከመግቢያው ጀምሮ እስከ ዓረባ ሸለቆ ድረስ፣

የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ፣ በእናንተ

ላይ አስነሣለሁ።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

阿摩司書 6:1-14

預言以色列的毀滅

1錫安生活安逸舒適的人啊,

你們有禍了!

撒瑪利亞山上自覺無憂的人啊,

你們有禍了!

你們是列國之首以色列的顯要,

以色列人都仰望你們。

2你們去甲尼看看,

然後從那裡到哈瑪大城,

再到非利士人的迦特看看。

你們比這些國家更好嗎?

他們的領土不比你們的更廣闊嗎?

3你們以為災難的日子離得還遠,

就大肆施行暴政。

4你們躺在象牙床上,靠在臥榻上,

你們吃養在圈裡的肥嫩牛羊。

5你們伴著琴聲唱慵懶的歌,

大衛一樣為自己製造樂器。

6你們以大碗狂飲,

用上等膏油抹身,

卻漠不關心約瑟家的衰亡。

7所以,你們要首先被擄,

你們的宴樂將從此消逝!

8萬軍之上帝——主耶和華憑自己起誓:

「我憎惡雅各的驕傲,

厭棄他的城堡。

我要把城和城中的一切都交給敵人。」

9那時,如果一棟房子裡剩下十人,這十人也要死亡。 10親屬抬出屍體焚燒時,必問內屋的人:「你那裡還有別人嗎?」那人必回答:「沒有。」問的人必說:「不要作聲,我們不可提耶和華的名。」

11看啊,耶和華一聲令下,

大屋頓成瓦礫,小房化為碎片。

12馬能在懸崖上奔馳嗎?

牛能在海中耕作嗎?

你們卻使公正淪為毒藥,

使公義之果變成苦艾。

13你們炫耀自己征服了羅底巴

吹噓憑自己的能力奪取了加寧

14萬軍之上帝耶和華說:

以色列家啊,

我要使一個國家興起攻擊你們,

他們要從哈馬口直至亞拉巴河,

到處欺壓你們。」