ነህምያ 12 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ነህምያ 12:1-47

ካህናትና ሌዋውያን

1ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤

ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣

2አማርያ፣ መሉክ፣ ሐጡስ፣

3ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣

4አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣

5ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣

6ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣

7ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ።

እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ።

8ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ። 9ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር።

10ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤

ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤

ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤

11ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤

ዮናታንም ያዱአን ወለደ።

12በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤

ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤

ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤

13ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤

ከአማርያ፣ ይሆሐናን፤

14ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤

ከሰብንያ፣ ዮሴፍ፤

15ከካሪም፣ ዓድና፤

ከመራዮት፣ ሔልቃይ፤

16ከአዶ፣ ዘካርያስ፤

ከጌንቶን፣ ሜሱላም፤

17ከአብያ፣ ዝክሪ፤

ከሚያሚንና ከሞዓድያ፣ ፈልጣይ፤

18ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤

ከሸማያ፣ ዮናታን፤

19ከዮያሪብ፣ መትናይ፤

ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤

20ከሳላይ፣ ቃላይ፤

ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤

21ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤

ከዮዳኤ፣ ናትናኤል።

22በኤሊያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። 23ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤሊያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። 24የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

25በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ። 26እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረ ገዥ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ።

የኢየሩሳሌም ቅጥር ምረቃ በዓል

27የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። 28መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። 29በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባና ከዓዝምት አካባቢ ነው። 30ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ።

31እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ12፥31 ወይም ከቅጥሩ ጎን እንዲሄዱ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት12፥31 ወይም ከቅጥሩ ጎን በስተ ቀኝ በኩል “ቈሻሻ መጣያ በር” ወደሚባለው ሄደ። 32እነዚህንም ሆሻያና ከይሁዳ አለቆች እኩሌቶቹ ተከተሏቸው፤ 33የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣ 34ከይሁዳ፣ ከብንያም፣ ከሸማያ፣ ከኤርምያስና፣ 35እንዲሁም መለከት ከያዙ ጥቂት ካህናትና ከአሳፍ ልጅ፣ ከዘኩር ልጅ፣ ከሚካያ ልጅ ከመታንያ ልጅ፣ ከሸማያ ልጅ፣ ከዮናታን ልጅ፣ ከዘካርያስ ጋር ነበር። 36ወንድሞቹ ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳና አናኒም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የዜማ መሣሪያዎቹን ይዘው ሄዱ፤ ሰልፉን የሚመራውም ጸሓፊው ዕዝራ ነበረ። 37“ከምንጭ በር” ተነሥተው በቀጥታ ወደ “ዳዊት ከተማ” ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ “ውሃ በር” ሄዱ።

38ሁለተኛው የመዘምራን ቡድን በስተ ግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋር ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ12፥38 ወይም ከቅጥሩ ጎን፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤ 39ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር12፥39 ወይም በጄሻና በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ “በጎች በር” ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም “በዘበኞች በር” አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።

40ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋር ቦታዬን ያዝሁ፤ 41እንደዚሁም ካህናቱ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሐናንያ መለከታቸውን ይዘው፣ 42መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ። 43እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።

44በዚያን ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሰኝተው ነበርና። 45እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ። 46ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። 47በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።

Thai New Contemporary Bible

เนหะมีย์ 12:1-47

ปุโรหิตและคนเลวี

1ต่อไปนี้คือปุโรหิตและคนเลวีซึ่งกลับมาพร้อมกับเศรุบบาเบลบุตรเชอัลทิเอล และเยชูอา ได้แก่

เสไรอาห์ เยเรมีย์ เอสรา

2อามาริยาห์ มัลลุค ฮัททัช

3เชคานิยาห์ เรฮูม เมเรโมท

4อิดโด กินเนโธน12:4 สำเนาต้นฉบับภาษาฮีบรูส่วนใหญ่ว่ากินเนธอย(ดู 12:16) อาบียาห์

5มิยามิน12:5 เป็นอีกรูปหนึ่งของมินยามิน โมอัดยาห์ บิลกาห์

6เชไมอาห์ โยยาริบ เยดายาห์

7สัลลู อาโมค ฮิลคียาห์ และเยดายาห์

คนเหล่านี้คือบรรดาผู้นำปุโรหิตกับพวกพ้องในสมัยเยชูอา

8คนเลวีได้แก่ เยชูอา บินนุย ขัดมีเอล เชเรบิยาห์ ยูดาห์ และมัททานิยาห์กับพวกพ้องซึ่งรับผิดชอบเรื่องบทเพลงขอบพระคุณ 9บัคบูคิยาห์กับอุนนีและพวกพ้องยืนอยู่ตรงกันข้ามกับพวกเขาในการรับใช้

