አሞጽ 5 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

አሞጽ 5:1-27

የእስራኤል ሕዝብ ለንስሓ መጠራት

1የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤

2“ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤

ከእንግዲህም አትነሣም፤

በገዛ ምድሯ ተጣለች፤

የሚያነሣትም የለም።”

3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“አንድ ሺሕ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣

አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤

አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣

ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።”

4እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፤

“እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”

5ቤቴልን አትፈልጉ፤

ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤

ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤

ጌልገላ በርግጥ ትማረካለች፤

ቤቴልም እንዳልነበረች5፥5 ሐዘን ትሆናለችና።

6እግዚአብሔርን ፈልጉ፤

በሕይወትም ትኖራላችሁ፤

አለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤

እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።

7እናንት ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣

ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!

8ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣

ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣

ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣

የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣

በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣

ስሙ እግዚአብሔር ነው፤

9እርሱ በብርቱው ላይ ድንገተኛ ጥፋትን፣

በተመሸገውም ከተማ ላይ ውድመትን ያመጣል።

10እናንተ በፍርድ አደባባይ

የሚገሥጻችሁን ትጠላላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ትንቃላችሁ።

11እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤

እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤

ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣

በውስጡ ግን አትኖሩም፤

ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣

የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤

12ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደ ሆነ፣

በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና።

ጻድቁን ትጨቍናላችሁ፤

ጕቦም ትቀበላላችሁ፤

በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።

13ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።

14በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፣

መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤

ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራችሁት፣

የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።

15ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤

በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ፤

ምናልባትም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር

ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል።

16ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤

በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤

ገበሬዎች ለልቅሶ፣

አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ።

17በየወይኑ ዕርሻ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤

እኔ በመካከላችሁ ዐልፋለሁና፤”

ይላል እግዚአብሔር

የእግዚአብሔር ቀን

18የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ፣

ለእናንተ ወዮላችሁ!

የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትሻላችሁ?

ያ ቀን ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።

19ይህ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ፣

ድብ እንደሚያጋጥመው፣

ወደ ቤቱም ገብቶ፣ እጁን በግድግዳው

ላይ ሲያሳርፍ፣

እባብ እንደሚነድፈው ነው።

20የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ፣

የብርሃን ጸዳል የሌለው ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?

21“ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤

ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም።

22የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣

እኔ አልቀበለውም፤

ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት5፥22 የሰላም መሥዋዕት በመባል የሚታወቀው ነው። ብታቀርቡልኝም፣

እኔ አልመለከተውም።

23የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤

የበገናህንም ዜማ አልሰማም።

24ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣

ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።

25“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣

መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?

26ለራሳችሁ የሠራችሁትን፣

የንጉሣችሁን ቤተ ጣዖት፣

የጣዖቶቻችሁን ዐምድ፣

የአምላካችሁን5፥26 ወይም ንጉሣችሁን ሱኮትን ከፍ ከፍ አደረጋችሁት እንዲሁም ጣዖታችሁን ቀይዋን የከዋክብት አማልክታችሁን፣ ሰብዓ ሊቃናት የሞሌክን ቤተ ጣዖት እንዲሁም የአምላካችሁን የሬፋንን ከዋክብት ከፍ አደረጋችሁ ይላሉ። ኮከብ አንሥታችሁ ተሸከማችሁ።

27ስለዚህ ከደማስቆ ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋችኋለሁ፤”

ይላል ስሙ የሰራዊት አምላክ የሆነ እግዚአብሔር

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

阿摩司書 5:1-27

勸以色列人悔改

1以色列家啊,

聽我為你們唱哀歌:

2「處女以色列跌倒了,

再也站不起來;

她被遺棄在自己的土地上,

無人扶她起來。」

3因為主耶和華說:

以色列家的城邑中,

出兵一千的,只有百人生還;

出兵一百的,只有十人生還。」

4耶和華對以色列家說:

「你們要尋求我,才能存活。

5不要去伯特利求問,

不要進入吉甲

也不要前往別示巴

因為吉甲人必被擄去,

伯特利也必化為烏有。」

6你們要尋求耶和華,才能存活。

否則,祂要在約瑟5·6 約瑟家」此處指約瑟的子孫以法蓮和瑪拿西兩個支派,聖經中有時用約瑟家代指北國以色列。如烈火爆發,

吞噬伯特利,無人能撲滅。

7你們這些使正義變為苦艾、將公義丟棄在地的人啊,

8那位造昴星和參星,

使幽暗變為黎明,

使白晝變為黑夜,

召來海水澆在大地上的——

祂的名字是耶和華。

9祂使毀滅如閃電臨到強者,

摧毀他們的堅城。

10你們憎恨在城門口主持公道的人,

厭惡正直的人。

11你們踐踏窮人,

對他們橫徵暴斂。

因此,你們用鑿過的石頭建房,

卻不得居住在裡面;

你們種植佳美的葡萄園,

卻喝不到葡萄酒。

12我知道你們的過犯眾多、罪惡無數。

你們迫害義人,收受賄賂,

在城門口冤枉窮人。

13這是邪惡的時代,

所以明智者靜默不言。

14你們要棄惡從善,才能存活。

這樣,萬軍之上帝耶和華必與你們同在,

正如你們所說的。

15你們要恨惡邪惡,喜愛良善,

在城門口伸張正義,

也許萬軍之上帝耶和華會恩待約瑟的餘民。

16因此,主——萬軍之上帝耶和華說:

「哀號之聲要響遍各廣場,

哭喊之聲將充滿大街小巷。

農夫被叫來哭泣,

哭喪者被召來哀號。

17每個葡萄園都傳出哀慟的聲音,

因為我要從你們中間經過,懲罰你們。

這是耶和華說的。」

18盼望耶和華的日子到來的人有禍了!

你們為什麼盼望耶和華的日子呢?

那日將帶來黑暗,而非光明。

19你們的光景將好像人逃避獅子,

卻遇上了熊,

逃回家裡,手扶牆壁,

又被蛇咬。

20耶和華的日子將充滿黑暗,毫無光明,

一片漆黑,

毫無亮光。

21「我憎惡、鄙棄你們的節期,

厭惡你們的聖會。

22即使你們獻上燔祭和素祭,

我也不悅納;

即使你們用肥美的牲畜獻上平安祭,

我也不屑一顧。

23撤去你們嘈雜的歌聲吧,

我不想聽到你們的琴音。

24惟願公正如江河滔滔不盡,

公義如溪流綿綿不絕。

25以色列家啊,

在曠野的四十年間,

你們向我獻過祭物和供品嗎?

26你們抬著為自己造的神像——

你們的王撒固和星神迦溫

27所以,我要使你們被擄到大馬士革以外的地方。」

這是耶和華說的,祂的名字是萬軍之上帝。