ነህምያ 2 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ነህምያ 2:1-20

አርጤክስስ ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ ፈቀደለት

1በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር የወይን ጠጅ በመጣለት ጊዜ፣ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ በፊቱ ዐዝኜ አላውቅም ነበር፤ 2ስለዚህ ንጉሡ፣ “ሳትታመም ፊትህ ለምን እንዲህ ዐዘነ? መቼም ይህ የልብ ሐዘን እንጂ ሌላ አይደለም” አለኝ።

እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፤ 3ለንጉሡም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር፤ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ስትፈርስ፣ በሮቿም በእሳት ሲቃጠሉ ለምን ፊቴ አይዘን?” አልሁት።

4ንጉሡም፣ “ታዲያ ምን ትፈልጋለህ?” አለኝ።

ከዚያም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ፤ 5ለንጉሡም፣ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ቢሆንና ባሪያህ በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፣ እንደ ገና እንድሠራት አባቶቼ ወደ ተቀበሩባት ወደ ይሁዳ ከተማ እንድሄድ ይፈቀድልኝ” አልሁት።

6ከዚያም ንጉሡ አጠገቡ ከተቀመጠችው ንግሥት ጋር በመሆን፣ “ጕዞህ ምን ያህል ቀን ይፈጃል? መቼስ ትመለሳለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ንጉሡም እኔን ለመስደድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜውን ወሰንሁ።

7ደግሞም እንዲህ አልሁት፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ቢሆን፣ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በደኅና እንዲያሳልፉኝ ከኤፍራጥስ ማዶ ላሉት አገረ ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ 8እንዲሁም ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ፣ በቤተ መቅደሱ አጠገብ ላለው ግንብ በሮች፣ ለከተማዪቱ ቅጥርና እኔም ለምገባበት ቤት ሠረገላ የሚሆን ዕንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ፤” መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ነበረችና ንጉሡም ፈቀደልኝ። 9ስለዚህ በኤፍራጥስ ማዶ ወደሚገኙት አገረ ገዦች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው፤ ንጉሡም የጦር አለቆችና ፈረሰኞች አብረውኝ እንዲሄዱ አድርጎ ነበር።

10ሖሮናዊው ሰንባላጥና አሞናዊው ሹም ጦብያ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እስራኤላውያን ደኅንነት የሚቈረቈር ሰው በመምጣቱ እጅግ ተበሳጩ።

ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ተዘዋውሮ ተመለከተ

11እኔም ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም ሦስት ቀን ከቈየሁ በኋላ፣ 12ከጥቂት ሰዎች ጋር በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ እግዚአብሔር በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ሌሎች እንስሳት አልነበሩም።

13በሌሊትም ወጥቼ በሸለቆው በር በኩል አድርጌ ወደ ዘንዶው2፥13 ወይም ቀበሮ ወይም በለሱ የውሃ ጕድጓድና ወደ ቈሻሻ መድፊያው በር ሄድሁ፤ የፈረሱትንም የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና በእሳት የወደሙትን በሮች ተመለከትሁ። 14ከዚያም ወደ ውሃ ምንጭ በርና ወደ ንጉሡ ኵሬ ሄድሁ፤ ይሁን እንጂ የተቀመጥሁበትን እንስሳ ማሳለፍ የሚያስችል በቂ ቦታ አልነበረም። 15ስለዚህ ቅጥሩን እየተመለከትሁ ሌሊቱን ሸለቆውን ዐልፌ ወደ ላይ ወጣሁ፤ በመጨረሻም ተመልሼ በሸለቆው በር በኩል ገባሁ። 16ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለመኳንንቱ ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ገና ምንም የተናገርሁት ነገር ስላልነበረ፣ ወዴት እንደ ሄድሁ ወይም ምን እንዳደረግሁ ሹማምቱ አላወቁም።

17ከዚያም፣ “ያለንበትን ችግር ይኸው ታያላችሁ፤ ኢየሩሳሌም ፈርሳለች፤ በሮቿም በእሳት ጋይተዋል፤ አሁንም ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደ ገና እንሥራ፤ ከእንግዲህስ መሣለቂያ አንሆንም” አልኋቸው። 18እንዲሁም መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደ ነበረችና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኋቸው።

እነርሱም፣ “እንደ ገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉ በኋላ ይህን መልካም ሥራ ጀመሩ።

19ነገር ግን ሖሮናዊው ሰንባላጥ፣ አሞናዊው ሹም ጦብያና ዐረባዊው ጌሳም ይህን ሲሰሙ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ እንዲሁም፣ “የምታደርጉት ይህ ምንድን ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ።

20እኔም፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛ ባሪያዎቹ እንደ ገና ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም ይገባናል የምትሉት ወይም የታሪክ መታሰቢያ የላችሁም” ስል መለስሁላቸው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

尼希米记 2:1-20

尼希米返回耶路撒冷

1亚达薛西王二十年尼散月2:1 尼散月”即希伯来历的一月,阳历是三月中旬到四月中旬。,酒呈到王面前后,我端起酒递给王。在王面前,我一向没有愁容。 2王问我:“你没有病,为什么面带愁容?一定是心中烦恼。”我非常害怕。 3我对王说:“愿王万岁!我祖坟所在的城邑已成废墟,城门也被烧毁,我怎能不面带愁容?” 4王问我:“你有什么要求?”我向天上的上帝祷告后, 5回答说:“如果王认为好,如果仆人在王面前蒙恩,请王派我到犹大,重建我祖坟所在的城邑。” 6当时王后坐在王的旁边,王问我:“你要去多久?什么时候回来?”我告诉王一个日期,王欣然批准。 7我又说:“如果王认为好,求王赐我诏书,通知河西省长准我经过前往犹大8求王再发一道诏书,通知管理王室园林的亚萨,吩咐他供给我木材,用来做圣殿堡垒的门梁及建造城墙和我住的房子。”王批准了我的请求,因为我的上帝施恩帮助我。

9王派将领率骑兵沿途护送我。到了河西省长那里,我把王的诏书交给他们。 10和伦参巴拉和官长亚扪多比雅听到有人来帮以色列人谋求好处,非常不悦。

尼希米视察耶路撒冷的城墙

11我到了耶路撒冷,在那里住了三天, 12然后在夜间起来,带着几个人出去。上帝感动我要为耶路撒冷做的事,我没有告诉任何人。除了我骑的牲口外,我们没有带其他牲口。 13我穿过谷门,朝龙泉的方向走到粪厂门,在那里察看耶路撒冷倒塌的城墙和被烧毁的城门。 14我又往前走到泉门和王池,我骑的牲口无法通过那里, 15我就乘夜沿溪而上,察看城墙,然后转身取道谷门回城。 16官员不知道我到过哪里,做过何事,因为我还没有向犹太人、祭司、贵族、官员和其他要参与这工程的人透露我的计划。

17后来我对他们说:“你们都看到了我们的困境。耶路撒冷已成废墟,城门也被烧毁。来吧,让我们重建耶路撒冷的城墙,免得我们再受凌辱。” 18然后,我把我的上帝怎样施恩帮助我以及王对我说的话都告诉了他们。他们就说:“我们起来重建城墙吧!”于是他们开始做这善工。 19和伦参巴拉和官长亚扪多比雅,以及阿拉伯基善听说后,就讥笑我们,藐视我们,说:“你们在做什么?想要背叛王吗?” 20我回答他们说:“天上的上帝必使我们亨通,我们身为祂仆人,要起来重建这城墙,但你们在耶路撒冷无份、无权、无业。”