10เยชูอาเป็นบิดาของโยยาคิม ผู้เป็นบิดาของเอลียาชีบ ผู้เป็นบิดาของโยยาดา 11ผู้เป็นบิดาของโยนาธาน และโยนาธานเป็นบิดาของยาดดูวา

12หัวหน้าครอบครัวปุโรหิตในสมัยโยยาคิมได้แก่

เมรายาห์จากครอบครัวของเสไรอาห์

ฮานันยาห์จากครอบครัวของเยเรมีย์

13เมชุลลามจากครอบครัวของเอสรา

เยโฮฮานันจากครอบครัวของอามาริยาห์

14โยนาธานจากครอบครัวของมัลลุค

โยเซฟจากครอบครัวของเชคานิยาห์12:14 สำเนาต้นฉบับภาษาฮีบรูส่วนใหญ่ว่าเชบานิยาห์(ดู 12:3)

15อัดนาจากครอบครัวของฮาริม

เฮลคายจากครอบครัวของเมเรโมท12:15 ภาษาฮีบรูว่าเมราโยท(ดู 12:3)

16เศคาริยาห์จากครอบครัวของอิดโด

เมชุลลามจากครอบครัวของกินเนโธน

17ศิครีจากครอบครัวของอาบียาห์

ปิลทัยจากครอบครัวของมินยามิน และ

ครอบครัวของโมอัดยาห์

18ชัมมุวาจากครอบครัวของบิลกาห์

เยโฮนาธันจากครอบครัวของเชไมอาห์

19มัทเทนัยจากครอบครัวของโยยาริบ

อุสซีจากครอบครัวของเยดายาห์

20คาลลัยจากครอบครัวของสัลลู

เอเบอร์จากครอบครัวของอาโมค

21ฮาชาบิยาห์จากครอบครัวของฮิลคียาห์

เนธันเอลจากครอบครัวของเยดายาห์

22บันทึกรายชื่อหัวหน้าครอบครัวของเหล่าปุโรหิตและคนเลวีในสมัยของเอลียาชีบ โยยาดา โยฮานัน และยาดดูวา ทำขึ้นในรัชกาลดาริอัสแห่งเปอร์เซีย 23หัวหน้าครอบครัวต่างๆ ในหมู่วงศ์วานของเลวีไล่ขึ้นไปถึงสมัยของโยฮานันบุตรเอลียาชีบบันทึกอยู่ในหนังสือพงศาวดาร 24บรรดาผู้นำของคนเลวีได้แก่ ฮาชาบิยาห์ เชเรบิยาห์ เยชูอาบุตรขัดมีเอล และพวกพ้องซึ่งยืนอยู่ตรงกันข้ามกับพวกเขาร้องเพลงสรรเสริญและขอบพระคุณตอบโต้กันตามที่ดาวิดคนของพระเจ้าได้กำหนดไว้

25ยามเฝ้าประตูพระวิหารซึ่งรับผิดชอบคลังต่างๆ ตามแต่ละประตูได้แก่ มัททานิยาห์ บัคบูคิยาห์ โอบาดีห์ เมชุลลาม ทัลโมน และอักขูบ 26คนเหล่านี้ปฏิบัติหน้าที่อยู่ในสมัยของโยยาคิมบุตรเยชูอา ผู้เป็นบุตรของโยซาดัก และในสมัยผู้ว่าการเนหะมีย์ และเอสราผู้เป็นปุโรหิตและธรรมาจารย์

การมอบถวายกำแพงเยรูซาเล็ม

27คนเลวีทั้งปวงทั่วแดนถูกตามตัวมายังเยรูซาเล็ม เพื่อฉลองพิธีมอบถวายกำแพงเยรูซาเล็มอย่างรื่นเริงด้วยการร้องเพลงขอบพระคุณ พร้อมด้วยเสียงฉาบ พิณใหญ่และพิณเขาคู่ 28คณะนักร้องก็ถูกรวบรวมมาจากภูมิภาคต่างๆ รอบเยรูซาเล็มคือจากหมู่บ้านชาวเนโทฟาห์ 29จากเบธกิลกาล และจากเขตเกบากับอัสมาเวท เพราะว่านักร้องเหล่านี้ได้สร้างหมู่บ้านเพื่ออยู่อาศัยรอบเยรูซาเล็ม 30เมื่อปุโรหิตและคนเลวีชำระตัวให้บริสุทธิ์ตามระเบียบพิธีแล้ว พวกเขาก็ทำพิธีชำระประชากร ประตูทั้งหลาย และกำแพงเมือง

31ข้าพเจ้าให้บรรดาผู้นำยูดาห์ขึ้นไปบน12:31 หรือไปตามแนวเช่นเดียวกับข้อ 38กำแพง และแบ่งนักร้องเป็นสองคณะใหญ่ เพื่อร้องเพลงขอบพระคุณ คณะหนึ่งเดินขึ้นไปบน12:31 หรือเดินตามแนวกำแพงไปทางขวาสู่ประตูกองขยะ 32โฮชายาห์กับผู้นำยูดาห์ครึ่งหนึ่งตามพวกเขาไป 33พร้อมด้วยอาซาริยาห์ เอสรา เมชุลลาม 34ยูดาห์ เบนยามิน เชไมอาห์ เยเรมีย์ 35รวมทั้งปุโรหิตผู้เป่าแตรกับเศคาริยาห์บุตรโยนาธาน ผู้เป็นบุตรของเชไมอาห์ ผู้เป็นบุตรของมัททานิยาห์ ผู้เป็นบุตรของมีคายาห์ ผู้เป็นบุตรของศักเกอร์ ผู้เป็นบุตรของอาสาฟ 36และพวกพ้องได้แก่ เชไมอาห์ อาซาเรล มิลาลัย กิลาลัย มาอัย เนธันเอล ยูดาห์ และฮานานี ใช้เครื่องดนตรีตามที่ดาวิดคนของพระเจ้าระบุไว้ ธรรมาจารย์เอสราเดินนำหน้าขบวน 37เมื่อมาถึงประตูน้ำพุก็เดินตรงขึ้นบันไดของเมืองดาวิดที่ทางขึ้นกำแพง และผ่านเหนือวังของดาวิดไปสู่ประตูน้ำทางทิศตะวันออก

38คณะนักร้องคณะที่สองนำขบวนไปทางตรงข้าม ข้าพเจ้าเดินตามพวกเขาขึ้นไปบนกำแพงพร้อมด้วยประชาชนอีกครึ่งหนึ่ง ผ่านหอคอยเตาอบไปยังกำแพงกว้าง 39เหนือประตูเอฟราอิม ประตูเยชานาห์12:39 หรือประตูเก่า ประตูปลา หอคอยฮานันเอล และหอคอยกองร้อย ไกลไปจนถึงประตูแกะ และพวกเขาหยุดที่ประตูยาม

40คณะนักร้องขอบพระคุณทั้งสองคณะเข้าประจำที่ในพระนิเวศของพระเจ้า ข้าพเจ้ากับเจ้าหน้าที่อีกครึ่งหนึ่งก็เข้าประจำที่ด้วย 41และปุโรหิตผู้เป่าแตรได้แก่ เอลียาคิม มาอาเสอาห์ มิยามิน มีคายาห์ เอลีโอเอนัย เศคาริยาห์ และฮานันยาห์ 42ร่วมด้วยมาอาเสอาห์ เชไมอาห์ เอเลอาซาร์ อุสซี เยโฮฮานัน มัลคียาห์ เอลาม และเอเซอร์ คณะนักร้องขับร้องเพลงโดยมียิสรายาห์เป็นผู้ควบคุม 43พวกเขาถวายเครื่องบูชามากมายในวันนั้น ต่างชื่นชมยินดีเพราะพระเจ้าประทานความชื่นชมยินดีอย่างยิ่ง ผู้หญิงกับเด็กก็ร่วมชื่นชมยินดีด้วย เสียงโห่ร้องยินดีในเยรูซาเล็มดังไปไกล

44ครั้งนั้นมีการแต่งตั้งผู้ดูแลคลังต่างๆ สำหรับของถวายผลแรกและสิบลด พวกเขาจะรวบรวมสิ่งเหล่านี้จากไร่นารอบเมืองต่างๆ มาไว้ในคลังตามที่บทบัญญัติระบุไว้สำหรับให้ปุโรหิตและคนเลวี เพราะชนยูดาห์พึงพอใจในปุโรหิตและคนเลวีผู้ปฏิบัติงาน 45พวกเขารับใช้พระเจ้าและทำหน้าที่ในพิธีชำระ คณะนักร้องและยามเฝ้าประตูพระวิหารก็เช่นเดียวกัน ต่างปฏิบัติตามพระราชโองการของดาวิดและราชโอรสโซโลมอน 46เพราะนานมาแล้วในสมัยของดาวิดและอาสาฟมีเหล่าหัวหน้ากำกับคณะนักร้องและกำกับเพลงสรรเสริญและขอบพระคุณพระเจ้า 47ดังนั้นในสมัยของเศรุบบาเบลและเนหะมีย์ ชนอิสราเอลทั้งปวงจึงนำของถวายประจำวันมาถวายสำหรับนักร้องและยามเฝ้าประตูพระวิหาร และพวกเขายังได้กันส่วนหนึ่งไว้สำหรับคนเลวีอื่นๆ คนเลวีเองก็กันส่วนหนึ่งไว้สำหรับวงศ์วานของอาโรนด้วย